Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሱና ለምን አስፈለገ?

ለምን አስፈለገ?
አላህና መልዕክተኛውን መውደድ የሚገለፀው የነብዩን ፈለግ (ሱንና) በመውደድ እና በመከተል ትዕዛዛቸውን በመተግበር ከከለከሉት በመራቅ ነው የነብዩ ወዳጅ  ሁልጊዜ ለእሳቸው ታዛዥ ነው አያምጽም መመሪያን አይጥስም ያልታዘዘውን አይሰራም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ሀጢያቶቻችሁን ለእናንተ ይምራልና አላህም መሀሪ አዛኝ ነው በላቸው አል ኢምራን 31
ነብዩን የተከተለ ሰው የሰሩትን ይሰራል የተዉትንም ይተዋል አል ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ረሱል እንዲህ ይላሉ
የእርሱን ፈለግ የሚይዙና ትዕዛዙን የሚከተሉ ረዳቶች እና ጓደኞች ከህዝቦቹ አድርጎለት እንጂ አላህ ነብይን አልላከም ከዚያም ከእነሱ በኋላ የማይሰሩትን የሚናገሩ ያልታዘዙትን የሚሰሩ ይተካሉ፡፡ (እነኚህን) በእጁ የታገላቸው መዕሚን ነው ከዚህ በኋላ የሰናፍጭ ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን የለም
በሱና ላይ ለመጠናከር አዳዲስና መጤ ከሆኑ አመለካከቶችና አምልኮዎች እራስን ማላቀቅ ስፈልጋል
በዲን ውስጥ አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ቢድዓ ነው ቢድዓ ደግሞ የተወገዘ ነው
መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው፡፡ ቡሃሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ በሌላ ተመሳሳይ ሀዲስ ትዕዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው ሙስሊም ከዓኢሻ ዘግበውታል፡፡ ኢስላም የተሟላ በመሆኑ ምንም ዓይነት ጭማሪንአይቀበልም፡፡ የተላለፈልንን ሱና ብቻ ብንተገብር ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ ታላቁ ለሀቢይ ኢብን መስዑድ እንዲህ ብለዋል ተከተሉ ቢድዓንም አትፍጠሩ ሱና በቂያችሁ ነውና፡፡ ሁዘይፋ ኢብኑል የማን ደግሞ እንዲህ ይላሉ የመልዕክተኛው ሰሃቦች ባልሰሩት ማንኛውም የዒባዳ ተግባር አምልኮን አትፈጽሙ የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ምንም የተዉት ነገር የለም አቡ ዳውድና ሌሎች ዘግበውታል፡፡ 
ታዲያ እስልምናችን ሙሉ ሆኖ ሳለ ለምን አዲስ ተጨማሪ አስፈለገ?

Post a Comment

0 Comments