Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቅንጭብጭብ ‪ ፂም ፂም ፂም

 Hassen Ibn Ali
ቅንጭብጭብ
‪#‎ፂም_ፂም_ፂም_ፂም_ፂም_ፂም_ፂም‬
ስለታችኛው ፂም ከዑለማዎች አንደበት
ኢማም አል-ቁርጡቢይ(ረሂመሁላህ) የታችኛውን ፂም በተመለከተ እንዲህ ይላሉ
"(ፂምን) መላጨትም፣ መንጨትም ሆነ ማሳጠር አይፈቀድም" ተህሪም ሐለቁ አል-ሊህያ ፥ 5
ሸይኹል ኢ�ስላም ኢብኑ ተይሚያህ(ረሃመሁላህ) እንዲህ ይላሉ
"የታችኛው ፂምን መላጨት እርም ነው" አል-ኢኽቲያራት አል-ዒልሚያ ፥ 6
ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አ-ሺንቂጢይ (ረሂመሁላህ) በቁርአን ላይ ነቢዩ ሐሩን(ዓ.ሰ) ለወንድሙ ነቢዩ ሙሳ(ዓ.ሰ) [የእናቴ ልጅ ሆይ ፂሜንም ፀጉሬንም አትያዘኝ] ያለበትን አንቀፅ ሲፈስሩ እንዲህ ብለዋል
"ይህች የተከበረች አንቀፅ ፂምን (እንዳለ) በመጠበቅ ላይ እንድንዘወትር የምታመላክት ነች። ፂምን በመጠበቅ (በመንከባከብ) እና ባለመላጨት ላይ ቁርአናዊ ማስረጃም ነች" አድዋኡ አል-በያን 4፥ 506-507
ሸይኽ ዓብደልዓዚዝ ቢን ባዝ(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል
"ፂምን ማሳደግ መንከባከብና መልቀቅ ግዴታ(ፈርድ) ነው፤ ይህን መተውም አይፈቀድም"
በድጋሜ ሸይኽ ኢብን ባዝ እንዲህ ይላሉ ...
"ፂምን መላጨትና ማሳጠር ኢማንን ከሚያጓድሉና ከሚያደክሙ ጥቅል ወንጀሎችና አመፀኝነት የሚቆጠር እንዲሁም የአላህን ቁጣና ቅጣት እንዳያመጣ የሚያሰጋ ነው" ውጁብ ኢዕፋኢ አል-ሊህያ ፥ 18
ሽይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል
"ፂምን መላጨት መልእክተኛውን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ማመፅ በመሆኑ ምክንያት ሐራም ነው፤ ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) "የታችኛውን ፂማችሁን አሳድጉ የቀድሞ ቀመሳችሁን ደግሞ አሳጥሩ" ብለዋልና። (ፂምን መላጨት) ከነብያት መንገድ ወጥቶ ወደ አጋርያንና ወደ መጁሳውያን(እሳት አምላኪዎች) መንገድ መሄድ ነውና" መጅሙዕ ፈታዋ ኢብን ዑሰይሚን 11፥ 125
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን(ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ብለዋል
"ትክክለኛ(ሶሂህ) የሆኑት ሐዲሶች የሚያመላክቱት ፂምን መላጨት ሀራም መሆኑን ነው" አል-በያን 312
قال القرطبي - رحمه الله تعالى - :
( لا يجوز حلقها ولا نتفها ولا قصها ) [ تحريم حلق اللحى : ( ص 5 ) ]
قال شيخُ الإسلام ابنُ تَيْمِيَّةَ - رحمه الله تعالى - :
( ويَحْرُم حلقُ اللحيةِ ) [ الاختيارات العلمية : ( ص 6 )
قال العلآمة الشنقيطي - رحمه الله تعالى - : عند تفسير قوله تعالى : ( قَالَ يَبْنَؤُمَّ لاَ تَأْخُذْ بِلِحْيَتِى وَلاَبِرَأْسِى ) :
هذه الآيةُ الكريمةُ تدلُّ على لزومِ إعفاءِ اللحية ، فهى دليلٌ قرآنىٌ على إعفاءِ اللحية وعدم حلقها .
[ أضواءالبيان : ( 4/ 506 ـ 507 ) ]
قال الشيخ ابن باز - رحمه الله تعالى - وهذا اللفظ في الأحاديث المذكورة يقتضي وجوب إعفاء اللحية وإرخائها ، وتحريم حلقها وقصها .
وقال أيضاً : إن تربية اللحية ، وتوفيرها ، وإرخاؤها ؛ فرض لا يجوز تركه )
وقال أيضاً : ( وهكذا حلق اللحية وتقصيرها من جملة الذنوب والمعاصي التي تنقص الإيمان وتضعفه
ويخشى منها حلول غضب الله ونقمته ) [ وجوب إعفاء اللحية ( ص : 18 )
قال الشيخ ابن عثيمين - رحمه الله تعالى - :حلق اللحية محرم لأنه معصية لرسول الله صلى الله عليه وسلم ، فإن النبي صلى الله عليه وسلم قال :
( أعفوا اللحى وحفوا الشوارب ) ولأنه خروج عن هدي المرسلين إلى هدي المجوس والمشركين.
[ مجموع فتاوى ابن عثيمين : ( 11 / 125 ) ]
قال الشيخ صالح الفوزان - حفظه الله - : ( إن الأحاديث الصحيحة تدل على حرمة حلق اللحية ) [ البيان : ( ص :312 ) ]