Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለመውሊድ የታረደን ዕርድ ስጋ መብላት ?

ለመውሊድ የታረደን ዕርድ ስጋ መብላት ?
ጥያቄ:- ለመውሊድም ሆነ ለሌሎች የልደት በዓላት የታረደን ስጋ መብላት ይቻላልን?
መልስ:- ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ሆነ ለሌላ ወሊይ (ደጋግ ሰዎች) ለልደታቸው ቀን እነሱን ለማላቅ ተብሎ የእርድ እንስሳን መሰዋት (ማረድ) ፍርዱ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ማለት ነው ። ይህም ማለት ሸርክ (ከአላህ ውጪ በአምልኮ አጋር ማድረግ) ነው ። በመሆኑም ከነዚህ (መስዕዋት) ከቀረቡ እንስሶች መብላት አይፈቀድም ። ጤነኛ በሆነው ሐዲስ ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተዘገበው {{ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ያረደ አላህ ረግሞታል }}
አላህ ለስኬት ያብቃን ። በአላህ መልዕክተኛ ሙሀመድ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሰላምና ሰላት ይውረድ ።
( የዑለማዎች ጥናትና ፈታዋ ቋሚ ኮሚቴ ( ዐብዱላህ ኢብን ጙዳያን ፣ ዐብዱረዛቅ አፊፊ ፣ ዐብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝ ) ፈታዋ ቁጥር 10685 )
______________
ጥያቄ:- ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የልደት ቀን የታረደን ዕርድ ስጋ መብላት ይቻላልን ?
መልስ:- ዕርዱ የሚደረገው ልደቱ ለሚከበርለት ወገን (ለረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተብሎ ከሆነ ይሄ ትልቁ ሸርክ ነው ። ነገር ግን ሊበላ የታረደ ከሆነ ግን ችግር የለውም (ሽርክ አይሆንም)። ነገር ግን ሊበላ አይገባውም ። ሙስሊምም ይሄን አይነት አጋጣሚ ሊታደም አይገባውም ። በቃልም በተግባርም ሊቃወማቸው ከሆነ ። ነገር ግን ሊቃወማቸው (እንደማይቻል ሊያስተምራቸው) ከሆነ ሳይቀላቀላቸውና ምግባቸውንም ሳይመገብ ካልሆነ በቀር ።
( ሰማሐቱ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ መጅሙዑ ፈታዋ ቁጥር 9/74)