Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

«ኢስላማዊ» ቻናሎች ፤ «የሙስሊሙ» ልሳን ነን ብለው የሚሞግቱ ራዲዮዎች ፤ የኢትዮ «ሙስሊምን» ድምፅ እናሰማለን የሚሉ ፔጆች ምነው

«ኢስላማዊ» ቻናሎች ፤ «የሙስሊሙ» ልሳን ነን ብለው የሚሞግቱ ራዲዮዎች ፤ የኢትዮ «ሙስሊምን» ድምፅ እናሰማለን የሚሉ ፔጆች ምነው ስለዚህ ዘመን አመጣሽ የመውሊድ «በዓል» አደገኝነት ለማስተማር አንደበታቸው ተለጎመ?
እነዚህ ለፍትህ ቆመናል ብለው ቀን ከሌት የጨቋኝ ባለስልጣናትን ስም የሚያስሸመድዱን ፤ ዙልምን (በደልን) ከሙስሊሙ ቀንበር ላይ እናስወግዳለን ብለው የሚደሰኩሩት «የኛዎቹ» ፍትህ ናፋቂዎች ምነው ታዲያ መውሊድን ዘነጉት?
መውሊድ በውስጡ እጅግ በጣም ብዙ ሽርክ እና አፀያፊ በዲን ላይ የመጡ ፈጠራዎች መናሀሪያ መሆኑን ማንም የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ታዲያ ሽርክን የሚያክል በደል ቢድዐን የሚያክል ግፍ መቃወም ሲገባቸው ምነው ዝምታቸው በረታ?
ሽርክ ማለት እጅጉን የከፋ የበደሎች ሁሉ በደል መሆኑን አላህ እንዲህ ሲል በታላቁ ቁርአን ይነግረናል: –
«ልጄ ሆይ! በአላህ ላይ አታጋራ ። ማጋራት (ሽርክ) ታላቅ በደል ነውና ።» [ሉቅማን]
ታዲያ ታላቁ በደል ሽርክ ከሆነ በደልና ግፍን እንቃወማለን ከሚል ወገን ይህን ታላቅ በደል ለማድወገድ ዝምታን ሲመርጥ ምንን ነው የሚያስይዘው?
ታዲያ ተውሒድ የፍትሖች ሁሉ ፍትሕ ከሆነ ፍትሕን እናሰፍናለን የሚል ወገን ዝምታን ሲመርጥ ምንን ነው የሚያስጨብጠን?