Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስልካችን‬

'‎#ስልካችን

- የ21ኛው ክፍለ ዘመን ለወጣቶች ከባድ ስራ ... ስልካቸውን ሳይነኩ ለሰላሳ ደቂቃ መቆየት ሆኗል ። 
- ከሞላ ጎደል አብዛኛው ወጣት የስልክ ሱስ ሰለባ ሆኗል ። 
- ወደ እንቅልፍ ከመሄድህ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የምትነካው እሱን (ስልክህን) ሆኗል ።
- ከእንቅልፍህ ስትነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ የምትነካው እሱን ሆኗል ። 
- አንዳንዶች እንደውም ስልካቸውን እየነካኩ ወይንም ጆሮ ማዳመጫ ጆሯቸው ላይ ስክተው በዛው ወደ እንቅልፍ የሚያሸልቡም አሉ ።
- አንዳንዶች ሌሊት ከእንቅልፋቸው ዳውንሎድ ለማድረግ ይነሳሉ ነገር ግን ለተሃጁድ ተነስተው አያውቁም ።
- አንዳንዶች ሁሌም ኦንላይን ቻት ላይ ናቸው ። 
- ማታ ሁለት ሰዐት ኦንላይን ናቸው ።
- እኩለ ሌሊትም ድረስ ላይ ኦንላይን ናቸው ።
- በሺዎች የሚቆጠሩ የማሕበራዊ ድሕረ ገፅ ጓደኞች አሏቸው ። ከነሱም ጋር ያወራሉ ። ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግን ቃልም አይተነፍሱም ። ክፍላቸውን ዘግተው ስልካቸውን ይዘው ቁጭ !
- አንዳንዶች ስለ ዲናቸው “ትግል” እስክ እኩለ ሌሊት ድረስ ይከራከራሉ ሱብሒ ሰዐት ላይ ግን ተኝተው ያንኮራፋሉ ።
- ልክ ሰላት ተጠናቆ ተስሊም እንደተባለ ሰዎች ስልካቸውን አውጥተው አሁንም ሲነካኩ ተመለከታለህ ። ለአዝካር ሰዐት የለም ። ልክ.. “መጪውና ያለፈው ወንጀል ተምሮላቿል” የተባሉ ይመስል ። 
- ልክ አንድ አደጋ ሲደርስ አንዳንዶች የሰውን ነፍስ ለማትረፍ ከመቻኮል ፋንታ ስልካቸውን አውጥተው ተጎጂውን አካል ፎቶ “ቀጭ!” “ቀጭ!” ሲያደርጉት ተመለከታለህ ። 
- አንዳንዴማ ቤት ሲቃጥል እያዩ በጉንጫቸው እንኳን ውሃ ይዘው መጥተው ለማጥፋት ከመረባረብ ፋንታ ፎቶ አንስተው ማሕበራዊ ድሕረ ገፅ ላይ የመጀመሪያው ለጣፊ ለመሆን ሲሯሯጡ ትመለከታለህ ። ለምን? አድናቆት ፍለጋ ።
- አረረ! እንደውም አንዳንዶች ሰው ሲሞትባቸው ሁሉ ማፅናኛ ኮሜንት ለማግኘት ይሁን ለምን ባላውቅም ስለቀብሩ ከማሰብ ይልቅ “እከሌ ሞተብኝ” ብለው ለመለጥፍ ሲቻኮሉ ታያለው ። አጂብ!
- በስልክ ሱስ በጣም ከመጠመዳችን የተነሳ አንዳንዶች ትራንስፖርት ውስጥ ተጣበን ቁጭ ብለን ሁላ ቻት እናደርጋለን ። አንዳንዱማ ፈተና ክፍል ውስጥም ቻት ያደርጋል ። 
- አንዳንዶች መስጂድ ውስጥ ፌስቡክና ዋትሳፕ ይጠቀማል ። ጌምም የሚጫወት አለ ። ሱብሃነላህ !
- አንዳንዶች መስጂድ ውስጥ ድራማ ነሺዳና ፊልም በስልካቸው ያያሉ ። 
ምን አይነት ፊትና ነው ዑማው ላይ የመጣው ?
- አንዳንዱማ መንገድ ላይ እየሄደ ስልኩን እየነካካ ተመስጦ ሳለ የሚባንነው ስልክ እንጨት ጋር ሲጋጭ ወይንም ሙዝ ልጣጭ አዳልጦት “ጢብ” ሲል ነው ።
- ቤታችን እንግዳ መጥቶም እንግዳውን ረስተን ሃሳባችን ስልካችን ላይ ነው ። አረረ ፊት ለፊትህ እንግዳ አለ ጎበዝ!! ሆሆ!!
- በስልክህ ምክንያት ለጁምዐ ሰላት መጨረሻ የምትመጣው አንተው ሆነሃል ። በስልክህም ምክንያት ሰላት ሲያልቅ መጀመሪያ የምትወጣውም አንተው ሆነሃል ። 
- አንዳንድ ባለትዳሮች የትዳር አጋራቸውን ፎርግተው ስልካቸው ላይ ከ ‹ቤስት› ጓደኞቻቸው ጋር ያወራሉ ።
- አንዳንዶችማ ሰላታቸውን ቶሎ አሳጥረው ሰግደው ወደ ስልካቸው ለመመለስ ሱረቱል አስርን ይቀራሉ ። ሱረቱል አስር ሰዐትን በመልካም ስራ ማሳለፍን እንደሚያሳስብ ዘንግተዋል ።
- አንዳንዱ ጁምዐ ጁምዐ ስልኩን ቻርጅ ላይ ጢም አድርጎ ይሞላል ። ለምን ? ሱረቱል ካህፍን ሊቀራበት ? በጭራሽ ! ዘመድ ጥየቃ ሊደውልበት ? በጭራሽ! እናስ? ‹ተቃውሞ› ሰልፍ ቪዲዮ ሊቀርፅበት! ከዚያስ ? አሜሪካና አውሮፓ ላሉት “ታጋዮች” ሊልክላቸው ። ቀድሞውኑ.. “ስልክህን ሳትይዝ እንዳትወጣ!” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ አለበታ ። 
- ብዙዎች ስልካቸው ‹ሙናፊቅ› ለመሆን ሰበብ የሆናቸው ሲኖሩ ብዙዎችንም ወደ ጀሃነም እሳት ለመምራት ሰበብ ይሆናቸዋል ። አላህ ከነርሱ አያድርገን ። 

اقْتَرَ‌بَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمْ وَهُمْ فِي غَفْلَةٍ مُّعْرِ‌ضُونَ
ለሰዎች እነሱ በመዘናጋት ውስጥ (መሰናዳትን) የተው ኾነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ 
[አንቢያ-1]‎'
‪#‎ስልካችን‬

[አንቢያ-1]