Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሰላሳ ክፍል ሀያ አንድ

A user's photo.
አሠላሙ አለይኩም
ኡሡሉ ሰላሳ ክፍል ሀያ አንድ
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
ይህን (ተውሒድን) ሢያስተምሩ ለአስር አመት ቆዩ¹ ። ከአስር አመት ቡሀላ ወደ ሠማይ ተስወጡ አምስት ወቅት ሠላት ተደነገገባቸው ። መካ ውስጥ ለሶስት አመት ከሠገዱ ቡሀላ ወደ መዲና በመሠደድ ታዘዙ ።
ስደት (ከክህደት ሀገር ወደ ኢስላም ሀገር) በዚህ ህዝብ ላይ ተደነገገ ይህች ድንጋጌ ቂያማ እስክትቆም የምትቆይ ናት
አላህ እንዲህ ይላል "እነዚያ (ባለመሠደድ) ነፍሶቻቸውን የበደሉት መላኢካዎች ሢገሏቸው የት ነበራቹ ይሏቸዋል በምድር ውስጥ ደካማዎች ነበርን አሉ መላይካዎችም የአላህም መሬት ትሠደዱባት ዘንዳ ሠፊ አልነበረችምን እነዚህ መኖሪያቸው ጀሀነም ነው መመለሻነትም ከፋች () ከወነንዶች ከሤቶች እና ከህፃናት (ለመሠደድ) መላን የማይችሉ መንገድንም ያልተመሩ ደካሞች ሢቀሩ (እነሢ አይቀጡም ()እነዚያ አላህ ከነሡ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል አላህም ይቅር ባይና መሀሪ ጌታ ነው)"
ከፍ ያለው የአላህ ንግግር " እናንተ ያመናቹ ባሮቼ ሆይ የኔ ምድር ሠፊ ናት እኔን ብቻ አምልኩኝ "
በገዊይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ ፦ "የዚህ ቁርአን አንቀፅ መውረድ ምክንያት አካ ውስጥ ሳይሰደዱ በቀሩ ሙስሊሞች ምክንያት ነው አላህ ሙእሚኖች ሢል ጠራቸው "
ለስደት ከሀዲስ መረጃ "ተውበት² እስክትቋረጥ ድረስ ሒጅራ አትቋረጥም ተውበት ደግሞ ፀሀይ ከመግቢያዋ ሳትወጣ አትቋረጥም "
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
አጭር ማብራሪያ
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
¹ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ነብይ ተደርገው ከተላኩበት ሠአት አንስቶ ይህችን አለም በሞት እስከተለዩባት ወቅት ድረስ ሠዎችን ከሽርክ ከማስጠንቀቅ እና ወደ ተውሒድ ከመጣራት ተወግደው አያውቁም በተለየ መልኩ ደግሞ ለድፍን አስር አመት ሌሎች የእስልምና አርካኖችን መኲከል የትኛውንም ከማስተማራቸው በፊት በብቸኝነት ተውሒድን ነበር ሢያስተምሩ የቆዩት ከሳቸው በፊት የተላኩትም ነብያቶች ህዝባቸውን ማስተማር በተውሒድ እንደጀመሩት እሣቸውም በተውሒድ ነው የጀመሩት ዛሬ ላይ እኛም እሣቸውን የምንከተል ከሆነ የዳዕዋችንን መጀመርያም መረማመጃም መጨረሻም ተውሒድ ማድረግ የግድ ይሆንብናል
² ከወንጀል መመለስ የግድ ነው ሆኖም ሶስት ወይም አራቱ ነገሮች ከመሟላት ቅሮት የለው
1 ወንጀሉን ማቆም
2 በሠራው ወንጀል መፀፀት
3 ወደ ወንጀሉ ላለመመለስ መቁረጥ
እና ከሠው ልጅ ሀቅ ጋር ከተያያዘ
4 ሀቁ ከሆነ መመለስ ከበደለው አውፍ ማስባል… እነዚህን አሟልቶ ፀሀይ ከምእራብ ከመውጣቷ እና ገርገራ ላይ ከመድረሱ በፊት ተውበት ካደረገ አላህ ተውበቱን ይቀበላዋል ከሸርጦቹ አንዱ ከጎደለ ወይም ጊዜው ካበቃ ተውበቱ ተቀባይነቱን ያጣል ።
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል