Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የማይታይ እሾህ ያላት ግጥም

'Abdellah Ibnu Mohammed

-የማይታይ እሾህ ያላት:
-ስለታማ ሜንጦ ያላት:
-ጠልፋ እምትይዝ ለተጠጋት:
-ፍቅረኞቿ ያበዱላት:
-ገንዘብና ጊዜን ሁሉየሰዉሏት:
-ከሰጋጅም ደግሞም አሏት:
-ነፍሳቸዉን የሳቱላት;
-ሶላት ሰዐት የረሱላት:
-አሱር ሶላት ወደ መግሪብ ያስጠጉላት:
-አንዳንደየም ሶላቷን ያለፉላት:
-አንዳንዱም ይሰግዳል በጉንጩ ዉስጥ ሸጉጧት:
-ካለዉ ፍቅር ካለዉ ስስት እንዳይተፋት:
-የሱ ፍቅር ከእሷ ጋር መቼ አሰበ ለሶላቱ መበላሸት:
-ወግ አይቀርም ሰገድኩ አለ እየበላት:
-አንጀቴ አያ መገን መስገድ መገን ሶላት:
-አፍ ሳይጠራ ከመብላት ከመጠጣት:
-ኧረ ስንቱ ጀዘቡላት:
-ደነዘዙም ሰከሩባት:
-ጥርሳቸዉን ሰበሩባት:
-ጥርስም ቢያጡ በድዳቸዉ ደግመዉ ቃሟት:
-አትረክርከዉ እንደ ትፋት:
-ጥቅም አጡና መጥፎ አፍ ጠረን አፈሩባት:
-ባልና ሚስት ተፋቱባት:
-ጊዜና ገንዘብ አጠፉባት:
-የአእምሮ እቃን ሰበሩባት:
-በሀሳብ ባህር ሰመጡባት:
-በመርቀን በመሳከር በእንቅልፍ እጦት:
-አተረፉ ጧት ላይ ድብርት ማታ ጩኸት:
-ኧረ ይብቃህ ተዉ ተፋታት:
-ላትቀርባት ላትድግማት:
-አቃጣይዋን አረንጓደ እርጥብ እሳት:
-አደንዛዧን "ጫት" የሚሏት::'
Abdellah Ibnu Mohammed
-የማይታይ እሾህ ያላት:
-ስለታማ ሜንጦ ያላት:
-ጠልፋ እምትይዝ ለተጠጋት:
-ፍቅረኞቿ ያበዱላት:
-ገንዘብና ጊዜን ሁሉየሰዉሏት:
-ከሰጋጅም ደግሞም አሏት:
-ነፍሳቸዉን የሳቱላት;
-ሶላት ሰዐት የረሱላት:
-አሱር ሶላት ወደ መግሪብ ያስጠጉላት:
-አንዳንደየም ሶላቷን ያለፉላት:
-አንዳንዱም ይሰግዳል በጉንጩ ዉስጥ ሸጉጧት:
-ካለዉ ፍቅር ካለዉ ስስት እንዳይተፋት:
-የሱ ፍቅር ከእሷ ጋር መቼ አሰበ ለሶላቱ መበላሸት:
-ወግ አይቀርም ሰገድኩ አለ እየበላት:
-አንጀቴ አያ መገን መስገድ መገን ሶላት:
-አፍ ሳይጠራ ከመብላት ከመጠጣት:
-ኧረ ስንቱ ጀዘቡላት:
-ደነዘዙም ሰከሩባት:
-ጥርሳቸዉን ሰበሩባት:
-ጥርስም ቢያጡ በድዳቸዉ ደግመዉ ቃሟት:
-አትረክርከዉ እንደ ትፋት:
-ጥቅም አጡና መጥፎ አፍ ጠረን አፈሩባት:
-ባልና ሚስት ተፋቱባት:
-ጊዜና ገንዘብ አጠፉባት:
-የአእምሮ እቃን ሰበሩባት:
-በሀሳብ ባህር ሰመጡባት:
-በመርቀን በመሳከር በእንቅልፍ እጦት:
-አተረፉ ጧት ላይ ድብርት ማታ ጩኸት:
-ኧረ ይብቃህ ተዉ ተፋታት:
-ላትቀርባት ላትድግማት:
-አቃጣይዋን አረንጓደ እርጥብ እሳት:
-አደንዛዧን "ጫት" የሚሏት::