Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሚዛናዊነት

ሚዛናዊነት

☞ ኢስላም በየትኛውም.የእምነቱ አካላት በሆኑት ነገራቶችም ላይ ፍጥረታቶችም ላይ ሚዛናዊ እምነት ነው 

✔ ከዚህ በመነሣት ርዕሡን ለሁለት ከፍለን እንመልከተው 

1 ኢስላም ባዘዛቸው ነገራቶች ላይ ሚዛናዊ መሆን  ፦   ማለት አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ በቁርአኑ መልእክተኛው ደግሞ በሀዲስ ያዘዟቸውን  እና የከለከሏቸውን  ነገራቶች ለማለት ተፈልጎ ነው 

☞እነዚህ ነገራቶች  በሁለት መልኩ ሚዛናዊነታቸውን ሊያጡ ይችላሉ 

1๏1በትእዛዛቶቹ ወይም በክልክላቶቹ ላይ  እራስን በማስገደድ ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንድንተገብራቸው የደነገገብን ነገራቶች በአጠቃላይ እኛን ለማስጨነቅ እና ለማስቸገር እንዳልሆነ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሢል ይነግረናል

" አላህ በናንተ ላይ ገሩን ነገር ይሻል ችግርን አይሻም "

☞ ይህም ከመሆኑ ጋር አንዳንድ ሠዎች የተለያዩ ኢስላም ቦታ ያልሠጣቸውን አልያም በጣም ያላጠበቃቸውን  ነገራቶች እንደ ትልቅ አጀንዳ በመያዝ.የሠው ልጅ መመዘኛ አድርገው ያስቀምጣሉ ለምሣሌ ከቅርብ ግዜ ወዲህ አገራችን ላይ አንዳንድ ግለሠቦች እራቸውን ወደ ሠለፍ(ሡሀቦች …) በማስጠጋት.ሠለፎች ይቻላል ለማለት እንኳን ጠቅሠው የማያውቋቸውን ወይም በመቻላቸው እና በመከልከላቸው ላይ እልባት ያልተሠጠባቸውን  ነገራቶች ከራሳቸው በመነጨ ግንዛቤ በመነሣት ከሠለፎች መንገድ አልያም ከኢስላም እንደሚያስወጣ የሚያስቡ እና  ለበራዕ በማያበቃ ርዕስ በራዕ የሚያደርጉ    ግለሠቦች ብቅ ብቅ ማለታቸው ሣንሠማ አልቀረንም. ድንበር ካለፋባቸው ነገራቶች መካከል ለአብነት ያክል

★ ሡሪ መልበስ ፦ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሡሪ አልለበሡም በሚል እሳቤ ሡሪ የለበሠን ሠው ከሠለፎች መንገድ  ለማባረር ይበቃሉ ይህ አካሔድ ከሠለፎች መንገድ እጅጉኑ የወጣ አካሔድ ነው 

★ ጀመአ (መልካም ነገራቶችን ለመተግበር መሠባሠብ)  ፦ ይህም ተግባር እነሡ ዘንድ ከሠለፎች አልተገኘም በሚል ምክንያት ከሠለፎች መንገድ    ማባረርያ መሣርያ አድርገው ይጠቀሙበታል. አልፎም ተሠባስበው የቲሞችን ፣  መድረሣዎች፣ ኡስታዞችን   በመርዳት ያሉ ሠዎች ላይ እጃቸውን ይቀስራሉ ፣  ስም ይለጥፋሉ…  

★ እና ሌሎችም በራዕ ደረጃ የማያደርሡ አልፎም ሀራም ያልሆኑ .ህግጋቶችን.እንደ ትልቅ የመንሀጅ ጉዳይ በመቁጠር ሠዎችን የሚያርቁበት ሁኔታ አለ 

✔ ከምክንያቶቻቸው በመነሣት ለነዛ ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሚስቶች መካከል ወደ አንዷ ለመጡት ሦስቱ ሠዎች ያሏቸውን እንላቸዋለን

"እኔ ከነናንተ በላይ አላህን ፈሪ ነኝ ነገር ግን እፆማለው አፈጥራለው ፣  እሠግዳለው እተኛለው ፣ ሤቶችንም አገባለው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም 

✔ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሡሪ አልለበሡም ብሎ ሡሪ መልበስ ከትክክለኛው  የሠለፎች አቋም ያስወጣል   ካሉ በርካታ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ያልሠሯቸው  ነገሮችን እንጠይቃቸዋለን 

1๏2 ቸልተኝነት ፦ ይህ ደግሞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የደነገጋቸውን ነገራቶች ከመጠን በላይ ቸል ማለት  ለዚህም ተግባ የተለያዩ ዛቻ አዘል አናቅፆች አሉ ከነዛ ውስጥ

"በጌታው አናቅፆች ከተገሠፀና ከዚያም ቸል ካለ ሠው ይበልጥ ነፍሡን የበደለ የለም እኛ አመፀኞችን ተበቃዮች ነን" ሠጅዳ

★ እና ሌሎች አያዎች!

☎ በማክረር ከተፈተኑት ባላነሠ ሁኔታ በቸልተኝነትም በርካታ ሠዎች ወድቀው እናገኛቸዋለን አስተውለን ከሆነ አንዳንድ ሠዎችን

★ የተለያዩ ዛቻ አዘል የሆኑ ትዕዛዛትን ቸል ሲሉ እናስተውላለን

★ ሡሪን ወይን ሽርጥን  ከቁርጭምጭሚት በታች ማውረድ የተለያዩ ዛቻዎች የመጡበት ነገር ነው ሆኖም አንዳን ጀመአዎች ግን ይህን ነገር ከመተግበርም ከማስተማር ቸል ብለው እናያቸዋለን 

★ ሽርክ ስራን በአጠቃላይ ያበላሻል ፣  ጀሀነም ውስጥ ዘውታሪ ያደርጋል   እያሉ ኡለሞች በየመፀሀፎቻቸው እየጠቆሙ  አንዳንድ ጀመአዎች ግን ኡማው እንዳይበታተን በሚል እሳቤ  ከሽርክ ማስጠንቀቅን ቸል በማለት እንደ ሁለተኛ ነገር የሚቆጥሩ ጀመአዎች አሉ 

★እንደ ተውሒድ ፣ ሡና  እና  ሌሎችም መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን ወደ ጎን በመተው በሌላ ነገር ሠውን የሚያጠምዱ ጀመአዎች አሉ  

2  በፍጥረታት.ላይ ሚዛናዊ መሆን ማለት ደግሞ ኢስላም ከመነሻው ዛሬ ድረስ የሚዪወሣቸው የተለያዩ ነብያቶች ፣  ሡሀቦች ፣  መላይካዎች እንዲሁም የተለያዩ የአላህን ሀያልነት ለማጉላት ተለምዶን በተቃረነ መልኩ የተፈጠሩ እንስሣዎች እና ሌሎች የኢስላም ሙሉ ታሪክ ሢወሣ አብረው የሚነሡ አካላትን በአጠቃላይ የተሠጣቸውን ክብር ሣንቀንስም ሣንጨምርም ክብራቸውን መስጠት ይህንን ለሁለት ከፍለን እንመልከት 

2๏1. በነዚህ ፍጥረታቶች ላይ ድንበር.በማለፍ ሚዛናዊነትን ማጣት  ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ከሰጣቸው ክብር  በላይ እየሠጡ በነዚህ አካላት ላይ ድንበር ማለፍ ይህ ተግባር ለመጀመርያ ግዜ አለም ላይ ሽርክ እንዲከሠት መነሻ የሆነው ምክንያት. ነው የኑህ ህዝቦች ለእነዛ አምስት ሦሊህ ሠዎች በነበራቸው ድንበር ያለፈ አመለካከት ሽርክን ለመጀመርያ ግዜ መሬት ላይ በማውረድ የመጀመርያዎቹ ናቸው

★ ዛሬም ላይ አንዳንድ መልካም ሠዎችን በተሣሣተ አመለካከት ያለ ደረጃቸው እያስቀመጡ ለማምለክ ይበቃሉ ይህ ተግባራቸው ደግሞ ከኢስላም ያስወጣቸዋል

★ መለኮታዊው ነብይ ግን  ይህ ሁሉ ነገር ያዩ ይመስል ገና ሣይከሠት ለኡመታቸው በማሠብ ነበር በሩን የዘጉት

"ነሣራዎች ኢሣን ከፍ ከፍ እንዳደረጉት እኔንም  ከፍ ከፍ ከፍ አታድርጉኝ.የአላህ ባርያ ነኝ የአላህ ባርያ እና መልእክተኛው በሉኝ  "

✔ ለነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የአላህ ባርያ መባል የሣቸውን ክብር ይጨምረዋል እንጂ አይቀንሠውም ለዚህም ነው የአላህ ባርያ ብላችሁ ጥሩኝ እያሉ የሚያስጠነቅቁን

✔ ይህ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ውጪ ያሉት ምን ሊባል ነው ከሣቸው በላይ አላህን የሚገዛ እንደሌለ ሁላችንም እናምናለን.ስለዚህ. ከሳቸው ውጪ ያሉት ደግሞ ከሣቸው በታች ናቸው 

2๏2 እነዚህን ፍጥረታቶች ከሚዛን በታች በማድረግ ሚዛናዊነትን ማጣት ፦  አላህ ሡብሀነሁ  ወተአላ እላይ የተጠቀሡትን አካላት በየደረጃቸው አስቀምጧቸዋል ከተሠጣቸው ደረጃ ዝቅ ማድረግ.አልያም ክብራቸውን መንካት  ሚዛናዊነትን ያሣጣል ለምሣሌ

★ሡሀቦች ለኢስላም የከፈሉትን መስዋትነት የትኛውም ትውልድ አልከፈለውም ስለዚህ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ደረጃቸውን ከፍ እንዳደረገው በነብዩ አንደበት እንዲህ ሢሉ ይነግሩናል 
"ሡሀቦቼን አትስደቡ አንደኛቹ የእሁድን ተራራ የሚያክል ወርቅ ቢሠጥ. እነሡ እፍኝ የሠጡትን አይደርስም ግማሹንም "

★ አንዳንድ ጀመአዎች ግን የሠሀቦችን ስም በአደባባይ ሢያነውሩ እንሠማቸዋለን ለአብነት ያክል 

✔ ሺአዎች አቡበከር ሢዲቅን ኡመርን አኢሻን (ረዲየላሁ አንሁም አጅመኢን) በጅምላ ያስከፍሯቸዋል   

✔ በሌላ በኩል ደግም  እነ ኡስማንን እና ሙአዊያን  ምንም ሣያስተርፉ በአደባባይ ሢያብጠለጥላቸው ሣንሠማ አልቀረንም

★ የሁዳዎች ኢሣ አለይሒ ሠላምን አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የሠጠውን ደረጃ በመንጠቅ  የመግደል ሙከራ እንዳደረጉት

★ እስካሁን በተጠቀሡትም ባልተጠቀሡትም የኢስላም ድንጋጌዎች ዙርያ #የአህለሡና_ወልጀመአ አቋም መሀከለኛ ነው ወደየትኛውም ጎን አያዘነብልም!!! 

አላህ የነሡን መንገድ የምንከተል ያድርገን

በማክረር ከተፈተኑት ባላነሠ ሁኔታ በቸልተኝነትም በርካታ ሠዎች ወድቀው እናገኛቸዋለን አስተውለን ከሆነ አንዳንድ ሠዎችን

★ እስካሁን በተጠቀሡትም ባልተጠቀሡትም የኢስላም ድንጋጌዎች ዙርያ ‪#‎የአህለሡና_ወልጀመአ‬ አቋም መሀከለኛ ነው ወደየትኛውም ጎን አያዘነብልም!!!
አላህ የነሡን መንገድ የምንከተል ያድርገን

Post a Comment

0 Comments