Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጀነት መንገድ አንድ እና አንድ ብቻ ነው!!

'‎የጀነት መንገድ አንድ እና አንድ ብቻ ነው!!
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው፡፡
አንተ የተከበርከው ወንድሜ ሆይ እወቅ፤ አንቺም የተከበርሽው እህቴ ሆይ! እወቂ፤ የጀነት መንገድ አንድ ብቻ ነው፡፡ ልክ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው እንደሚባለው የጀነትን መንገዶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች(ጎዳናዎች) አላደረገውም፤ ከረሱል ጀርባ የሳቸውን ሱና ተከትለን ቢሆን እንጂ ጀነትን መግባት አንችልም፡፡
‹‹አብደላህ ኢብኑ መስዑድ(ረዐ) እንዲህ አለ፤  ያአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ቀጥ ያለ መስመርን አሰመሩልን  ከዚያም ((ይህ የአላህ መንገድ ነው፡፡)) አሉ፤ ከዚያም ከቀኝ እና ከግራ ሌሎች መስመሮችን ካሰመሩ ቡሃላ ((እነኚህ ጎዳናዎች ናቸው፤ በእያንዳንዱ ጎዳና ላይ ሸይጣን ወደሷ ይጣራል፡፡)) ከዛም ሱረቱል አንዓም 153ኛውን አያ አነበቡት፡፡
((وَأَنَّ هَذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَنْ سَبِيلِهِ ذَلِكُمْ وَصَّاكُمْ بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ (15)))
‹‹ ይህ ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ ሌሎችን (የጥመት) መንገዶች እንዳትከተሉ (ከቀጥተኛው) መንገድ ይለያችኋልና፤ ይሃችሁ ትጠነቀቁት ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡›› ሀዲሱን ዳሪሚ በሱነናቸው ሀዲስ 202 እና ኢማሙ አህመድ  ሙስነዳቸው ላይ ሀዲስ 4131 የዘገቡት ሲሆን አላመቱል አልባኒ (ረሁ) ሚሽካት በሚባለው ኪታባቸው ሀዲስ (166) ላይ ሀዲሱ ሀሰን ነው ብለዋል፡፡
የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) ለኡማቸው የጀነት መንገድ አንድ እና አንድ ብቻ መሆነዋን ግልፅ ያደረጉ ሲሆን ይህችንም ሳይጠቁሙ አልተዋትም፡፡ አቢ ሑረይራ( ረዐ0 ባወራው ሀዲስ ረሱል (ሰዐወ) ‹‹ ሁሉም ህዝቦቼ ጀነትን ይገባሉ እምቢ ያሉት ሲቀሩ፤›› አሉ፡፡ ሰሃባዎችም ‹‹ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ጀነት መግባትን እንቢ የሚል ማን አለ? ብለው ጠየቁ፤ ረሱልም ‹‹ እኔን የታዘዘኝ ጀነትን ገባ፤ ያመፀኝ በእርግጥም እሱ እምቢ አለ፡፡›› ቡኻሪ ሀዲስ 7280 እና ሙስሊም ሀዲስ 1835 ሀግበውታል፡፡
ከዚህም ባለፈ ከአቢ ሁረይራ በተወራ አስገራሚ በሆነው ሀዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ አሉ፤ ‹‹ እኔ በህልሜ ጂብሪል ከእራስጌ ሚካኤል ከእግርጌ ሆነው አንደኛቸው እንዲህ አለ፤ ምሳሌን አድርግለት አለው፤ አንደኛውም ‹‹ ስማ! ጆሮሀ ትሰማለች፤ ተገንዘብ ልቦናህ ይገነዘባል፤ ያንተ እና የህዝቦችህ ምሳሌ ልክ የሆነን አገር እንደተቆጣጠረ ንጉስ ነው፤ ከዛም ይህ ንጉስ በዛች ሐገር ላይ (ትልቅ) ቤትን ገነባና በውስጧም ድግስን አዘጋጀ፤ ከዚያም መልእከተኞችን ወደ ሕዝቦቿ ላከ፤ ከሕዝቦቿም  ከፊሉ የመልእክተኞችን ግብዣ ተቀበሉ፡ ከፊሉ ምላሽን ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ አላህ እሱ ንጉሱ ነው፤ ሐገሪቷ እስልምና ነች፤ ቤቷም ጀነት ስትሆን፤ አንተ ደግሞ ሙሃመድ ሆይ! (ሰዐወ) መልእክተኛው ነህ፤ ጥሪህን የተቀበለ እስልምና ውስጥ ገባ፤ ወደ እስልምና የገባ ደግሞ ጀነትን ገባ፤ ጀነትን የገባ ደግሞ ውስጧ ካለው (ድግስ) ይመገባል፡፡ ኢማሙል ቡኻሪ ሀዲስ 7281 ኪታቡል ኢዕቲሳም ውስጥ ዘግበውታል፡፡
በመሆኑም ውድ የአላህ ባሪያዎች ሆይ የጀነት መንገድ አንድ ብቻ ነው፡፡ ይህም መንገድ አላህ (ሱወ) ለኛ የመረጠልን መንገድ ሲሆን፤ ይህም ማለት በረሱል (ሰዐወ) ፈለግ ልንብቃቃ እና የሳቸውን ሸሪኣ እና ሱና በመከተል ነው የሚገኘው፡፡ ይህም ትክክለኛ መከተል በዱንያም ሆነ በአኺራ የደስታን ሂይዎት የሚያጎናፅፈን ፈለግ ነው፡፡ 
አብሽር ወንድሜ በዚህ ሰለፎች በተጓዙት ፋና(ድካ) ላይ ከተጓዝክ ስኬታማ ትሆናለህ፡፡ ልብ በል ይህች ጎዳና ሰዎችን ለማስደሰት አንቺም ነይ አንቺም ነይ ሁላችንም አንድ ነን እያልን ቢድዓ እና ሽርክን የማናወግዝበት ሳይሆን የአህለ ሱና ወልጀመዓ ጎዳና ነው፡፡ ላ ሂዝቢያ፣ ወላ ተብሊጊያ፣ ወላ ኢኽዋኒያ፤ ወላ ሱፊያ፤ ወላ ሺኢያ፤ ወላ አህባሺያ፤ ወላ  ቀደሪያ ፤ ወላ ሱሩሪያ፣ ወላ ተክፊሪያ፣ ወላ ቲጃኒያ፣ ወላ ከዋሪጂያ፣ ወላ አሽዓሪያ፣ ወላ ነቅሸበንዲያ፣ ወላ ማቱሪዲያ፣ ወላ ሀሩሪያ፣ ወላ ሙርጂኢያ፣ ወላ ራፊዲያ፣ ወላ ከራሚያ፣ ወላ ሳሊሚያ፣ ወላ ኩላቢያ፣ ወላ. . ወላ. . .ወላ. . . . . . . እኚህ ሁሉ የጥመት ግሩፖች ሲሆኑ አላህ ከእነሱ እንዲጠብቀን እና ያቺን ቀጥተኛዋን ጎዳና እንዲመራን እንማፀነዋለን፡፡
አኢማዎች ምን ይላሉ
አብደላህ ኢብኑ መስዑድ ( ተከተሉ እንጂ ፈጠራን አታምጡ፤ በእርግጥም (ከዲን በኩል) ተበቅታችኋልና፡፡ ዳሪሚ 205 ዘግበውታል አልባኒ ተኽሪጁል ኢልም በሚለው ኪታባቸው ላይ ሰሂህ ብለውታል፡፡
ኢማሙ ሻፊኢይ ( በአላህ አመንኩኝ ከአላህም በመጣው እንደ እሱ ፍላጎት፤ በመልእክተኛውም አመንኩኝ ከእሱ በመጣውም እንደ እሱ ፍላጎት፡፡)
ኢማሙል አውዛኢ እንዲህ ይላሉ ‹‹ የሰለፎችን መንገድ በመከተል ላይ አደራህን፤ ሰዎች ያሉትን ቢሉህ አደራህን የሰዎችን ሎጂክ (አመለካከት) ባማረ አንደበታቸውም ቢያሳምሩልህም እንኳን በእነሱ ከመሸንገል ተቆጠብ፡፡››
ማንም ምንም ቢልህ/ሽ ማንንም እንዳትሰማ/ እንዳትሰሚ፡፡ አላህም በቁርዓኑ አማኞችን ሲያወድስ ‹‹ የወቃሽን ወቀሳ አይፈሩም፡፡›› ነው ያለው፡፡ አላህ ሆይ ከእነሱ አድርገን፡፡‎'

ማንም ምንም ቢልህ/ሽ ማንንም እንዳትሰማ/ እንዳትሰሚ፡፡ አላህም በቁርዓኑ አማኞችን ሲያወድስ ‹‹ የወቃሽን ወቀሳ አይፈሩም፡፡›› ነው ያለው፡፡ አላህ ሆይ ከእነሱ አድርገን፡፡

Post a Comment

0 Comments