Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በአላህ ይሁንብኝ አልቅስ አልቅስ ያሰኛል! የሰፈር ልጆች አቅራቢያ ባለው ...

በአላህ ይሁንብኝ አልቅስ አልቅስ ያሰኛል!
የሰፈር ልጆች አቅራቢያ ባለው መስጂድ ተሰባስበው ድቤ እየደለቁ የሽርክ ቃላትን ሲያነበንቡ የሚመለከት አይን እንዴት ያስችለዋል ?
በነገራችን ላይ ይህ የሰፈር ልጆችን በቀበሌ በቀበሌ እየከፋፈሉ በቡድን በቡድን አዋቅሮ ድቤ እየሰጡ የሽርክ መንዙማ ግጥምን እያስሸመደዱ በየመሳጂዱ እየሄዱ እንዲጨፍሩ የማድረግ እና ከዒልም ርቀው በሽርክ ተጨማልቀው አኺራቸውን እንዲያጡ ከፍተኛ ፕሮጀክት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለው የአሕባሹ መጅሊስ ቢሮ መሆኑን ያላወቃቹ እወቁ!
በመቀጠልም እስካሁን ባለኝ መረጃ መሠረት የአሕባሹን መጅሊስ እቅድ በማስፈፀም የአንበሳውን ድርሻ ይዞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው መቀመጫውን ኳስ ሜዳ (አ|አበባ) ያደረገውና በክልል ከተሞችም ከሌላው ጊዜ በላይ እየተንቀሳቀሰና እየተስፋፋ የሚገኘው የጀምዐቱ ተብሊጝ («ዳዕዋ» ጀምዐ) ነው። እንዴት? በሉኝ!
ጀምዐቱ ተብሊጞች በአሁን ሰዐት በየሰፈሩ የሚገኙ የዒልምን ብርሐን በጨረፍታም ያላዩ ታዳጊ ልጆችን እስከ አዛውንቶች እርከን በሚኖሩበት አካባቢ ባለ በነሱ ቁጥጥር ስር የሆነ መስጂድ ውስጥ በ«ዳዕዋ» ኹሩጅ መውጣት ሰበብ አሰባስበው ወደ መውሊድን በ«ዚክር» ማክበር ስብስብ ይቀይሩታል ። ይህ ዕቅድ በተጠንቀቅ የተጠናና ከበላይ አካላት ድጋፍን የተቸረው መሆኑን ማንም የቀረባቸው ሰው የሚያሸተው ነው። በቅርቡ በየትራንስፓርት ላይና በየፌስቡኩ የምንመለከተው የካፊሩ ሳይቀር መዘባበቻ ያደረገን «ኢስላማዊ» ዲጄ አስነዋሪ ቡድንም የዚህ ስራ ውጤት ነው ። ቀስ በቀስ እየተሰራጨ የመጣው ይሀው የሰፈር ቡድድን እየሰፋ መጥቶ አሁን ላይ ጭራሽ የእንትን ሰፈር የ«ዳዕዋ»ና የመንዙማ ቡድን የእንትን ሰፈር የ«ዳዕዋ»ና የመንዙማ ቡድን ጋር ጠብ አላቸው ተብሎ መወራት ከጀመረ ሰነባብቷል ። ይህ የሆነው በምን ይመስላቿል? ጥናት ለማድረግ እንደሞከርኩት አንዳንድ የሰፈር መንዙማ ባይ ቡድኖች በሰርግ ማጀቢያነት ዝናቸው ከፍ ያለ መሆኑ ሲሰማ የሌላ ሰፈር የድቤ ጀምዐዎችም ይህን የጦፈ ቢዝነስ መቀላቀላቸውና እርስ በርስ በዚህ የሰርግ አጃቢነት ቢዝነስ አማኻኝነት ቁርሾ መፈጠሩ ነው ።
አላህ እንዲህ ይላል :–{ ﺗَﺤْﺴَﺒُﻬُﻢْ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﻗُﻠُﻮﺑُﻬُﻢْ ﺷَﺘَّﻰ }
[ የተሰባሰቡ (አንድነት ያላቸው) ናቸው ብለህ ታስባለህን? ቀልቦቻቸው የተበታተኑ ናቸው] (አልሐሸር: 14)

እናም በሁለተኛ ደረጃ የሙስሊሙ ዑማ በመውሊድ ሰበብ እዚህ አዘቅጥ ውስጥ የመውደቅ ሰበብ ኢኽዋኖች ናቸው። የነዚህ ደግሞ የሚገርማቹ ልክ እንደነዛ አይን ባወጣ «ዚክር» ሰበብ ባይሆንም አልሸሹም ዞር አሉ እንደሚባለው ይሄን ቀን እና ቀናት ታላቁ ነቢይ የተወለዱበት ስለሆነ እሳቸውን በማስታወስ ስል አኽላቃቸው ኑቡዋቸው ገድላቸው እያስታወስን እናሳልፈው የሚል ፈሊጥ ነው። አሁን ግን ከሱም እያለፈ ነወደ ። ልክ እንደነዛኞቹ እነዚህም በነሺዳ በድራማና በመሳሰሉት ቀኑን እናሳልፈው የሚል ማስቀየሻ መንገድ ነው ። ሕዝቡን ቢያታሉ አላህን ያታልላሉን?
ነገ የካፊሮቹ አንድ ሲኒማ የሚዘጋጀውም ዝግጅት የዚሁ የኢኽዋንኛ የላብራቶሪ ውጤት ነው ። አንድ ወዳጄም እንደነገረን በዚህ ቀንም (ዛሬም) ቢሆን አለቃቸው ሐሰን ታጁ ከና ከረፋዱ ከዚህ ቀደም «ሙዚቃ ሃላል ነው» ባለበት ኤፍ ኤም ራዲዮ ስለመውሊድ ሊናገር ተሰይሟል ። አስቡት እሱን ዐሊም አድርገው የያዙ ስንቶቹ ሙስሊሚች ይህ ተርጓሚ ራዲዮ ላይ ቀርቦ ስለመውሊድ ማውራቱን መውሊድ ለመቻሉ ማረጋገጫ ያደርጉት ይሁን? እነዚህ ቡድኖች ከላይ ከጠቀስናቸው የመንዙማ ቡድኖች ጋር ከላይ ሲታዩ ልዩነት ያላቸው ቢመስሉም አላማቸው ግን አንድ መሆኑን በጥልቀት ያያቸው መረዳት የሚችለው ነው ። ልዩነታቸው እነዚህ Modern (ስልጡን) ነን ሲሉ እነዚያ ደግሞ የቀደምት ሸኾቻችን ጦሪቃ (መንገድ) ተከታይ ነን ባዮች ናቸው ። ካነሳሁት አይቀር ሰሞኑን መነጋገሪያና አስደንጋጭ የነበረው የ«ኢስላማዊ» ዲጄ ጉዳይ አሳሳቢነቱ እኔንም አሳስቦኝ እነዚህ የመንዙማ «ኢስላማዊ» ዲጄ ቡድኖች ማስታወቂያ ፔጅ ላይ ገብቼ ስቃርም ያየሁት ከላይ የነገርኳቹን ነው ። ይህም በተለያዩ መድረኮች ለሶሓባ ተሳዳቢው ሰይድ ቁጥብና ለሐሰን ታጁ ሸይኽ ቀረዳዊ ሽንጡን ገትሮ የሚሞግተው ከሱም አልፎ በነሱና በአሕባሽ መካከል የፓለቲካ አጀንሰዳ እንጂ ልዩነት እንደሌላቸው አስረግጦ የሚናገረው ዶ/ር ሰመሐር ተክሌ (ነሲም) እና ጓደኞቹ ከ«ኢስላማዊ» የመንዙማ ቡድን ሃላፊ ጋር በፍቅር የተነሱትን ፎቶግራፍ ማየቱ አንድነታቸውን ፓለቲካዊ አጀንዳም ይለያየዋል ማለትም የሚከብድ ነው። አዎን አንድ ናቸው! መልክና ይዘታቸው ይቀያየር እንጂ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሽርክና ቢድዐ ነው የሚጣሩት!
እናም ወንሞቼና እሕቶቼ በመጀመሪያ ደረጃ የሽረክና የቢድዐና አስከፊነት እራሳችን እንረዳው ከዚያም ቤተሰቦቻችንን እናስጠንቅቅ! ከቤታችን አንድ አባል «ዳዕዋ» እወጣለው በሚል ሰበብ ከነዚህ አላህ ከሚጠላቸው ቡድኖች ጋር ሲቀላቀል ዝም ካልን ነገ አላህ ፊት ለሚጠብቀን ጥያቄ መልስ እናዘጋጅ ! አሊያም ኢስላምን ለኛ ያስተላለፉልን ሰለፎች እና የነሱን ጎዳና የተከተሉት ዑለማዎችን ትቶ የሌሎቹን ኢኽዋንኛ እስትንፋስ የሚተነፍሱ መፅሃፍትን የሚያነብ የቤተሰባችንን አባል "ተው!" ካላልን አሁንም ለአላህ መልስ እናዘጋጅ ።
አላህ ቅኑን መንገድ ይምራን

Post a Comment

0 Comments