Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከውስጥም ከውጭም ማማር

ከውስጥም ከውጭም ማማር
```````````````` ````````````````
ابو فوزان
አንድ ሰው ሙስሊም ነው የሚባለው አምስቱን የኢስላም መሰረቶች በተግባር ሲያውል ነው።
① ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም ብሎ በአንደበት መመስከር
°> ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ መመስከር
② ሰላትን በስርዓቱ ቀጥ አድርጎ መስገድ
③ ዘካት (ምፅዋትን) በስርዓቱ መስጠት
④ ረመዳን ወርን መፆም
⑤ የመንገዱንና የወጪውን ጣጣ የቻለ ሐጅ ማድረግ
የልባዊ እምነቱ እውነታነት ደግሞ በእምነት መሰረቶች ይፈተሻል።
የኢማን መሰረቶች
¹~• በአላህ ማመን
* ብቸኛ ፈጣሪ፣ ጌታ፣ አምላክ መሆኑን ማመን
* ፍጡራንን በሙሉ የፈጠረ
* የሁሉም ጌታና አስተናባሪ
* በማንም የማይመሰል፣ ከማንም የማይመሳሰል፣
* ሊመለክ የሚገባውም ብቸኛ አምላክ እንደሆነ ማመን………
²~• በመላዕክቱ ማመን
* ከብርሃን የተፈጠሩ፣ ሃይላቸው፣ ፍጥነታቸው… ብርቱ የሆኑ እና
* ማንኛውንም ትዕዛዙን ወዲያው ሚፈፅሙ መላእክት እንዲሁም
* በትዕዛዙ ላይ የማይጨምሩ የማይቀንሱ የማይጥሱ መላእክት እንዳለው ማመን
ለምሳሌ:
ጅብሪል፣ ሚካዒል፣ ኢስራፊል፣ ማሊክ…
³~• በመፃህፍቱ ማመን
* ከነቢያት መካከል ለመረጠው መልእክተኛው መመርያ መፅሃፍ እንዳወረደላቸው ማመን
* ከቁርኣን በስተፊት ያሉት መፅህፍት ሁሉ ከአላህ ወደ ነቢያቱ መውረዳቸውን ከማመን ጋር በቁርኣን መውረድ እንደተሻሩና አሁን የሚሰራበት መመርያ ቁርኣን ብቻ እንደሆነ ማመን
ለምሳሌ:
# ቁርኣን፣ ተውራት፣ ኢንጂል፣ ዘቡር
⁴~• በመልዕክተኞቹ ማመን
* ከሰው ልጆች መካከል የመረጣቸውና የወደዳቸው መልእክተኞች እንዳለው ማመን
* መልእክተኞቹ ይዘው የመጡት ህዝባቸውን የሰበኩት መመርያ ሁሉ ከጌታችን የተላከብን መሆኑን ማመን ……
ለምሳሌ:
# ሙሀመድ፣ ዒሳ፣ ሙሳ፣ ኢብራሂም፣ ኑህ ...
ሰለላሁ ዐለይሂም ወሰለም አጅመዒን
⑤• በመጨረሻው ዕለት ማመን
* ይህቺ ዓለም ማብቂያ እንዳላትና በስተ መጨረሻም የትንሳዔው እለት የምትባል ሌላ ዓለም እንዳለ ማመን
* በእለቱ ሙታን እንደሚቀሰቀሱና ዳግም ሞት እንደሌለ ማመን
* የዘልዓለም የማይቋረጥ ደስታና ፍስሃ፣ ምቾትና እርካታ የተሞላበት ጀነት የሚባል ህይወትና ቦታ እንዳለ ማመን
* ዘልዓለማዊ የማይቋረጥ ቅጣትና ስቃይ ያለበት ጀሃነም የሚባል በእሳትና በተለያዩ መቅጫዎች የተሞላ ቦታ ራሱን የቻለ ዓለም እንዳለ ማመን
* በሰራነው መልካምም ይሁን ክፉ ተግባራችን መተሳሰብ (ሂሳብ) እንዳለብንና ምንዳውም እንደሚከፈለን ማመን
⑥• ደግም ይሁን ክፉ በቀዳእ እና በቀደሩ ማመን
* ማንኛውንም ክስተት የሚከሰተው በአላህ ውሳኔ ብቻ መሆኑን ማመን
* በህይወት የምንኖረው እሱ እስከወሰነልን ቀነ ገደብ ብቻ መሆኑን ማመን
* የሚደርስብን ክፉ ነገርም ይሁን የሚደርስልን መልካም ነገር በሙሉ በሱ እውቀትና ውሳኔ መሆኑን ማመን………
# ጠቅለል ስናደርገው አንድ ሰው አርካኑል ኢስላምን በተግባር እስካሳየ ድረስ ሙስሊም ይባላል።
`> ይሁንና የእምነቱ ትክክለኛነት የሚረጋገጠው ደግሞ የእምነት መሰረት ተደርገው የተቀመጡትን ስድስት መሰረቶች ሲቀበልና ሲያሟላ ነው።
`> ሁለቱም መሰረቶች ኣንዳቸው በአንዳቸው የተካተቱ ናቸው ።
`> አንድ ሰው ሙስሊም የሚያሰኘውን ተግባር እያሳየ በልቡ ግን ከእምነት መሰረቶች ያላመነበት ወይም የተፃረረው ነጥብ ካለ እስልምናው ጥያቄ ውስጥ ይገባል።
`> በተቃራኒው በልቤ ሁሉንም የእምነት መሰረቶች አምኛለሁ እያለ በተግባሩ የእስልምና መሰረቶችን የማያሳይ ከሆነም ጥያቄ ውስጥ ይገባል ።
ስለዚህ
እስልምናችን እንዲሰምር
ሙስሊምነታችን እንዲያምር
እምነታችን በፅኑ እንዲኖር
ሁለቱንም መሰረቶች ለይተንና አጣርተን እንወቅ እንተግብር።
ወላሁ አዕለም
ወሰለላሁመ ዓላ ነቢዪና ሙሐመዲን
ወዓላ ኣሊሂ ወሳህቢሂ ወሰለም
°°°°°°°°°°°••°°°°°°°°°°°
``~>> Abufewzan 18Dec2014

Post a Comment

0 Comments