Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እስከመቼ ከሡናው ጀርባ!!????

እስከመቼ ከሡናው ጀርባ!!????

አሠላሙ አለይኩም ውድ የኢስላም ወንድም እህቶቼ  ዛሬ እራሴንም ጨምሮ ሁላችንም ራሳችን ልንገመግምበት የሚያግዙን ወሣኝ ወሣኝ ነጥቦችን አንግቤ ነው የተነሣሁት 

በጥያቄ ልጀምረው እሰከ …መቼ ከሡናው ጀርባ???  እስቲ መልስልኝ ወንድሜ እስከመቼ ከሡናው ጀርባ ሆነን እንጓዛለን?? አንቺስ እህቴ   እስከ መቼ ድረስ ከሡናው ተቃራኒ እየሆንሽ ትኖርያለሽ????

ተመልከቱማ ☞" አባትየው እና እናትየው" አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እዚሁ ቅርብ ነኝ እኔን ጠይቁኝ ካልጠየቃችሁኝ እቀጣቹሀለው እያለ በቁርአኑ እየነገራቸው እንዲለምኑት  እያነሣሣቸው እነሡ ግን አንድም ቀን ዞር ብሎ ያላያቸውን ቢጠሩት የማይሠማቸውን ቢለምኑት የማይቀበላቸውን እንኳን ለነሡ አይደለም ለራሡ የማይችለውን ደካማ ሙት የሆነ አካልን መማፀን መርጠው ፣ የመጣላቸው ረግጠው ፣ ቢሄዱ መድረሣቸውን እየማያውቀው ሙት ቀብር አፋፍ ላይ መቆምን መርጠዋል፣ አመት የለፉትን ለቀማ ተኛ ሊገብሩ ወስነዋል ምን ዋጋ አለው "አመድ አፋሽ" ሆነው ቀሩ!!!

እስከ መቼ  ለምኑኝ እያለ የሚጨቀጭቅን አካል ቸል ብሎ የማይሠማውን እንደው ሠማ ቢባል እንኳን ምላሽ የማይሠጠውን  ሙት አካል ሢማፀን የሚኖር?? 

"መሀኗ "እሦ ደግሞ አላህ የነሣትን የመውለድ ችሎታ እጠንቋይ ዘንድ ሔዳ ታገኘው ይመስል ጠንቋዩ ዘንድ በመሄድ የዶሮ እና የበግ  ቀለም ስታማርጥ ትኖራለች  ልጅ የከለከላት አላህኑ ስጠኝ ብሎ ከመማፀን ምን አግዷት ይሆን??  ልጅ የመስጠት ችሎታ በአላህ እጅ መሆኑን ከቶ እንዴት ዘነጋችው 

ተመልከቱማ ☞ "ወጣቷ " የምትለብሠው ቀሚስ ሠፊና ጠንካራ ግን ምንዋጋ አጥሮ እነዛ ውብ ባቷቹዋን በፀሀይ ያጠቁራቸዋል ሌላኛዋ ደግሞ እረጅም ይሆንና ይሣሣል አካሏን በሙሉ  ፍንትው አድርጎ  እስኪያሣይ ድረስ ብቻ በተቻላት መጠን ቁርአኑን ስትጋጭ ትኖራለች  አላህ በግልፅ " አንተ ነብይ ሆይ ለሚስቶችህ እና ለሴት ልጆችህ በላያቸው ላይ ጅልባባቸውን ጣሉ በላቸው  "ሢል አንቺ ግን በተቻለሽ አቅም ተገላልጦ ለመሔድ ጥረት ታደርጊያለሽ   ግን እስከ መቼ??? እስቲ ራስሽን ጠይቂው 

☞ "ወጣቱ " እሡ ደግሞ አሣጥረው የተባለውን ሡሪ  ቬሎ ይመስል ከተረከዙ ስር እየረገጠው ይሔዳል አልያም ያሣጥረውና ያጠረው ለሡና እንዳይመስልበት ይመስል ከየሁዳውያን ለማመሣሠል ያስቀረቅረዋል ።ሡብሀን ሡናው እንዳይመስልበት ከየሁዳውያን ጋር ግን…  

አንተስ እስከ መቼ ሡናቸውን እየተቃረንክ ትኖራለህ???

"ሁለቱ ወጣቶች " በቀጥተኛው መንገድ ተጋብቶ ቤተሠብ መስርቶ ከብሮ መኖርን ኢስላም እየሠበከ እያነሣሣ ባለበት  በጀርባ በኩል በአቋራጭ የከለከለውን አልፎም ከከባባድ ወንጀሎች የፈረጀው ዝሙት ያምራቸውል 

ግን ለምን ሡናውን  ለምን ይቃረኑታል???

☞ ከላይ በተጠቀሡም የተወሠኑ ሡናውን የሚጋጩ ፀያፍ ተግባራቶች  ባልተጠቀሡ በርካታ የሆኑ ከሡናው ተቃራኒ የሆኑ  ነገሮች መመከርን ከራሤ ጀምሮ የሚመለከተን ሁሉ አደራ እላለው  

☞ አላህ መጥፎውን ሽርኩን ቢድአውን  የምንጠላ ሀቅ ሀቁን ሡና ሡናውን ተውሒዱን  የምንወድ ያድርገን አሚን