ለሸህ ኡሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) ጥያቄ ቀረበላቸው
ጥያቄ፡- ነብዩን(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ማሞገስን በንግድነት መጠቀም እንዴት ይታያል?
መልስ፡- ይህ ሐራም ነው፡፡ የነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙገሳ በሁለት እንደሚከፈል መታወቅ አለበት፡-
አንደኛው፡- ሳያጋንኑና ከልክ ሳያልፉ በሚገባቸው ነገር ማሞገስ ነው፡፡ ይህ ችግር የለውም፡፡ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከስነምግባራቸው በሚገባቸው ነገር ቢሞገሱ ችግር የለውም፡፡

ሁለተኛው፡- ከልክ ያለፈ ሙገሳ ነው፡፡ ይህን ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ በማለት ከልክለዋል፡፡
“ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ እንዳላቁት አታልቁኝ እኔ ባሪያ ነኝ የአላህ ባሪያና መልእክተኛው በሉኝ” ብለዋል፡፡
ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እርዳታ የጠየቃቸውን የሚረዱ (የሚደርሱለት) ናቸው፡፡ የተቸገረን ሰው ዱዓ ይቀበላሉ የአዱንያና የአኺራ ተቆጣጣሪ ናቸው፡፡ ገይብን ያውቃሉ እና የመሳሰሉትን በማለት ነቢዩን ማሞገስ ሐራም ነው፡፡ ከኢስላም ወደ ሚያስወጣው ሽርኩል አክበር ደረጃም ሊደርስ ይችላል፡፡
ነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከልክ አሳልፎ ማሞገስ አይቻልም፡፡ ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከልክለውታልና፡፡
ወደ ጥያቄው ጭብጥ እንመለስና የሚፈቀደውንም ሙገሳ ቢሆን በንግድነት መጠቀም ሐራም ነው፡፡
ምክንያቱም ነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከስነ ምግባራቸው ምስጉን ከሆነ ባህሪያቸውና ቅኑን መንገድ ከመምራታቸው በሚገባቸው ነገር እሳቸውን ማሞገስ ኢባዳ ነው፡፡
ዒባዳ ደግሞ ወደ አላህ የሚቃረቡበት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ ለዓለማዊ ጥቅም መፈለጊያ መዋል የለበትም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡፡
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْحَيَوٰةَ ٱلدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَٰلَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِى ٱلْءَاخِرَةِ إِلَّا ٱلنَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا۟ فِيهَا وَبَٰطِلٌ مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
“ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑን ሰዎች ስራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው የሰሩትም ስራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሰሩት የነበሩትም በጎ ስራ ብልሹ ነው፡፡” (ሁድ 11፡15-16)
ትክክለኛውን መንገድ የሚመራ አላህ ብቻ ነው፡፡