Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቤተሰቦቻችንስ ?

'‎ልክ እንደሌላውም ከሃገር ወጥታቹ ባህር ማዶ የምትኖሩ ወንድሞችና እሕቶች በቅድሚያ እጃቹ ላይ ያለውን ኒዕማ (ኢንተርኔት) በመጠቀም ሸሪዓዊ ዕውቀታቹን አጎልብቱ ። 
ቀጥሎም ቤተሰቦቻቹ ጋር በመፃፃፍ ፣ ስልክ በመደወል በጥሩ ልታዟቸው ከመጥፎም ልትከለክሏቸው ሐቅ እንዳለባቹ አትዘንጉ ። 

ምንም ዛሬ ብትራራቁም የወለዷቹን ቤተሰቦች ፣ ያደጋቹበትን ቤት ፣ዘመድ አዝማድ ወደ ኸይር ከመጥራት አትቦዝኑ ። በኢትዮ በአራቱም አቅጣጫ ሁላችንም አካባቢ ሽርክ ፣ ቢድዓ ይሰራል ። የአንዳንዶቻችን ቤተሰቦች ደግሞ በነዚህ ከባባድ ወንጀሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ናቸው ። ታዲያ ዛሬ እኛ ዕውቀትን ሸምተን ከዚህ ጨለማ  ብንወጣ ወላጆቻችንን በዝምታ ማለፋችን ራስ ወዳድነት አይሆንብንም? አላህ ፊትስ አያስጠይቀንም ያ ጀምዓ ? 

“ ፋዘር ሃርደኛ ነው ፣ ማዘር ትቆጣለች ” በሚል ተልካሻ ምክንያት ወደ እሳት ሲሄዱ እያየን ዝምታን መምረጡ ወላሂ ወላሂ የነሱን አማና መካድ ነው። 
 
እዚህ ጋር የውዱ ወንድሜን ሳዳት ከማል (አላህ ይጠብቀውና) ምክር ልዋሰውና በአንድ ሙሓደራው ላይ እንዲህ አለ:-
‹‹ አንዳንዱ... “ለምን የገዛ አባህን ከዚህ የሽርክ ተግባር (ቀብር አምልኮ የመሳሰሉት) ይቅርቦት” አትላቸውም ሲባል  ምን እንደሚል ታውቃላቹ  ? “ተወው ባክህ! በፋዘር ሙድ አልገባም” 
 ሱብሃነላህ!! ስማኝ ወንድሜ!
 አንተ ልጅ እያለህ ዳዴ እያልክ ወደ እሳት ስትጠጋ አባትህ.. “በልጄ ሙድ አልገባም” ብለው ዝም አላሉክም ባይሆን እሳቱ እንዳያቃጥልህ አፈፍ አድርገው ጥፍርግ ነው የያዙህ ! እንደውም አባትህና እናትህ... “ጀምዓ ሰላት ስንሰግድ ልጃችን ኤሌክትሪክ ይጨብጥብንና ይሞትብናል” ብለው አንተን እየጠበቁህ  በየተራ ነበር የሰገዱት ። ተመልከት..! ይሄ የዱኒያው እሳት ነው ። አንተ ግን ዛሬ ሸሪዓዊ ዕውቀትን ይዘህ ስታበቃ ሽርኩና ተውሒዱን ለይተህ ስታበቃ ወላጆችህ ወደ ተንቀልቃዩ የጀሃነም እሳት ሲሄዱ እያየህ “በሙዳቸው አልገባም”  ትላለህን ? ›› 

ስለዚህ ወንድሞቼና እሕቶቼ ሃገር ውስጥም ብንሆን ከሃገር ውጪ ብንሆን ቤተሰቦቻችንን በተውሒድ በማዘዝ ከሽርክ በመከልከል ወደሱና በመጥራት ከቢድዓ በማስጠንቀቅ ከትላልቅም ይሁን ከትናንሽ ወንጀሎች እንዲቆጠቡ በጥበብ መምከሩን አንዘንጋ ።

{{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا }}
(( እናንተ ያመናችሁ ሆይ፦ ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ)) [ተሕሪም-6]

ባረከላሁ ፊኩም‎'
ልክ እንደሌላውም ከሃገር ወጥታቹ ባህር ማዶ የምትኖሩ ወንድሞችና እሕቶች በቅድሚያ እጃቹ ላይ ያለውን ኒዕማ (ኢንተርኔት) በመጠቀም ሸሪዓዊ ዕውቀታቹን አጎልብቱ ።

ባረከላሁ ፊኩም