Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

Beware of this jewish sites:ፀረ ኢስላም ዌብሳይቶችን ተጠንቀቁ

‎www.....com
Beware of this jewish sites:

አሰላሙአለይኩም

 ፀረ ኢስላም ዌብሳይቶችን ተጠንቀቁ፣ መልእክተኛውን የሚሳደቡ  ዌብሳይቶችን ተጠንቀቁ...ወዘተ

 እየተባሉ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎችን የሚያሰራጩት ባብዛኛው ባለ ዌብሳይቶቹ  ናቸው። ለጉግል እና መሰል ድርጅቶች ለማስታወቂያ ከሚያወጡት ወጪ ይላቀቃሉ። 
አላህና መልእክተኛው ላይ ዘለፋዎችን እንዲሁም ቅጥፈቶችን በነፃ ማሰራጨት ይችላሉ። 

እስቲ ቆም ብለን እናስበው፤
ኢስላምን የሚሳደብ አንድ መፅሄት ቢወጣ ያንን መፅሄት እንዳይሰራጭ እንፈልጋለን ወይስ በብዛት ገዝተን ተጠንቀቁት እያልን እንበትናለን??

በግል ህይወታችን ከሰዎች ጋር ባለን አለመግባባት ስለኛ መጥፎ ፕሮፓጋንዳ ቢነዙ እናሰራጨው ነበርን?

አሁን አሁንማ መልእክተኛውን የሚሳደቡ ስእሎችን እያሰራጩ "ተመልከቱ ሲያሾፉብን" የሚሉ ቀልደኞች በዝተዋል።

እያንዳነዱን መልእክት ስናስተላልፍ ከበስተጀርባው ላለው ቅናቻ ወይም ጥመት ሰበብ አስተዋፅኦ እያበረከትን መሆኑን እናስተውል። 

መልካም ስራዎች አናሳ በሆኑበት ዘመን፤ ከሞትን በኃላ የመልካም ስራ ምንዳችን እንዳይቋረጥ የሚያደርጉ ቀጣይ ስራዎችን ትተን ለማለፍ መጣር አለብን። ይህ ተግባር ግን በቋሚነት ወንጀል እንዲፃፍብን የሚያደርግ ጥፋት ነው።  አላህ ማስተዋልን ይለግሰን!!

√ እራስን ማጥራት ግዴታ ነው!

በሳንባ በሽተኞች መካከል፤ በተበከለ አየር ውስጥ ካለመከላከያ የሚኖር ሰው ስለጤንነቴ እጨነቃለው ቢለን አትቀልድ እንለዋለን።   

ለፀረ ኢስላም አቡጃህሎች ጆሮውን ያዋሰ ሁሉ ሊነቃ ይገባዋል። ግሩፓቻቸውን ያሞቁ ፔጆቻቸውን በላይክ ያደመቁ ሁሉ ሊያስቡበት ይገባል።  ለአላህና ለመልእክተኛው ያላቸውን ክብር፤ ለኢስላም ያላቸውን ቁርጠኛ እምነት ካስተዋሉ ከከሀዲያን ጋር ለመቀመጥ ትእግስቱ አይኖራቸውም። አራስን ማፅዳትም ተቀዳሚ ተግባራቸው ይሆናል።

( وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آَيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّى يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ ) النساء/140 .

«በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ፤ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም ሲላገጥባት በሰማችሁ ጊዜ፣ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከነርሱ ጋር አትቀመጡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፤ እናንተ ያን ጊዜ ቢጤያቸው ናችሁና፤ አላህ መናፍቃንን እና ከሐዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና» ኒሳእ 140

ኢስላምን ከምንጩ መማር፤ ልብን ንፁህ በማድረግ፤ እራስን በእውቀት በማበልፀግና በአላህ በመታገዝ ማንኛውንም አይነት መደናገርና የቀልብ በሽታ መከላከል ይቻላል። 

የአላህን ውዴታና ፍቅር ከፈለግን ኢስላማዊ እውቀትን ከትክክለኛ ምንጮች እናጣጥም።  
ባወቅን ቁጥር ብርሀን እንደሆነና ጨለማን እንደሚገላልጥ እንረዳለን።  

አዎ! ኢስላምን ከምንጩ እንረዳው፤ ያን ግዜ  ለሚነሱ ሹቡሀቶች ሁሉ የኢስላም ሊቃውንት ምን ያክል የማያዳግሙ ምላሾችን እንደሰጡ በዝርዝር ማወቅ  እንችላለን። እነዚህ ግሳንግስ ማወናበጃዎች ሁሉ በቁርአናዊ አስተምህሮ እንደሸረሪት ድር ሲበጣጠሱ እናስተውላለን።

ኢስላምን ስንኖረው ጉዞአችን መሰናክሎች የተደረደሩበት ነው። ስሜታችንን ተከትለን ለዱንያ እጅ ሰጥተን ከመስመር እንድንወጣ፤ አለያም ውዥንብሮችን በመስማት መደናገር ውስጥ እንድንገባ ሌት ተቀን የሚለፉ የሸይጣን ወታደሮች ብዙ ናቸው። ከኛ የሚጠበቀው፤ ጥሩ የጉዞ ጓደኞችን መቅረብና ጉዞአችንን የሚያሰናክሉ ሽፍቶችን መራቅ ነው።  

አላማ ያለው ሰው ለስኬት የሚያበቁትን እርምጃዎች መሳት የለበትም፤ መርከብ በየብስ አይጓዝምና!! 

Abujunaid 
 
www....com‎
www.....com

www....com