Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እውነት መውሊድ ውስጡ ሽርክ አለው ወይንስ ቢድዓ ብቻ ነው???

እውነት መውሊድ ውስጡ ሽርክ አለው ወይንስ ቢድዓ ብቻ ነው???
............
የአላህ ባርያዎች ሆይ! መቼም የሽርክ 1 ናት ችግር የለውም የሚባል ነገር የለም፡፡ አንድ ስራ ሽርክ ከተደባለቀበት ከዚህ በፊት የተሰራውን ሁሉ ጥሩ ስራ ድምጥማጡን ያጠፋዋል፤ ሰውየው በንሰሃ እስካልተመለሰ ድረስ፡፡ ሽርክ ከቢድዓ የሚለየው፤ ቢድዓ ያ የተሰራው ቢድዓ ብቻ ሲሆን ውድቅ እና ተመላሽ የሚሆነው፤ ሽርክ ግን ስራን ሁሉ አፈር ከድሜ ያስገባል፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አንዳንድ ወንድም እና እህቶች ‹‹ይህ አርስት ይዘግይልን፤ ወቅቱ አይደለም፤ ይበታትነናል፤ ጠላት ይጎዳናል እና የመሳሰሉትን›› የማይሆኑ ንግግሮች ሲደረድሩ ይታያሉ፡፡ እስቲ በአላህ ፈቃድ ትንሽ የፈሩትን ፍርሃት መልስ የሚሆን እንስጥ በአላህ ፈቃድ፡፡
1) አላህ ‹‹ፊትና ከመገደል ይበልጥ የበረታ ነው›› ይላል፤ ይህን አንቀፅ የተፈሰረው፤ ‹‹ሽርክ ከመገደል ይበልጣል›› በሚል ነው፡፡ ታድያ፤ ከመታሰርም፤ አገር ለቆ ከመሰደድም፤ ከመሸነፍም፤ ከመገደልም ሁሉ በላይ የሆነው አስከፊው ‹‹ሽርክ›› ጉዳቱ ተገለፀልን የአላህ ባርያዎች ???
2) ሽርክ የፍርሃት፤ የመከራ፤ የእርስ በርስ አለመስማማት፤ በጠላት የበታች መሆን፤ የአላህን ቁጣ የሚያመጣ፤ የአላህን ድል በፍፁም የማያስገኝ፤ በዱንያም የሚያዋርድ፤ በአኸይራም አሳማሚ ቅጣት የሚያስገኝ ነው፡፡
3) ተውሂድ እና ሱና በፍፁም አይበታትንም፡፡ እንዲያውም ‹‹ቢድዓ እና ሽርክ›› እየታየ ‹‹አይበታትነንም›› የሚለው ቃል ነው፤ ሰውን ሁሉ ባለበት እንዲሄድ እና የተበታተነ ሆነ ‹‹አንድ ነን›› ብሎ ‹‹የውሸት አንድነት›› ልቦናዎች እና እምነቶች የተለያዩበትን ያካተተው ግን ‹‹አንድ ነን›› እንዲሉ የሚያደርገው፤ የውሸት አንድነት ነው ኡማውን የሚበታትነው፡፡ ለመከራ የሚዳርገውም ‹‹ሽርክ እና ቢድዐ›› እንጂ ‹‹ተውሂድ እና ሱና›› አይደለም፡፡
4) ‹‹እንዳንከፋፈል›› በሚል ሀሳብ፤ ሽርክ እና ቢድዓን ይዘን ሄደን፤ አላህ ይረዳን ይመስላችኋልን??? ይልቁንስ ሃቅን ይዞ መሄድ ነው፡፡ በተለይ በፈተና ዘመን፡፡ ከሽርከ የበለጠም ፈተና የለም፡፡
እስቲ እውነት መውሊድ ውስጡ ሽርክ አለው ወይንስ ቢድዓ ብቻ ነው???
የሚከተሉት የሽርክ አባባሎች ኢትዬጵያ ውስጥ ከሚባሉ ሽርኮች ውስጥ ናቸው፡፡
1) አጊሱና ገውሱ አልዩል ጎንደሪ
2) አጊስና ሰይድ ሐጂ ሙጃሂዱ፤ ፈይዲ ረህመቲ አላህ ፤ አለይኩም መደዱ
3) ያሪጃለላህ ያሪጃለላህ አጊሱና ቢላህ
-- ይህ እንግዲህ ‹‹ኢስቲጋሳ›› የጭንቅ ግዜ ዱዓ ይባላል፡፡ በጭንቀትም በሰላምም ግዜ ተለማኙ አላህ ብቻ ነው፡፡ ዱዓን ከአላህ ውጭ ማድረግ ደግሞ ታላቁ ሽርክ ነው፡፡ በመቀጠል
4)አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
መገን ነቢ (በጣም ይገርማሉ ነቢ)
የሁሉ ቀላቢ
በመቀጠልም
5)ለካም አንቱ ነሁ ያነቢ
ለመላው ኸልቅ ቀላቢ
ብትን ያለውን ሰብሳቢ
በሶፋ ቡራቅ ጋላቢ
አላህ ደግሞ የነዚህን ሽርክ አባባሎች ውድቅነት እንዲህ ሲል ያስቀምጠቃል
በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ እውነታው ይህ ነው፡፡ መውሊድ ውስጡ ሽርክ አለ፡፡
በመቀጠልም
6)አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
መህቡቢላሂ (የአላህ ውድ)
ጃሚኢ ሲፋቱላሂ
(የአላህን ባህሬ ጠቅልለው የያዙ)
ይህ ከባድ አባባል ነው፡፡ የአላህን ባህሪ ጠቅልሎ መያዝ፡፡
በመቀጠልምአገራችን መውሊድ ላይ ከሚባሉት ሽርክ አባባሎች ውስጥ ሙናዊ የሚባለው ኪታብ ላይ፤ አዲስ አበባ የሚቀራው ይህ ነው፡፡
7)ያሙሀመዲ ያሀቢቢ
ያሙሀመዱ ኩን ጠቢቢ
(ዶክተሪ ሁኑ)
ወአጂርኒ ሚን ለሂዲ
(ከእሳት ጠብቁኝ)
ኢነ አውዛሪ ሲቃል
(ወንጀሌ ከባድ ነው)
የሚከትለውም ቅጥፈት ይገኝበታል
8)ያወጣማ ሰው መውሊድ
ቀልቡን ሳይከብደው በውድ
ይደርሱለታል ከለህድ (በቀብር ማለት ነው)
ትቶት ሲመለስ ዘመድ
9) አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲ
ኡህዱርሊ ፊይ ቀብሪ አጂቡ ሱዓሊ (ቀብሬ ላይ ኑ እና መልስ ስጡልኝ የአላህ መላክተኛ እያሉ ነው)
ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ከአላህ ሌላን እየጠራ (እየለመነ) የሞተ ሰው እሳት ገባ››፡፡
ታድያ እነዚህ እና የመሳሰሉት ካሉ የአላህ ባርያዎች! ወገናችንን የሽርክ እና የቢድዓን አስከፊነት ማስጠንቀቅ ወይንስ አይለያየንም ብሎ ኡማው ወደ እሳት ሲሄድ እያዩ ዝም ማለት???
መልካም አስባችሁ ይሆናል፤ እኛ ሌላ አላማ አላቸው አንላችሁም፤ ግን ከአላህ እና መልክተኛው በላይ አዛኝ የሆነ ስለሌለ፤ እኛ ሁላችንም የአላህ እና መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትእዛዝ እንከተል፤ ክልከላዎችን እንራቅ እያልን ነው፡፡
መቼም ሽርክ እና ቢድዓ እያለ አላህ ይረዳናል ብሎ መገመት ዘበተት ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው ሃቁን ማድረስ ነው፤ ረዳቱ አላህ ነው፡፡ ለወገናችን እንዘን፤ በሰው ህይወት አንጨክን፤ ዛሬ አንድ ነን ተብለው በሽርክ የሞቱ ሰዎች ነገ ክስ ቢያቀርቡ ምን ይውጠናል???
መቼም አላህ የሚረዳው ሃቅን ነው፤ ባለቤቶቹ ጥቂት ቢሆኑም፤ ልክ እንደ ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) ብቻውን ቢሆንም፡፡ ይህ ለአእምሮ ባለቤቶች ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ አላህ ሆይ! አንቃን፡፡
አላህ ሆይ! ፈተናችንን በሃይማኖታችን ላይ አታድርግብን፤ ዱንያን ታላቁ ግባችን አታድርጋት፤ በጠላቶቻችን ላይ ድልን ስጠን፡፡ የአላህ ሰላትና እና ሰላም በመልክተኞቹ፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አላሁመ አሚን