ፊዳ ልሁንልሁ ! !
አላህ ሳይለው ቀርቶ ያኔ ባልታደል
በኡሑድ ተራራ በመዲና ገደል
ካንቱ ጋር ሰግጄ ካንቱ ባልታገል
እጅሁን ጨብጬ ካንቱ ቃል ባላስር
እንዲያ እንደታደሉት በዚያች በዛፏ ስር
በክብር ሰፍረዋል ልቤ ላይ ኖት ዛሬ
ይዤኋለሁና በውስጤ ቀብሬ
አለም ያለ ዘመድ ቅርብ ሩቅ ቤተሰብ
ሚስት እናት ተብሎ ልጅም በሰበሰብ
ደግሞ በዚሁ ላይ ብጨምራት ራሴን
ሳልሳሳላት ነፍሴን
በለጥኩብኝ አንቱ ሌላው ታየኝ ደቆ
ፊዳ ይሁንሉህ ነፍሴ ከወላጅ ጋር
ታጥፎና ተጨምቆ
በሙሓመድ ሲራጅ
አላህ ሳይለው ቀርቶ ያኔ ባልታደል
በኡሑድ ተራራ በመዲና ገደል
ካንቱ ጋር ሰግጄ ካንቱ ባልታገል
እጅሁን ጨብጬ ካንቱ ቃል ባላስር
እንዲያ እንደታደሉት በዚያች በዛፏ ስር
በክብር ሰፍረዋል ልቤ ላይ ኖት ዛሬ
ይዤኋለሁና በውስጤ ቀብሬ
አለም ያለ ዘመድ ቅርብ ሩቅ ቤተሰብ
ሚስት እናት ተብሎ ልጅም በሰበሰብ
ደግሞ በዚሁ ላይ ብጨምራት ራሴን
ሳልሳሳላት ነፍሴን
በለጥኩብኝ አንቱ ሌላው ታየኝ ደቆ
ፊዳ ይሁንሉህ ነፍሴ ከወላጅ ጋር
ታጥፎና ተጨምቆ
በሙሓመድ ሲራጅ