Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ከአጭር ማብራሪያ ጋር ክፍል 6

የኪታቡ ፀሀ እንዲህፊ እንዲህ አሉ ፦

★ የሠው ልጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ሦስት መሠረታዊ ነገሮች ምንድናቸው በተባልክ ግዜ

★ ባርያ ጌታውን ፣ ሀይማኖቱን እና ነብዪን ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ማወቅ ነው በል!

★ ጌታህ ማነው? በተባልክ ግዜ

★ ጌታዬ አላህ ነው ያ! በፀጋው እኔን እና የአለምን ህዝብ የተንከባከበ

መረጃ አላህ እንዲህ ይላል
«« ለአለማቱ ጌታ ምስጋና ይገባው» » አል ፋቲሀ.

★ ከአላህ ውጪ ያለው በአጠቃላይ አለም ይባላል

★ እኔም ከዚህ አለም ከሚባለው ነገር አንዱ ነኝ

አጭር ማብራሪያ
―――――――__
★ እነዚህ ሦስት ወሣኝ ጥያቄዎች የሠው ልጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ (ግዴታ የሚሆኑ )ነገራቶች ናቸው ምክንያቱም አንድ ሠው እቀብሩ ስር ሲገባ እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች ከመጠየቅ አያመልጥም

★ አንድ ሠው ሞቶ ቀባራዎቹ ከእሡ እንደራቁ ሁለት መላይካዎች ወደ ሟቹ ይመጡና ይቀመጣሉ በመቀጠል ጌታህ ፣ ሀይማኖትህ ፣ ነብይህ ማነው በማለት ይጠይቁታል

★አላህ ፣ ዲኑን ፣ መልእክተኛውን ዱንያ ላይ የሚያውቅ ሙእሚን ከሆነ ጌታዬ አላህ፣ሀይማኖቴ ኢስላም ፣ ነብዬ ብሎ የነበረበት ነብዩን ይናገራል (የሙሣ ህዝብ ከሆነ ሙሣ በማለት የኢሳም ልክ እንደዛው) እኛ ደግሞ የነብዩ ሠለላሁ ዐለይሒ ወሠለም ህዝብ እንደመሆናችን መጠን ሙሀመድ በማለት ይመልሣል

★ አላህ ፣ዲኑን ፣መልእክተኛውን የማያውቅ ሙናፊቅ ከሆነ ደግሞ « ሀ…ሀ…አላውቅም ሠዎች ሢሉ ሠማው አልኩ» በማለት ሢመልስ ይመቱታል
አላህ ከቀብር ቅጣት ይጠብቀን እና የቀብር ቅጣት ከዚህ ይጀምራል

★ወንድም እህቶች ዛሬ (ዱንያ ላይ) እነዚህን ነገሮች አውቀን እና ተግብረን ካላለፍን ነገ ቀብር ውስጥ የምንመልሠው ምላሽ አይኖረንም!!!

አላህ ከቀብር ቅጣት ይጠብቀን!!!