Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 16

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 16
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ስለመመስከር መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ « ከጎሣችሁ የሆነ፣ችግራችሁ በሡላይ የሚጠና የሆነ ፣ እናንተ መልካም ነገር እንድታገኙ የሚጓጓ ፣በምእመናን ላይ አዛኝ እና ሩህሩህ የሆነ መልዕክተኛ በርግጥ መጥቶላቹሀል»
ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ የመመስከር ትርጉም፦ ያዘዙትነን መታዘዝ ፣ የተናገሩትን እውነት ማለት.፣ የከለከሉትን መከልከል ፣ አላህን በሚገዛበት ወቅት ረሡል መንገድ ካደረጉት ውጪ ላይገዛ አለመገዛት
አጭር ማብራርያ
☞ ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን የምስክርነት ቃሉን የሠጠ ሠው እነዚህን አራት ነገሮች አምኖ መቀበል እና በተግባር ላይ የማዋል ግዴታ አለበት
① የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል እና ማመን አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ « በአላህ እና በመልዕክተኛው በዛም ባወረድነው ብርሀን እመኑ አላህ በምትሠሩት ስራ ውስጥ አዋቂ ነው» ((ተጋቡን 8)
የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ « ሠዎችን ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብለው እስኪያምኑ ድረስ እና በኔ እና ይዤ በመጣሁት ነገር እስኪያምኑ ድረስ እንድጋደላቸው ታዝዣለው»
★ እውነት ብሎ መቀበል ማለት መልዕክተኛነታቸውን እና ይዘውት ያመጡትን ነገር አምኖ መቀበል ማለት ነው
② ያዘዙትን መታዘዝ ፦ የአላህ መልዕክተኛን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም መልዕክተኛነት ያመነ ሙስሊም በአጠቃላይ የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ያዘዙትን የመታዘዝ ግዴታ አለበት አላህ እንዲህ ይላል
« መልዕክተኛው ያመጣላችሁን ነገር በአጠቃላይ ያዙት» የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ « እኔን የታዘዘኝ በርግጥ አላህን ታዟል …»
③ የከለከሉትን መከልከል ፦ አላህ እንዲህ ይላል ፦ «… መልዕክተኛው የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ»
የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ «… እኔን ያመፀ በርግጥም አላህን አምፆል» የአላህ መልዕክተኛን አለመታዘዝ ከጀነት እንቢ እንደማለት ነው.የአላህ መልዕክተኛ « ኡመቴ ባጠቃላይ ጀነት ይገባል እምቢ ያለ ሢቀር» . ሢሉ ማነው እምቢ የሚለው ተብለው ሢጠየቁ የታዘዘኝ ጀነት ይገባል ያመፀኝ ከጀነት አልገባም አለ» በማለት መለሡ.
④ አላህን በሚገዛበት ግዜ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በደነገጉት መልኩ መሆን አለበት ፦ አጠቃላይ የምንሠራቸው ኢባዳዎች ከሦስቱ የወጣ መሆን የለበትም ¹ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የተናገሩት ² ተግብረው ያሣዩት ³ ሢሠራ አይተው ዝም ያሉት ተግባር መሆን አለበት ከዚህ ውጪ. ያለው ቢድአ ወይም በዲን ላይ አዲስ ፈጠራ ነው ይህንን ደግሞ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አጥብቀው ከልክለውታል እንዲህ ይላሉ « የኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ወደ ራሡ ተመላሽ ነው»
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
share ማድረጎን እንዳይረሡ