Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድን ማክበር ይፈቀዳል የሚሉ ወገኖች የሚያቀርቧቻዉ ማደናገሪያዎችና የተሰጧቸዉ ምላሾች



መውሊድን ማክበር ይፈቀዳል የሚሉ ወገኖች የሚያቀርቧቻዉ ማደናገሪያዎችና የተሰጧቸዉ ምላሾች
መውሊድን ማክበር ስለመፈቀዱ እንደ መረጃ የሚጠቀሱት ማደናገሪያዎች (ሹቡሐት) ከላይ ከተብራሩት ክልክልነቱን ከሚያስረግጡ ግልፅ መረጃዎች ጋር የሚጋጩ በመሆናቸዉ ዉድቅነታቸዉ አያጠያይቅም፡፡ አብዛኛዎቹ ተራ ውዥብሮች ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ስለዲናቸዉ ሰፋ ያለ ግንዛቤ በሌላቸዉ ሙስሊሞች ላይ ዉዥንብር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ዋናዎቹን ከነምላሸቸው እንሆ!!
   ሹብሐ ቁ 1- እነዚህ ሰዎች ‹‹ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው!!›› ከሚለዉ ነብያዊ መርሆ በመውጣት ‹‹ቢድዓ ሁለት ዓይነት ነው፤ጥሩና መጠፎ›› ይላሉ!! መውሊድ ጥሩ ቢድዓ (ቢድዐቱል ሀሰናህ) ነው፡፡ የተከለከለው ደግሞ መጥፎ ቢድዓ ነው፡፡ ለዚህም ሁለት ማደናገያዎችን በመጥቀስ ቢድዓ ሀሰናህ የሚለዉን ሃሳብ ያጠናክራሉ፤
አንደኛ፡- መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል ‹‹በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ(ሱና) ፈር የቀደደ ለእርሱ የዚህ ስራ ምንዳ እና ይህንን ፈለጉን ተከትሎ የሚሰራ ሰውን ሁሉ ምንዳ አለው፡፡ ይህም ከእርሱ ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ነው›› ሙስሊም በቁጥር 1017 ከጀሪር ኢበኑ አብዲላህ አል-በጀሊይ ዘግበውታል
የመጀመሪያዉ ማደናገሪያ ምላሽ እነደሚከተለው ይሆናል፡-
ويمكن أن يقال إن معنى قوله ( :( من سن ) أي من أحيا سنة كانت موجودة فعدمت فأحياها وعلى هذا فيكون " السن " إضافياً نسبياً كما تكون البدعة إضافية نسبية لمن أحيا سنة بعد أن تركت .
رواه مسلم عن جرير بن عبد الله البجلي رضي الله عنه قال: ( بينما كنا عند رسول الله صلى الله عليه وسلم إذ جاء قوم عامتهم من مضر، بل كلهم من مضر، مجتابي النمار؛ فلما رآهم النبي صلى الله عليه وسلم، تمعر وجهه -مما رآهم عليه من الفاقة- فأمر بلالاً فأذن فأقام فصلى، فخطب في الناس ثم قال: ليتصدق أحدكم من صاع بره، من صاع تمره، من درهمه، حتى ذكر شق التمرة، فقام رجل من الأنصار فأتى بصرة كادت يده أن تعجز عن حملها بل عجزت فوضعها، فتتابع الناس كل يأتي بما عنده حتى صار عند النبي صلى الله عليه وسلم كومان من طعام وإهاب، فرأيت وجه رسول الله صلى الله عليه وسلم تهلل كأنه مذهب، ثم قال: من سن في الإسلام سنة حسنة فله أجرها وأجر من عمل بها إلى يوم القيامة، ومن سن في الإسلام سنةً سيئة فعليه وزرها ووزر من عمل بها إلى يوم القيامة ).

1ኛ፡-ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) ይህንን ሀዲስ የተናገሩበትን ምክኒያት በዚሁ ሀዲስ ላይ ስናነብ ሀሳቡን በትክክል እንረዳዋለን፡፡ነገር ግን ቢድዓቱል ሀሰናህ አለ የሚሉ ሰዎች የሀዲሱን ሙሉ ሀሳብ ማስቀመጥ ስለማያዋጣቸዉ አይጠቅሱትም፡፡ ጀሪር በዚሁ ሀዲስ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ረሱል ዘንድ ተቀምጠን እያለ ከሙደር ጎሳ የሆኑ ሰዎች መጡ፡፡ ረሱልም በሰዎቹ ላይ ባዩት እንግልትና ችግር ስሜታቸዉ ተነክቶ ፊታቸዉ ተቀያየረ…›› ከዛም ሰሃቦችን ሰደቃ አንዲሰጡ ሲያነሳሷቸው አንድ ከአንሳር የሆነ ሰሃብይ ሊሸከመዉ የከበደዉን ምግብ ከሁሉም ቀድሞ በመስጠት መዋጮዉን  ጀመረዉና ለሌሎቹ አርዓያ ሆነ፡፡ ሁሉም በሰደቃ ተሽቀዳደሙ፡፡ ጀሪር ‹‹የረሱል ፊት ልክ እንደወርቅ ሲያብረቀርቅ አየሁ›› አሉ፡፡ ከዛም ከላይ የቀረበዉን ንግግራቸዉን ተናገሩ…፡፡ቢድዓ የሚባለዉ በዲን ዉስጥ አዲስ የተጨመረ ነገር ነዉ፡፡ ሰደቃ ደግሞ በሸሪዓ አስቀድሞ የተደነገገ ተግባር እንጂ አዲስ ፈጠራ አይደለም! ስለዚህ ይህ በዲኑ ውስጥ ለሚጨምሩ ሰዎች በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም።
2ኛ- ነቢዩ በዚህ ሀዲስ ላይ ‹‹በኢስላም ውስጥ›› እና ‹‹ (ሰነ ሱነተን ሀሰናህ) የጥሩ ፈለግ(ሱና) ፈር የቀደደ ›› ማለታቸውን እናስተዉል፡፡
3ኛ- ይህ ሀዲስ ሰዎች የረሱትንና የዘነጉትን ሱና ህያው ማድረን ይመከታል፡፡ ይህንን ሀዲስ በሚገባ የሚያብራራዉ ለመነገሩ ሰበብ የሆነዉ ክስተት ቢሆንም ሀሳቡን የሚያጠናክርና ምን እንደተፈለገበት የሚያሳይ መልዕክት ያለዉ ሀዲስም አለ፡፡ቢላል ኢብኑልሀሪስ ረሱል እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ይላሉ ‹‹ከኔ በኋላ (የሞተን) የተረሳን ሱና ህያዉ ያደረገ (እርሱን ተከትለዉ) ይህንን ሱና በሰሩበት ሰዎች ሁሉ ከእነርሱ ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ምንዳ ያገኛል፡፡
عن بلال بن الحارث( قال :( سمعت رسول الله ( يقول : من أحيا سنة قد أميتت بعدي فإن له من الأجر مثل من عمل بها من الناس لا ينقص ذلك من أجورهم شيئاً ومن ابتدع بدعة لا ترضي الله ورسوله فإن له مثل إثم من عمل بها من الناس لا ينقص ذلك من آثام الناس شيئاً ) رواه الترمذي وابن ماجة . وقال الترمذي : هذا حديث حسن . وقال البغوي : هذا حديث حسن . وصححه الشيخ الألباني (1).
سنن الترمذي مع شرحه عارضة الأحوذي 10/106-107 ، سنن ابن ماجة 1/76 ، شرح السنة 1/233 ، صحيح سنن ابن ماجة 1/41-42 .

ሁለተኛ፡- (ሰዎች የተራዊህን ሰላት ተለያይተው በሚሰግዱ ጊዜ ኸሊፋው ዑመር ተሰባስበው እንዲሰግዱ ካደረጓቸው በኋላ ‹‹ምንኛ ያማረች ፈጠራ(ቢድዓ) ናት!›› አሉ) አል ቡኻሪ በቁጥር 2012 ዘግበውታል
1. إن القول بأن البدعة في الدين تنقسم إلى حسنة وسيئة مما لا أصل له في الشرع فلا دليل عليه من قول الرسول ( فلم يرد لفظ البدعة على لسان رسول الله ( إلا على سبيل الذم .
وأما قول عمر ( : ( نعمت البدعة هذه ) فليس فيه ما يفيد أن لفظ البدعة بمجرده يطلق في الشرع على ما هو حسن وإنما يقصد بقول عمر ( البدعة بمعناها اللغوي فهي التي تنقسم إلى حسنة وسيئة .
قال شيخ الإسلام ابن تيمية :[ أكثر ما في هذا تسمية عمر تلك بدعة مع حسنها وهذه تسمية لغوية لا تسمية شرعية وذلك أن البدعة في اللغة تعم كل فعل ابتداء من غير مثال سابق وأما البدعة الشرعية فكل ما لم يدل عليه دليل شرعي ] (1).

قول عمر ( الذي رواه الإمام البخاري بسنده عن عبد الرحمن بن عبد بن عبد القاري أنه قال :[ خرجت مع عمر بن الخطاب ليلة في رمضان إلى المسجد فإذا الناس أوزاع متفرقون يصلي الرجل لنفسه ، ويصلي الرجل فيصلي بصلاته الرهط ، فقال عمر : إني أرى لو جمعت هؤلاء على قارئ واحد لكان أمثل ثم عزم فجمعهم على أبي بن كعب ثم خرجت معه ليلة أخرى والناس يصلون بصلاة قارئهم ، قال عمر : نعم البدعة هذه والتي ينامون عنها أفضل ، يريد آخر الليل وكان الناس يقومون أوله ] (1) وقوله أوزاع أي جماعة متفرقون .
قال الحافظ ابن حجر :[ في بعض الروايات نعمت البدعة بزيادة تاء ] (2).
خرج أبو داود عن أبي ذر قال : ( صمنا مع رسول الله ( رمضان فلم يقم شيئاً من الشهر حتى بقي سبع ، فقام بنا حتى ذهب ثلث الليل فلما كانت السادسة لم يقم بنا ؟ فلما كانت الخامسة قام بنا حتى ذهب شطر الليل فقلنا : يا رسول الله لو نفلتنا قيام هذه الليلة ؟ قال ، فقال : إن الرجل إذا صلى مع الإمام حتى ينصرف حسب له قيام ليلة . قال : فلما كانت الرابعة لم يقم ، فلما كانت الثالث جمع أهله ونسائه والناس فقام بنا حتى خشينا أن يفوتنا الفلاح . قال ، قلت : وما الفلاح ؟ قال السحور . ثم لم يقم بنا بقية الشهر ) ونحوه في الترمذي وقال فيه: حسن صحيح.
لكنه ( لما خاف افتراضه على الأمة أمسك عن ذلك ففي الصحيح عن عائشة رضي الله عنها : ( أن النبي ( صلى في المسجد ذات ليلة فصلى بصلاته ناس . ثم صلى القابلة فكثر الناس ثم اجتمعوا الليلة الثالثة أو الرابعة فلم يخرج إليهم النبي ( فلما أصبح قال : ( قد رأيت الذي صنعتم فلم يمنعني من الخروج إلا أني خشيت أن يفرض عليكم ) وذلك في رمضان وخرجه مالك في الموطأ .
فتأملوا ففي هذا الحديث ما يدل على كونها سنة فإن قيامه أولاً بهم دليل على صحة القيام في المسجد جماعة في رمضان وامتناعه بعد ذلك من الخروج خشية الافتراض لا يدل على امتناعه مطلقاً لأن زمانه كان زمان وحيٍ وتشريع فيمكن أن يوحى إليه إذا عمل به الناس بالإلزام : فلما زالت علة التشريع بموت رسول الله ( رجع الأمر إلى أصله وقد ثبت الجواز فلا ناسخ له .
وإنما لم يقم ذلك أبو بكر( لأحد أمرين : إما لأنه رأى أن قيام الناس آخر الليل وما هم به عليه كان أفضل عنده من جمعهم على إمام أول الليل، ذكره الطرطوشي ، وإما لضيق زمانه ( عن النظر في هذه الفروع مع شغله بأهل الردة وغير ذلك مما هو أوكد من صلاة التراويح

وقال ابن حجر المكي :[ وقول عمر ( في التراويح نعمت البدعة هي ، أراد البدعة اللغوية وهي ما فعل على غير مثال كما قال تعالى :( قُلْ مَا كُنْتُ بِدْعًا مِنَ الرُّسُلِ ) وليست البدعة شرعاً فإن البدعة الشرعية ضلالة كما قال ( ] (2).
1ኛ፡-የተራዊህ ሰላት ሱና እንጂ ቢድዓ አይደለም! ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) የተወሰኑ ቀናት ሰርተው አቁመውታል፤ ምክንያታቸውንም ተናግረዋል፡-ዋጂብ (ግዴታ) እንዳይሆንብን ፈርተው ነው18፣ ግን ከአላህ የሚተላለፈዉ ወህይ ከነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) በኋላ ስለማይመጣ በዑመር ጊዜ ዋጂብ እንዳይሆንብን የሚፈራበት ምክንያት አልነበረም፤ ስለሆነም ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) የጀመሩትን ሥራ ዑመር ቀጠሉት፣ ይህን ይበልጥ የሚያብራራው የሚቀጥለው ነጥብ ይሆናል፡­2ኛ፡-በዲናችን የተከለከለዉ ቢድዓን መስራት ነዉ እንጂ ቢድዓ የሚለውን ቃል መጠቀም አይደለም።ቢድዓ እንደሌሎች ብዙ ቃላት ሸሪአዊና የቋንቋ ትርጉም አለው።ተቋርጦ እንደ አዲስ በመጀመሩ፤ ዑመር የፈለጉት ቋንቋዊ ትርጉሙን ነው።የሰሩትም ሥራ ሱናና መሰረት ያለው እንጂ አዲስ ፈጠራ አልነበረም። 3ኛ፡-ዑመር የሠሩት ሥራ በሰሀቦች ሁሉ ስምምነት የፀደቀ የኹለፋዎች ፈለግ በመሆኑ በሸሪዓ ቢድዓ አይባልም!
ታዲያ ከላይ በተጠቀሱት አስረጂዎች የተኮነነው በዲን ስም የሚተገበረው የቢድዓ ዓይነት  ነው እንጂ አንዳንድ ሰዎች ‹አዲስ ፈጠራ ማምጣት ይቻላል!› ብለዉ ለመሞገት ሲፈልጉ የሚጠቅሷቸዉ የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች አይደሉም።ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) በዋነኝነት ለማስተማር የተላኩት እነዚህን ዝርዝር የዱንያ ጉዳዮች አይደለም፤ ለመዲና ገበሬዎችም ይህንን ምላሽ ሰጥተዋል፡-
“ስለ ዱንያ ጉዳያችሁ እናንተ ይበልጥ ታውቃላችሁ!” ስለዚህ ቁርዓንን በአንድ ጥራዝ ማስቀመጥ፣ የእስር ቤቶችን ማዘጋጀት፣ ስፒከርን መጠቀም የመሳሰሉት በመልእክተኛው ዘመን ባይከሰቱም ወጥ የዒባዳ ተግባራት ሳይሆኑ ወደ ኢባዳ የሚያደርሱ አጋዥ መዳረሻዎች ስለሆኑ ነው።እነዚህ ደግሞ (መሳሊህ ሙርሰላ) ይባላሉ፣ ከቢድዓ ጋር በፍፁም አይገናኙም20
2- ሙስሊሞች ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚሰሩት ተግባር ነው፡፡ ኢብኑ መስዑድ በተናገሩት መውቁፍ በሆነ ሀዲስ መሰረት ‹‹ሙስሊሞች ጥሩ አድርገዉ የተመለከቱት ነገር ሁሉ አላህ ዘንድ ጥሩ ነው››  ስለዚህ መውሊድ የብዙኃኑ ሙስሊም ስራ ነዉና ልንቀበለዉ ይገባል ይላሉ፡፡
የእዚህም ምላሽ፡- ኢብን መስዑድ ይህንኑ ንግግር የጨረሱበትን ዐረፍተ ነገር ስንመለከት  መልክቱን እንረዳዋለን ፡፡  ‹‹በአቡበከር ኸሊፋነት ሶሃቦች ተስማምተዋል ነው›› የሚለው፡፡ በዚህ መሰረት ብዙ ዑለማዎች ይህ ንግግር የሙስሊሞች ሙሉ ስምምነትን ወይም ‹‹ኢጅማዕ››ን የተመለከተ እንጂ የብዙኃኑን (የተራውን) ህዝብ ስምምነት የተመለከተ እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡ ለኢጅቲሀድ ብቁ የሆኑ ታላላቅ ዑለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) ሁልጊዜ ትክክለኛ መረጃን መነሻ ያደረገ በመሆኑ እንደ አንድ የኢስላም መረጃ ምንጭ ይቆጠራል፡፡
መውሊድን ማክበር በሁሉም ኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) የፀደቀ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ቢድዓ ለመሆኑ የሁሉም ስምምነት አለ፡፡ ለመዉሊድ ሸሪዓዊ መሰረት የሚሰጡት እንኳ ቢድዓ መሆኑን ግን ይቀበላሉ ‹‹ጥሩ ቡድዓ ነው›› የሚል መከራከሪያ ቢያነሱም፡፡ ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነዉ የቢድዓ ጥሩ የለዉም፤ ሁሉም ጥመት ነዉ፡፡

3 - አላህ በቁርዓኑ ላይ ነብዩን እንድናብርና እንድናልቃቸው አዞናል፡፡ ስለዚህ ለእሳቸው ያለንን ክብር ልደታቸውን በማክበር እንገልጻለን ይላሉ፡፡ የዚህ ምላሽ
·      አላህ (ሱ.ወ) ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከበሩት እና ከጎኑ የቆሙት ሲያወድስ አያይዞ ለእሳቸው የወረደው ወይም ኑር (ብርሃን) የተከተሉትን ያወድሳል (አልአዕራፍ157) ‹‹የተከተሉ›› የሚለው በራሳቸው ፈጠራ ውዴታን የገለፁ ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ እውነት ተከታይ የሆነ ሰው ከሚያዝዘው አካል ትዕዛዝ ውጭ በፍፁም አይዛነፍም
·      ሶሃባዎች በዚህ አንቀፅ የተወደሱት አምነው በመከተላቸው እንጂ መውሊድን በማድረጋቸው አይደለም ፡፡ ይህንን አስበውትም አያውቁም ለነብዩም (ስዐወ) ይህንን ጥያቄ አላነሱም፡፡ ይህ የቁርዓን አንቀፅ እነሱን ሳይሆን እኛን መውሊድን የምናከብረውን ብቻ ነው “ሚመለክተው” ካላችሁ ግልፅ ጥመት ነው፡፡
·      ነቢዩን ማክበርና ማላቅ የሚረጋገጠው ትዕዛዛቸውን በማክበር፤ፈለጋቸውን በመከተልና በመሳሰሉት እንጂ በዓመት እንድ ጊዜ እየተሰባሰቡ መውሊድን ማክበር አይደለም ፡፡ በጥቅሉ በዚህ ዙሪያእንደ መረጃ የሚጠቀሱት አንቀፆች በሙሉ በተዘዋዋሪ የሚጠቀሙት ተቃራኒውን ነው፡፡

4- ነብዩ (ሰዐወ) ሰኞን ይፆሙ ነበር፡፡ ሲጠየቁም ‹‹ይህ የተወለድኩበት፤ቁርዓንም
በኔ ላይ የተወረደበት ቀን ነው››፡፡ ማለታቸው በሱኒህ ሙስሊም ተዘግቧል የነብዩ(ሰዐወ) ልደት የሚከበር ባይሆን ኖሮ ባናከበሩትነበር ፡-ይላሉ
የዚህ ምላሽ
    4.1 ነብዩ (ስዐወ) የተወለዱት ቀን ሰኞ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን ሰኞ
        የፆሙት ቀኑን ለማክበር ነው የሚለው እሳቸው ያሉት አይደለም ፡፡
        እንዲያውም ነብዩ (ሰዐወ) (በብዙ ሐዲሶች ላይ)‹‹ ሰኞና ሐሙስን ለምን
        ይፆማሉ?›› ተብለው ሲጠየቁ ፡-‹‹እነዚህ ሁለት ቀናት ሥራዎች ወደ አላህ
        የሚቀርቡባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ሥራዬ እኔ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርቡልኝ
        እወዳለሁ፡፡›› በማለት መልሰዋል፡፡
          የሰኞና የሐሙስ ፆሞች የተያያዙና አላማቸው አንድ የሆኑ ፆሞች ናቸው
       ነብዩ(ሰዐወ) የአኺራ ጥቅሞችና ደረጃቸው ከፍ እንዲል የፆሟቸው እንጂ ወደ
       ዱንያ የመጡበትን ቀን ለማክበር ፈልገው እንዳልሆነ ራሳቸው ገልፀውታል፡፡
       ነቢያችን (ሰዐወ) የተወለዱት በነብይነት የተላኩበትና ያረፍበት ቀን ሰኞ
       መሆኑን ልብ እንበል፡፡
    4.2 ነብዩ (ሰዐወ) የፆሙት ሰኞን እንጂ ረቢዕ 12ኛን ቀን አይደለም ፡፡ ስለዚህ
        ረቢዕ 12ን ለመፆምም ሆነ ለማክበር ማስረጃ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰኞን መፆም 
        ማንም አይከለክለንም ፡፡ ቢድዓ ነው ያለም የለም፡፡
    4.3 በመውሊድ አክባሪዎች ዘንድ ይህ መውሊድ በዓል ነው ፡፡ ነብዩ(ሰዐወ) ግን
       ሰኞን ፆም አድርገው ነው የያዙት፡፡ ፆምና በዓል (ዒድ) ደግሞ ተቃራኒ የሆኑ
       ተግባሮች ናቸው፡፡ ነብዩ (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹የኢዳችሁን ቀን ፆም
        አድርጋችው  አትያዙ ›› ሃኪምና አህመድ በዘገቡት ስሂህ ላይ ሀዲስ
       እውነተኛ የነብዩ ወዳጆች ከሆንን ለነብዩ (ሰዐወ) ሱና እጅ እንስጥ በእርግጥ ሰኞ
       ሐሙስን እንፁም ፡፡ በአመት አንድ ጊዜ ተሰብስቦ በመብላትና በመጨፈር ግን
       ለእሳቸው ያለንን ክብርና ውዴታ ገለፅን አይቻልም፡፡
5.‹‹ነብዩ (ሰዐወ) የተለያዩ ክስተቶችን በማስታወስ ድሆችን ያበላሉ፤ይፃማሉ፤ያርዳሉ፡፡
       ለዚህም የጁምዐ፤የሐጅንና የአሹራን ተግባሮች መመልከቱ በቂ ነው፡፡ በዚህ
       መልኩ የነብዩን ውልደት በማስታወስ ድሆችን ባናበላ ምንም እግር የለውም
       እንዲሁም አደም( )የተፈጠሩበት ቀን ስለሆነ ጁምዓን እንደምናከብር ሁሉ ነቢዩን (ሰዐወ) እያስታወስን የልደታቸውን ቀን ብናከብር ምንም ችግር የለበትም ይላሉ፡-

የዚህ ምላሽ፡-
5.1 ነቢዩ (ሰዐወ) ክስተቶችን በማስታወስ ያረዱበትንና ያበሉበት አንድችም አጋጣሚ የለም፡፡ በነቢዩ (ሰዐወ) የህይወት ዘመን በርካታ ጥሩ ክስተቶች አልፈዋል፡፡
ለምሳሌ፡- ኢስራእ፣ሚዕራጅ፣የበድር ዘመቻ፣ የመካ መከፈት፣ የቁርአን መውረድ (ቅደም ተከተላቸውና ተጨማሪ ክስተቶች ይተከሉ) እና የመሳሰሉት ታላላቅ ክስተቶችን ተጨማሪ ክስተቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ችስተቶች በማስታወስ የሚያከብሩት ዓመታዊ በዓል አልነበራቸውም፡፡ ለዚህም መረጃ ለማምጣት እነሞክራለን ካሉ ይሞክሩት፡፡ የኑህን ዕድሜ ቢሰጣቸውም መረጃ አያገኙለትም
4.2 ሓጅ የተደረገው የሀጃሮን የኢብራሂምንና የኢስማኤልን ታሪክ የማውሳትና ለማስታወስ ነው ብለው ካሰቡ ይህ ትልቅ ስህተት ነው ነቡዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ያስተማሩን ሃጅ የተደነገገው የአላህን ውዳሴ ከፍ ለማድረግ ነው ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ የኢሻ በምታስተላልፈው እንዲህ ሀዲስ ይሉናል፡፡
     ‹‹ ካዕባን መዞር በስፋንና መርዋ መሀል መሮጥ ጠጠርንም መወርወር የተደነገጉት የአላህ ውዳሴ ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ ›› በአንዳንድ ዘገባናዎች ላይ አላህን ለማወደሰ ነው እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡
በቂያስ ላይ መመርኮዝ እንደማይቻል የታወቀ ነው፡፡ ያ ካልሆነ ግን ሁሉም ልቅ በሆነ መልኩ አዳዲስ የአምልኮ ተግባሮችን በመጠንሰስ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ ህግጋት እንዲረሱና እንዲቀየሩ በር ይከፍታል፡፡ ይህ በሌሎች ሀይማኖቶች ላይ የሚስተል ዕውነታ ነው፡፡
አህመድ (24351) አቡዳውድ፣አትቲርሚዚይ (902)፣አዳሪሚይ (1853) አለ እና ሌሎችም ዘግበውታል በሰነዱ ውስጥ ዑለማዎች የተለያዩበት አስተላላፊ አለ፡፡
4.3 አሹራን በተመለከተ የተደነገገው ፆም ነው መፆም ማለት ደግሞ እለቱን የተለየ በአል ማድረግ እልዳልሆነ ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ አሹራ መቼ እንደሆነ በትክክል ይታወቃል መውሊድ ግን ቀኑ እንኳን በትክክል አይታወቅም እኛም አሹራን አትፁሙ አላልንም መፆምና እለቱ ማክበር ግን በፍፁም የተለያዩ ናቸው፡፡ ለዚክር እራሳችንን እናዘጋጅ ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ላዘዙን ተግባሮች ለስለዋትና
4.4 ጁምዓን የምናከብረው አደም የተፈጠሩበት ቀን ስለሆነ እንደሆነ ማን ነገራችሁ እንዲህ አይነት ንግግር በቂ ማስረጃ ያስፈልገዋል በጁምአ ደግሞ ብዙ ነገሮች ተከስተዋል ሙስሊሞች የታዘዝነው በሰላትና በኹጥባ አላህን እንድናወሳ ነው እንጂ አደም የተፈጠሩበተ ቀን ስለሆነ በዚህ ምክንያት እንድናከብረው አይደለም፡፡
”እናንት ያመናችሁ ሆይ በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ሂዱ መሸጥንም ተው ይሃችሁ የምታውቁ ብትሆኑ ለናንተ በጣም የተሻለ ነው”
                              / - ቅዱስ ቁርዓን 62-9/
5. <<ነብዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ሰዎችን አቂቃ እንዲያወጡ ካዘዙ በኋላ ለራሳቸው አወጡ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ ግን በልጅነታቸው አቂቃ አውጥተውላቸዋል ስለዚህ ሁለተኛ ያወጡት ለአቂቃ ሳይሆን ልደታቸውን ለማክበር ነው ምክንያቱም በኢስላም ሁለት አቂቃ የለም አንዱ ልደት መሆን አለበት >> ይላሉ፡፡
የዚህ ምላሽ
5.1 አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ አቂቃ ማውጣቸው በትክክለኛ ሀዲስ ተዘግቦ አልተገኘም የተገኘው በጣም ደኢፍ በሆነ ሀዲስ ነው /ኢስትአይብ የኢብኑ ዐብዱልበርን ሃቪየተል ኢሷባነ እና ሰብለል ሁዳ ወረሻድን ይመልከቱ/ ስለዚህ ደኢፍ የሆነ ማስረጃ መቁጠራቸው ተገቢም ትክክልም አይደለም፡፡
5.2 አቂቃን ለምን የልጅ ልደት ብላችሁ ትተረጉሙታላችሁ ይህንንስ ተፍሲር ያገኛችሁት ከየት ነው ፍፁም የተለያዩ ናቸው፡፡ አቂቃ የልጅ ልደት ነው ብላችኋል ልደት በየዓመቱ ማክበር ይቻላል ካላችሁ አቂቃ ለምን ሁለቴ አይደረግም የሚገርመው ነገር አቂቃ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲወጣ ስለተደነገገ ሁለት ጊዜ አይደረግም ካላችሁ በኋላ በጭራሽ አንድም ጊዜ ያልተሰራውን መውሊድን በየዓመቱ ሲላችሁም ለወራት ደጋግማችሁ ማክበራችሁ ነው አስተውሉ
5.3 ነብዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ለራሳቸው አቂቃ አወጡ ተብሎ የተገለፀው ሐዲስ
* / በእርግጥ ሐዲሱ ውዝግብ አለበት፡፡ በርካታ ዑለማዎች ሰነዱ ደካማ ይገልፃሉ/ ለመረጃነት አይበቃም እንደምትሉትም የኹኛው አቂቃ ”መውሊድ ” ቢሆን ኖሮ ለምን በየአመቱ አልደጋግመውም፡፡
6. ሌላው ጠንካራ ማስረጃችን ብለው ከቁርዓን የሚጠቅሱት / የመልእክቱ ትርጉም/
 ”በአላህ ችሮታና በእዝነቱ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ እርሱ ከሚሰበስቡት /ሃብት/ በላጭ ነው በላቸው፡፡ ”
” ራሕማ” ብሎ አላህ በዚህ አንቀፅ ላይ የጠራቸው ነቢዩን /ሰ.ዐ.ወ/ ነው ነቢዩን / ሰ.ዐ.ወ/ ራህማ ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡ ስለዚህ በራህማ /በነቢዩ ሰ.ዐ.ወ/ እንደሰታለን ይላሉ፡፡
የዚህ ምላሽ
6.1- በሙፍሲሮች ዘንድ በዚህ አንቀፅ ”ራሕማ ” የተባለው ከዚህ በፊት ባለው አንቀፅ መሠረት ”ቁርዓን ” ነው አንዳንዶቹ ”ኢስላም ” ብለው ነው የፈሰሩት፡፡ ”ራሕማ ” የነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ መልእከተኛ ሆነው መላክ ነው ብለው የፈሰሩ ሰዎችም አሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ በነቢዩ መደሰት አስፈላጊ ነው፡ ሰሃቦች ከማንኛችንም የበለጠ በረሱል ይደሰቱ ነበር። ነገር ግን ይህንን ደስታቸውን መውሊድን በማክበር አልገለፁትም መደሰት የሚገልፀው በአመት አንዴ / በረቡዕ 12/ በመፈንጠዝ አይደለም፡፡
6.2- አላህ /ሱ.ወ/ በቁርዓኑ ውስጥ ለነቡዩ /ሰ.ዐ.ወ/ የዋለላቸውን ውለታና ያጎናፀፋቸውን የተለይዩ ፀጋዎች አውስቷል፡፡ ኢስራዕ እንዳስደረጋቸው ለሙእሚኖች ነቢይ አድርጎ እንደላካቸው እና ሌሎችንም በርካታ ፀጋዎችን ያወሳል፡፡ ውልደታቸውም ቢሆን በዚህ መልኩ ባይጠቀስም ታላቅ ፀጋ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ውልደታቸው ፀጋ አይደለም ለማለት ሳይሆን እነዚህን አላህ /ሱ.ወ/ የተመፃደቀባቸውን ታላላቅ ክስተቶች በየዓመቱ እንዲከበሩ ሳይለነገግ መውሊድን ማክበር እንዴት የተደነገገ ይሆናል?


7 - አቡለሀብ የተባለው የነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ አጎት ሱይወባ የተባለች ባሪያው የነቢዩን /ሰ.ዐ.ወ/ መወለድ ስትነግረው ነፃ አወጣት፡፡
ምላሽ
ሱይወባን አቡለሀብ ነፃ ያወጣት ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ሲወለዱ ሳይሆን ወደ ሂጅራ ከመሄዳቸው በፊት ነው ኹዲጃ ሱይወባን እንዲሽጥላቸው አቡለሀብን ለምነውት ነበር እሱ ግን አልተስማማም ነቢዩ/ሰ.ዐ.ወ/ መዲና ሆነው መልዕክት ይልኩላት ነበር፡፡ ይህንንም ኢብኑ ኢስሃቅም ሌሎችም ዘግበውታል፡፡  በዚህም ምክንያት አላህ/ሰ.ወ/ ሰኞ፤ሰኞ ቅጣቱን ይቀንስለታል ይህም በቡኹሪ ተዘግቧል ይላሉ፡፡
የዚህ ምላሽ
7.1 ቡኹሪ ላይ የተጠቀሰው በዚህ መልኩ አይደለም ይህ የአቡለሃብ ጉዳይ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በሕልም የታየ ነው እንጂ አንዳንዶች አባስ የነቢዩ አጎት ከመስለማቸው በፊት ያዩት እንደሆነ ይናገራሉ ይህንንም ክስተት ያወራው አንድ የሐዲስ አስተላላፊ ነው እንጂ ነቡዩ አይደሉም፡፡
7.2 የነቢዩ ንግግር ቢሆን ኖሮ እንኳ ይህንን ነገር በማፅደቅ መውሊድን ካልደነገኑት በስተቀር ይህ ተራ ክስተት ያውም በጃሂሊያ ጊዜ የተፈፀመ መውሊድ ለማክበር በምንም መልኩ መረጃ አይሆንም፡፡ በአል ማለት ደግሞ ተደጋግሞ የሚመጣ ነው እንጂ አንድ ግለሰብ ስሜቱን ለመግለጽ ለብቻው የፈፀመው ተግባር አይደለም፡፡
7.3 ይህ ሕልም ከቁርአን ጋር ይጋጫል አላህ ለሙሽሪኮች ምንም አይነት የቅጣት ቅነሳ እንደማያደርግ ሲገልፅልን እንዲህ ይለናል፡፡
 ” እነዚያን የካዲትም ለነርሱ የገሃነም እሳት አላቸው ይሞቱ ዘንድ በነሱ ላይ /በሞት/ አይፈረድም ከቅጣቷም ከነሱ አይቀለልላቸውም እንደዚሁ ሁሉን ከሀዲ እንመነዳለን፡፡ ” ቁርዓን 35-36
እውነታ ከናልም ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡ ህልም ሻሪዓው ህግ አይገነባበትም በተለይም ይህ ህልም፡፡
<<መውሊድ ምን አጠፋ?  ብዙ ሰለዋት እንድናደርግ ይገፋፉናል የነቢዩን /ሰ.ዐ.ወ/ ታሪክ ለማስተማር እድል ይከፍታል ሰደቃ እንድናበላ ያደርጋል ስለዚህ የጥሩ ነገር በር ከፋች ስለሆነ አትዋጉት፡፡>> ይላሉ
የዚህ ምላሽ
8.1 ሰለዎት ሰደቃ ዚክር እና የመሳሰሉት ኢባዳዎች አመቱን ሙሉ ያለገደብ እንዲፈፀሙ በነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ የተደነገጉ ናቸው፡፡ ረሱልም /ሰ.ዐ.ወ/ ለእነዚህ ብዙ መንገዶችና እድሎችን አመቻችተውልናል ለምሳሌ ያህል ”በጅምአ ቀነ ሰለዋት በእኔ ላይ አብዙ የናንተ ሰለዋት እኔ ፊት ትቀርባለች ሌላም አዛን በምትለው ጊዜ ሙአዚኑ እንደሚለው በሉ እኔም ላይ ሰለዋት አብዙ በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርድበታል፡፡ ”
      እነዚህንና የመሳሰሉ እድሎችን ከተጠቀምን ትልቅ ነገር ነው፡፡ “በአመት አንድ ጊዜ” ብቻ መገደቡ ለምን አስፈለገ ?
8.2 ስለ መውሊድ ጥሩ ጎን ነው ያላችሁትን ትናገራላችሁ በጣም ብዙ የከፋ ተግባሮችን ግን ትደብቃላችሁ እስከ ሽርክ የደረሱ ወንጀሎች እየተፈፀሙበት መሆኑን ከላይ ለማየት ሞክረናል ቅድሚያ ሰጥታችሁ ማየት ያለባችሁ ካመጣው ጥቅም ይልቅ ያሰረሰውን ጉዳት ነው ምክንያቱም ዑላማዎች ያፀደቁት መርህ አለ፡፡
“ጥሩውን ነገር ከማምጣት መጥፎውን ነገር መጋፋት ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡”ስለዚህ ጉዳቱን መጀመሪያ ተመልከቱ፡፡
8.3 የነቢዩን /ሰ.ዐ.ወ/ ታሪክ ለመማር በዓመት አንድ ቀን ብቻ በቂ አይደለም እውነት ነብዩን /ሰ.ዐ.ወ/ ከወደድን ታሪካቸውን በየዕለቱ ጊዜ ሰጠተን እንማር
9. <<ለመውለድ የታረደ ምግብን ለምን አትበሉም ? አላህ ግዴታ አድርጎባችኋል ካልበላችሁ እንደሚቆጣባችሁ በቁርአን እንደዚህ ተገልጿል>> ይላሉ
“በአንቀፆቹም አማኞች እንደሆናችሁ /ሲታረድ/ የአላህ ስም በርሱ ላይ ከተወሳበት / እንስሳ/ ብሉ”ስለዚህም በመውሊድ በአል ላይ በመገኘት ለበዓሉ የታረዱ ምግቦችን መብላት አለባችሁ ይላሉ፡፡
ለዚህ ምላሽ
9.1 ከላይ የተጠቀሰው የቁርአን አንቀጽ የወረደው ሰሃባዎች እርድን ለመብላት በፈሩ ጊዜ ጥርጣሬያቸውን ለማንሳት ነው፡፡ ይህም ቢሆን የሚያመለከተው መፈቀድን እንጂ ግዴታ አይደለም ግዴታ ያልሆነን ነገር ግዴታ ማድረጉ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡ ለዚህ አንቀጽ ማብራሪያ
      * ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ኢብኑ ጀሪር አጠበሪ ፈትሁል ቀዲር የመሳሰሉት መመልከት ሃቁን ያስረዳል፡፡
9.2 እኛ በአላህ ስም የታረደን አንበላም አላልንም፡፡ ነገር ግን መውሊድ ነቢዩ ያልሰሩት ተግባር በመሆኑ ማነኛውንም መሰረት የሌላቸው ኢባዳዎችን እንድንነቅፍ ታዝዘናል፡፡
  ”ያልታዘዙትን የሚሰሩት ከቻላችሁ በእጃችሁ በምላሳችሁ ወይም በልባችሁ ታገሏቸው” ተብለን ታዝዘናል
ሰሂህ ሙስሊም እንደዘገቡት
10. <<የአዝሃር ዑለማዎች በሙሉ ድምፅ አፅድቀውታል በሃገራችንም የተቋቋመው የዑለማዎች የጋራ መድረክም እንዲከበር ወስኗል ስለዚህ መውሊድ ይፈቀዳል>> ይላሉ
የዚህ ምላሽ
10.1 አዝሃሮችንም ይሁን የጋራ መድረኩን መመሪያ አድርጎ መያዝ ተገቢ አይደለም አዝሃሮች በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ቸልተኝነት የሚታወቅ ነው፡፡ የሰይድና ሁሴንን አና ዘይነብን ቀብር የሚያመልኩትን አንኳን በግልፅ ተቅውሞ አያሰሙም የሁሉም አቋምና ተግባር ማስረጃ አይሆንልንም፡፡ ሰዎች በሀቅ ይመዘናሉ እንጂ ሀቅ በሰዎች አይመዘንም፡፡
10.2 ከላይ የተዘረዘሩት መልሶች አዝሃሮችንም ይመለከታል፡፡ እነሱ ከቁርአንና ከሐዲስ በላይ አይደሉም ወደ አላህ የምንቀርብባቸውን የአምልኮ ዘርፎች ከአላህና ከነቢዩ/ሰ.ዐ.ወ/ ውጭ ማንም ቢሆን የመደንገግ መብትና ሥልጣን የለውም፡፡ ነቡዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ካልሰሩት ሰሃባዎች ካልሰሩት የሦስቱ ምርጥ ክፍለ ዘመናት ሙስሊሞች ካልሰሩት እንዴት እና ዲን ብለን እንስራው አንዳንድ የተሳሳቱ ምሁራን ስለሰህረት ብቻ ኢስላም እንደ ሰው ሰራሽ ሕግጋት በጉባኤ የሚወሰን አይደለም ይህ ደግሞ የነሳራዎችና የአይሁዶች መንገድ ነው፡፡
10.3 አዝሃሮች በሙሉ ድምፅ አፅድቀውታል የተባለውም ትክክል አይደለም፡፡ ከቀደምት የአዝሃር መሪዎች መካከል መሀመድ እብዱ ሸዋህ መራሪ ዓሊ ማሕፉዝ ሀሠነይን መኺሉፍ እና የመሳሰሉት መውሊድን በግልፅ ተቃውመዋል፡፡ ከአሁኖቹ ምሁራንም ሸይህ መሀመድ በረካት አብድልአዚመን መጥአኒ አብዱልመንአመልበሪይ የመሳሰሉትም በግልፅ ተቅውመዋል፡፡
10.4 የሀገራችን ዑለማዎች የጋራ መድረክ ስምምነትን በተመለከተ የሰዎች ስምምነት ግልፅ ከሆኑ መረጃዎች ጋር እስከተጋለጡ ድረስ ቦታ አይኖረውም በመረጃ ባልተደገፈ መልኩ አክብሩ ቢሉ ተቀባይነት አይኖረውም በጋራ መድረክ በመታቀፍ ፊርማቸውን ያኖሩ ሰዎች ብዙ እንደሆኑ ሁሉ ብዙዎችም የተቃውም ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ እንደሚታወቀው በዘጠኝ ክልሎች የሚገኙ የሙስሊም ተወካዮች ስምምነቱን በመቃወም መግለጫ አውጥተዋል፡፡
11. <<መውሊድ ብናከብር በምን አለበት? ለምስጋና ብለን ነው የምናከብረው>> ይላሉ፡፡
ለዚህ ምላሽ
                  አንድ ሰው አል-ኢማሙማሊክ ዘንድ መጥቶ” ከየት ነው ኢሕራም የማድርገው?” ሲላቸው ”ረሱል ከሰሩበት ከዙል ሁለይት” አሉት፡፡”እኔ የምፈልገው ከቀብራቸው መሀረም ነው ” አላቸው እሳቸውም ”አታድርግ ፈተና እፈራለልሀለሁ”አሉት፡፡ ”ይህ ምን ፈተና አለበት? ” ሲል ጠየቃቸው በመቀጥልም ”ጥቂት ርቀት እኮ ነው የጨመርኩት” አላቸው ”ረሱል ያልደረሱበትን መልካም ስራ በመስራት ቀዳሚ መሆንህን ከማሰብ የበለጠ ምን ፈተና አለ? ”አሉና የሱረቱ ኑርን አንቀፅ 24-63 ጠቀሱለት፡፡
      ”ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡ ”
12. ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ መውሊድን ማክበር አጅር /ምንዳ/ ያስገኛል ብለዋል፡፡
ለዚህ ምላሽ
12.1 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ለንግግራቸው ከቁርአንና ከሱና መረጃ ይፈለግለታል እንጂ ንግግራቸው ብቻ በራሱ መረጃ ተደርጎ አይወሰድም፡፡  
12.2 ሸይኹል ኢስላም የተናገሩት እንዲህ በማለት ነው፡፡ ” አንዳንድ ሰዎች መውሊድን ያለቃሉ እንደ በዓልም ያከብሩታል ይህንን የሚያደርጉት ከመልካም ኒያና ረሱልን ከማላቅ የተነሳ ነው በዚህም ኒያቸው ታላቅ ምንዳ ያገኙበትል፡፡
* አቅቲዷኡ ሲራጥ አል-መስተቂም ገፅ 297
ንግግራቸውን ስናጤነው -ስለ ተግባራቸው ሳይሆን ስለ መልካም ኒያቸው ነው ምንዳው፡፡
12.3 እኚህ ታላቅ አሊም ንግግራቸውን በዚህ መፅሐፍ ላይ ግልፅ አድርገውታል፡፡
 ”እንደዚሁ አንዳንድ ሰዎች ክርስቲያኖችን በኢሳ ልደት በመፎካከር ወይም ለነቢዩ/ሰ.ዐ.ወ/ ካላቸው ውዴታ በመነሳት የሚፈጥሩትን /ቢድዓ/ በተመለከተ አላህ ስለ ውዴታቸውና ጥረታቸው ሊመነዳቸው ይችላል፡፡ በቢድዓው ግን አይመነዳቸውም፡፡”
አቅቲዲኡ ሲራጥ አል-ሙስተቋም ገፅ 294
12.4 ለክርክርም ሆነ ለንትርክ ምንም በር በማይከፍት መልኩ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ  ተይሚያህ በመፅሐፎቻቸው በተለያዩ ቦታዎች ላይ መውሊድ ማክበር እንደማይፈቀድ ተናግረዋል፡፡
ይኹውም፡- ”የበዓል ወቅት ተደርጎ ያልተደነገገን በዓል አድርጎ መውሰድ ለምሣሌ በረቢዑል  አወል የመውሊድ ሌሊት ተብሎ እንደሚከበረው ዓይነት ሁሉም የዚህ ኡማህ አበው ትውልዶች መልካም አድርገው ያላዩትና ያልሰሩት የቢድዓ ተግባር ነው፡፡ ”
አል-ፈታዋ 25/298


Post a Comment

1 Comments

  1. ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ አቅቲዷኡ ሲራጥ አል-መስተቂም ያሉትን፤ መውሊድ ማክበርን በምንም መንገድ ማስረጃዎችን አንሻፎ ለመከራከር የሚፈልገዉም፤ መውሊድ ማክበር አይፈቀድም ብሎ የሚከራከረዉም ወገን፤ ሁለቱም የሳቱት ሸይኹል ኢስላም የፊቅህ እይታ፤ በመውሊድ ጥያቄ ሙስሊሞች በመሐከላቸው ጥላቻና መከፋፈልን እንዳይፈጥሩ የሚለዉ ነው!!! በሐገራችብ ተጨባጭ ተውሒድን እና ሰላት አስተካክሎ መስገድ ከማይችሉ መሓይማን ሠዎች ጋር በመውሊድ ጥያቄ ዉዝግብ ዉስጥ በመግባት (ከልካ ወገንዩ ነብዩን አይወድም የሚል እንድምታ በጭንግላታቸው ዉስጥ በመፍጠር)፤ የቀን ጅቦች ለሆኑት ለአሕባሽና የአክፍሮት ሐይሎች ሙስሊሙን ከፋፍለው ለማጥቃት የሚያስችል ክፍተት ባለማወቅ ይፈጥራል!!!

    قال صلى الله عليه وسلم : من يرد الله به خيرا ; يفقه في الدين

    ReplyDelete