Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"በሱመያ" ስም መነገድ ይቁም።

"በሱመያ" ስም መነገድ ይቁም።
የጥመት መንገድ ላይ ያሉ ሰዎች ባጢላቸውን፣ ጥፋታቸውን ጥሩ ስም ይሰጡታል፣ ጥሩውን መንገድ መጥፎ ስም ይሰጡታል። ይሄ ከጥንት ጀምሮ የጥመት አካሄድ እና ባለቤቶቹ የሚሄዱበት ነው።
የቅርብ ጊዜው ማታለያ ደግሞ "የሱመያ ድምፅ፣ የሱመያ ጉዳይ" እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
1) ምንም ቁርዓናዊ እና ሀዲሳዊ ማስረጃ ሳትጠየቅ ቁጭ በይ ስትባል ቁጭ፣ ቁሚ ስትባይ ቆም፣ ዘምሪ ስትባል መርሃባ፣ ያለችውን እህት "ሱመያዎች አኮራችሁን" ብሎ ውጭ አገር ያለው ይሰብካቸዋል። እነሱም እውነት ይመስላቸዋል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን።
2) እውነት የሱመያ ጉዳይ የሚያስጨንቀው ሱመያ ላይም ይሁን ቢላሎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው እያወቀ "ውጡ" ብሎ እሱ ቦታው ላይ ሳይገኝ አሳልፎ ይሰጣቸዋል?
ከዛም በኀላ ካለበት ድሎት የአዞ እምባውን እያነባ ዜና ይዘግብባቸዋልን???
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን።

ሱመያን ለአደጋ ማግዶ እሷን የዜና ማጣፈጫ ማድረግ ይብቃ። ዲኗን እንዳትማር የመፈክር መዓት አስጠንተህ ካለህበት ትልካታለህ፣ አሳልፈህም የሌሎች መጫወቻ ታስደርጋታለህ
"እራሱ በድሎ እራሱ አለቀሰ" ሆነ እኮ ነገሩ። ደግሞ ብለህ ብለህ "የሱመያ ጉዳይ፣ የሂጃብ ጉዳይ የማያሳስባቸው፣ ለሴት ልጅ ሰላማዊ ሰልፍ አይበቃም የሚሉ" እያልክ የአብዬን ለእምዬ እንደሚሉት ታደርገው ነገር አለሙን??? አረ አላህን እንፍራ።
አሁን እማ ሱመያ በአላህ ፈቃድ ነቅታለች፣ መከራዋን ያንተ የዜና ማጣፈጫ ልታደርገው አትችልም። ሃይማኖትዋን መማር ጀምራለች አልሃምዱሊላህ። የጥመት ቡድን የሆኑትን ሱፍያ እና አሽአርያን አትንኩ ብለህ እንዳልሰበካት፣ እሷ ግን ዛሬ በአላህ ፍቃድ ሀቅ አንድ ብቻ እንደሆነች አውቃለች።
በአንድ እራስ ሁለት ምላስ አትሁን። ያኔ ብዙም እውቀት ሳይኖራት "ሱመያ" እያልክ እንዳላሞካሸሃት፣ ዛሬ ያንተን መፈክር እና ፍልስፍና አልቀበልም፣ እስቲ ዲኔን ልወቅበት፣ ሸሪዓ ያዘዘኝ ሌላ አንተ የምታዘኝ ሌላ ስትልህ ማስረጃ ማምጣት ሲያቅትህ ስም አታውጣላት። ስም ብታወጣላትም በአላህ ፍቃድ ማንነትህን ጠንቅቃ እንድታውቅ ያደርጋታል እንጂ ወደኀላ አይመልሳትም በአላህ ፈቃድ።
ደዩሱ እማ ሱመያን እንድትደበደብ እና ስቃይ እንዲደርስባት ውጭ አገር ወይንም online ተቀምጦ የሚቀሰቅሳት ነው።
መቼም ሃቅ ግልፅ ያለች ናት። ጥቂቶች እያሉ ከፖለቲከኞች በወረሷት ኩነና ቢወርፏትም ሃቅ በሃቅነቷ ትሰነብታለች፣ ከሃቅ ያፈገፈገ ነፍሱን እንጂ ሃቅን አይጎዳትም።
አሁንም ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው። ከዚህ በፊት ኡማው ላይ የደረሰው ትምህርት ሊሆን ይገባል። የሙስሊሞች ደም የሚፈስበት በሆነ ጉዳይ ላይ ዝም ብሎ መቀስቀስ ሳይሆን፣ ነገ አላህ ፊት የዚህ ደም ተካፋይም ልሆን እችላለሁ ብሎ ቆም ብሎ ማሰብ ይበጃል።
እውነተኛ ወደ አላህ መመለስ በእያንዳችን ላይ ይጠበቃል።
አሳዛኙ ፣ ተውበት እናድርግ፣ ትግስት እናድርግ፣ እንረጋጋ ሲባል አብዛኞች ውጭ ተቀምጠው "ፈሪዎች፣ ድል እጅ አጣጥፎ ይመጣል፣ እኛ ለዲናችን እንሞታለን" እና የመሳሰለውን ብለው ይሰብካሉ። ሱብሃነላህ ሸሪዐው የጠቆመበትን ትግስት፣ መረጋጋት፣ ዱዐ ለውጥ እና መፍትሄ ካላመጣ መፈክር ማሰማት ይሆን ለውጥ የሚያመጣው???
ሀስቡነላሁ ወኒእመል ወኪል።
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን።