Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላም ሃይማኖታችን ታላቁ ፀጋ

ኢስላም ሃይማኖታችን ታላቁ ፀጋ፣ ለማንኛውም ዘመን፣ ለማንኛውም ትውልድ፣ ለየትኛውም ቦታ ብቁ የሆነ ከጉድለት የፀዳ ሙሉ፣ ውብ ሃይማኖት ነዉ። አላህ እንዲህ ይላል
أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ
"ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ፀጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ"
ይህ መልክት በትክክል የገባው ሙስሊም ከእርሱ የሚጠበቀው አላህ ያወረደውን ቀጥ ብሎ መከተል ብቻ ነው። "በጎደለ ሙላ" እንዳይባል ኢስላም አንድም የጎደለው ነገር የለውም፣ ጭራሽ ሙሉ ነው። ከእኛ የሚጠበቀው መከተል ብቻ ነው።
አላህ የሞላውን ኢስላም ታላቁን ፀጋ እንደታዘዝነው ብቻ ሳንጨምር ቀጥ ማለት ከቻልን የስኬቶች ሁሉ ታላቅ ስኬት ነው በሱና ላይ መታገስ ከቢድአ መራቅ ታላቁ እድል ነው።
*) መውሊድ ሙሉው ዲን አያውቀውም መጤ ፈጠራ ነው፣
*) ከሰላት በኀላ ኢማሙ ወደ ህዝብ ዞሮ ተከታዬች እየተቀበሉት ዱኣ ማድረግ መጤ ፈጠራ ነው፣
እና የመሳሰሉት "ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው" የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
አላህ ሆይ! ይህን ሙሉ ሃይማኖት ኢስላም በመከተል ላይ መጤ ነገሮችን በመራቅ ላይ ፅናቱን ለግሰን። አላሁመ አሚን።
ሀቅ 1 እና 1 ብቻ ናት የጥንት የጠዋቱ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎች መንገድ።