Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ግልፅ ሜዳ ላይ ነው የተውኳችሁ፡፡-----


'ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ግልፅ ሜዳ ላይ ነው የተውኳችሁ፡፡ ሌሊቱ እንደቀኑ ፍንትው ያለ፡፡ ጠፊ ካልሆነ በቀር ከዚህ አያዘነብልም፡፡” ይላሉ፡፡ ታዲያ ግልፅ ከሆነ ለምን እንደናበራለን? አሁንም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሁለት ነገሮችን ትቼላችኋለሁ፡፡ እነሱን እስከያዛችሁ ድረስ አትጠሙም” በማለት ወደ ቁርኣንና ሱና ያመላክቱናል፡፡ ሁለቱም በመካከላችን አሉ፡፡ እኛ ግን መአት አይነት ሆነናል፡፡ ለምን? ችግሩ ቁርኣኑንና ሱናውን ልንረዳ የምንፈልግበት መነፅር መለያየቱ ነው፡፡ አንዱ ቁርኣኑን በሱፍያ መነፀር ማየት ያሰኘዋል፡፡ ሌላው በኸዋሪጅ መነፀር መመልከት ያምረዋል፡፡ እዚያጋ በኢኽዋን መነፀር ካልታየ በቀር ቁርኣኑም ቁርኣን ሐዲሡም ሐዲሥ አይመስለውም፡፡ እዚያ ማዶ ደግሞ ሻንጣ ካልተሸከመ በቀር ጭራሽ ምንም አይታየውም፡፡ ሲሸከም ደግሞ ነገሮች የሚታዩት ተገልብጠው ነው፡፡ “ከሚበትን ሱና የሚሰበስብ ቢድዐ ይሻላል”ይልሃል፡፡ ትክክለኛው መነፅር ግን ሊጠቀምበት ለፈለገው ብዙም ርቀት የለውም፡፡ መነፀሩ የሰለፎች፣ የሰሐቦች፣ የታቢዖች የአትባዑታቢዒን መነፀር ነው፡፡ የነዚያ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከትውልድ ሁሉ በላጩ የኔ ትውልድ ነው” ያሏቸው እንቁ ትውልዶች መነፅር፡፡ ሰው በሌ ግን ያለዚህ ትክክለኛ መነፅር ከለበት ጭግር ሊወጣ ይቧጭራል፡፡ ሃይሃት!
ያለ አቅጣጫ እያየክ መድህንን አታልም
ጀልባ በየብስ ላይ ሲሄድ ታይቶ አያውቅም'
ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ግልፅ ሜዳ ላይ ነው የተውኳችሁ፡፡ ሌሊቱ እንደቀኑ ፍንትው ያለ፡፡ ጠፊ ካልሆነ በቀር ከዚህ አያዘነብልም፡፡” ይላሉ፡፡ ታዲያ ግልፅ ከሆነ ለምን እንደናበራለን? አሁንም ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሁለት ነገሮችን ትቼላችኋለሁ፡፡ እነሱን እስከያዛችሁ ድረስ አትጠሙም” በማለት ወደ ቁርኣንና ሱና ያመላክቱናል፡፡ ሁለቱም በመካከላችን አሉ፡፡ እኛ ግን መአት አይነት ሆነናል፡፡ ለምን? ችግሩ ቁርኣኑንና ሱናውን ልንረዳ የምንፈልግበት መነፅር መለያየቱ ነው፡፡ አንዱ ቁርኣኑን በሱፍያ መነፀር ማየት ያሰኘዋል፡፡ ሌላው በኸዋሪጅ መነፀር መመልከት ያምረዋል፡፡ እዚያጋ በኢኽዋን መነፀር ካልታየ በቀር ቁርኣኑም ቁርኣን ሐዲሡም ሐዲሥ አይመስለውም፡፡ እዚያ ማዶ ደግሞ ሻንጣ ካልተሸከመ በቀር ጭራሽ ምንም አይታየውም፡፡ ሲሸከም ደግሞ ነገሮች የሚታዩት ተገልብጠው ነው፡፡ “ከሚበትን ሱና የሚሰበስብ ቢድዐ ይሻላል”ይልሃል፡፡ ትክክለኛው መነፅር ግን ሊጠቀምበት ለፈለገው ብዙም ርቀት የለውም፡፡ መነፀሩ የሰለፎች፣ የሰሐቦች፣ የታቢዖች የአትባዑታቢዒን መነፀር ነው፡፡ የነዚያ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከትውልድ ሁሉ በላጩ የኔ ትውልድ ነው” ያሏቸው እንቁ ትውልዶች መነፅር፡፡ ሰው በሌ ግን ያለዚህ ትክክለኛ መነፅር ከለበት ጭግር ሊወጣ ይቧጭራል፡፡ ሃይሃት!
ያለ አቅጣጫ እያየክ መድህንን አታልም
ጀልባ በየብስ ላይ ሲሄድ ታይቶ አያውቅም