Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለየትኛውም ዘመን ስኬት

ለየትኛውም ዘመን ስኬት
በ 21ኛው ክፍለ ዘመንም ይሁም በ 22 ኛው እናም ከዛም በኋላ ያለ ተውሂድ (አላህን በብቸኝነት ማምለክ፤ ከአላህ ውጭ ባሉት ሁሉ መካድ) እና ሽርክን በመራቅ እንጂ ፈላህ (ነፃ መውጣት) አይገኝም፡፡
እንዲያውም ቂያማ የምትቆመው መጥፎ ሰዎች ላይ ነው፡፡ ልቡ ውስጥ የጎመንዘር ፍሬ ታክል ኢማን ያለውን ሰው ያቺ ንፋስ ሰበብ ሆና ትገለዋለች፤ ከዛም መጥፎ የሆኑ ሰዎች ላይ ነው ቂያማ የሚቆመው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ምድር ላይ አላህ አላህ የሚል በሌላ ዘገባ ላኢላሃኢለላህ የሚል ሰው ሲጠፋ ቂያማ ትቆማለች››
ስለዚህ ዘመን ሰልጥኗል ቢባልም (21፣22፣ እና የመሳሰለውን ክፍለ ዘመን) ተውሂድ አንገብጋቢነቱ፤ አስፈላጊነቱ፤ ተቀዳሚነቱ ማንም ሊክደው አይችልም ወይ አውቆ አጥፊ ወይ ስለ ተውሂድ ምንነት ያልተረዳ ቢሆን እንጂ፡፡
አላህ ሆይ! ተውሂድን አሳውቀን፤ በተውሂድ ላይ አኑረህ፤ በተውሂድ ላይ ግደለን፡፡