Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አጅር መዝጋቢው facebook ሆነ እነዴ ያጀምአ??

አጅር መዝጋቢው facebook ሆነ እነዴ ያጀምአ??
By Berekah Ayemen
አል ቢጣቃ እና ሌሎች የ ኢስላም ድረ ገፆች ጉድ አፈሉ እኮ ጎበዝ ነገሩ ገርሞ ገርሞ የሚገርም ነው መቼም ፌስቡክ ጥቅም እንዳለው ሁሉ ጉዳቱም በዛው ልክ ነው ምን አረገ ደግሞ ብትሉ እሱ ምንም አላረገም እኛ ነን እንጂ እንዲያረገን የፈቀድንለት አብዘሃኞቻችን መቼም የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶችን የሚሰጡ ነገሮችን በ Facebook መስኮት Share እና Post በማድረግ እንታወቃለን አላህ ኢኽላስ አያሳጣን እና ነገር ግን ዋናው ጥያቄ የሚሆነው Share እና Post የምናደርጋቸውን ነገሮች ምን ያክል እንስራባቸዋለን መልሱን ለእናንተ ልተው......... ሆኖም እንደሚመስለኝ ብዞዎቻችን ኢባዳዎቻችንን በ Facebook ላይ አስቀርተነዋል ወደ ራሳችን አላመጣነውም ያመጣነውም አንጠፋም ኸይር ነው ስራችንን Facebook ላይ ብቻ ከማስመዝገብ ድነናል ማለት ነው:: ሌሎቻችን ደግሞ ሰላተል ለይል በመስገድ ፋንታ ለሊት ተነስቶ ስለ ለሊት ሰላት Post እናደርጋለን ነገር ግን አንሰግድም ምክንያቱም ኢባዳውን የሰራው ይመስለናል አረ ስነቱ የ Facebook ኢባዳ መች ተቆጥሮ ያልቃል Facebook ይፍጀው ከማለት ወጭ ምን ይባላል ብዙዎቻችን ሳናውቀው በ Facebook ኢባዳ ከ አቁዋማችን ወርደናል በ ኢባዳችን ተዘናግተናል ሆዳችን ያውቀዋል ኢባዳችንን በ Share እና በ post ብቻ አድርገናል ከመች ወዲህ ነው ደግሞ Facebook አጅር መዝጋቢ የሆነው ይገርማል እኮ ሳናውቀው ለ Facebook ትልቅ ክብር አጎናፀፍነው አጅር መዝጋቢ አደረግነው አርፍ አሁንም ቢሆን እስላማዊ ትምህርት የሚሰጡ ነገሮችን አናውጣ ማለቴ አይደለም ነገር ግን Share እና Post የምናደርጋቸውን ነገሮች ወደ አራሳችን ሂወት እናምጣቸው በ አላህ ፍቃድ ለውጥ እናመጣ ዘንድ ነገር ግን አሻፈረኝ ብለን ኢባዳችንን ለ Facebook የምንሰጥ ሰዎች የአቁዋም መውረድ ሊያጋጥመን ስለሚችል ከወዲሁ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ እንደሚታወቀው የዱንያ ሂወት አጭር እና በብዙ ብልጭልጭ ነገሮች የተሞላች ናት:: ታድያ ብልጥ ሰው ማለት በእነዚህ ብልጭልጭ ነገሮች ሳይታለል ለ አኼራው ጥሩ ጥሩውን የሚሰንቅ ሰው ምክንያቱም ጀነትን ስለሚናፍቅ ማለት ነው :: የሞኞች ሞኝ ሰው ማለት ደግሞ በዱንያ ብልጭልጭ ነገሮች ተታሎ ስንቁን አሳንሶ መመለሻውን ጀሃነም እንዲሆን የፈቀደ ሰው አላህ ይጠብቀን እና መቼም ሞት ሲመጣ አያማክርም ስለዚህ ሞት በእኛ ላይ ከመምጣቱ ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ እያልኩ ፅሁፌን በዚሁ እጨርሳለሁ ፡፡ አላህ ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን ለስራዎቻችንም ኢኽላስ ይስጠን!!!

Post a Comment

0 Comments