Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተውሒድና የሱና ወንድሞች ስለእሕታቸው ሒጃብ አይጨነቁም?

« የተውሒድና የሱና ወንድሞች ስለእሕታቸው ሒጃብ አይጨነቁም? »
በአላህ ይሁንብኝ ይሄን የሚከረፋ ውንጀላቹን ሃቅ እንዳልሆነ ከማንም በፊት እናንተው እራሳቹ ጠንቅቃቹ ትረዱታላቹ !
ዛሬ ሕዝብን ተውሒድ ለማስተማር የነቢያትን ዋና አላማ ለማድረስ ደፋ ቀና የሚሉ ወንድሞችና እሕቶች የአንድ ቀፋፊ ጨቋኝ ባለስልጣን ስም አንስተው ይሄው ሰድበነዋል እዩልን ስላላሉ ስለሒጃብ አልተጨነቁምን? ምን አይነት ሂሳብ ነው?
እስኪ እውነት እናውራ ከተባለ የኛ ኪቦርድ ጂሃዲሰቶች በፌስቡክ ላይ ሒጃብ ሒጃብ እያሉ መጮኽ ማንን በጀ? ለማለት በሚከብደኝ ሁኔታ እንደውም ይሄን ዟሊም አባሱበት እንጂ ! እስኪ ቅድሚያ አንቺ የሙስሊሙ ጉዳይ አሳስቦሽ ኮምፒዩተር ላይ የተለጠፍሺው እሕትዋ ቅድመሽ አንቺ ሒጃብሽን አስተካክለሽ ልበሺው ። አንተም የፌስቡክ ዋሪየሩ ኤጭ–ቲሺስቱ ወንድምዋ ስለ ኢትዮጵያ ሙስሊም መጅሊስን ማጣት እንዳሳሰበህ የሴቷም ሒጃብ እንዳስጨነቀህ እስኪ ቀድመህ አጠገብህ ያለችውን የስጋ እሕትህን አስተካክለሽ ልበሺ በላት ። ቤተሰቦችህንም የአሕባሹን ኢማም ጥሪ አክብረው አንዴ ወደ ቃጥባሬ አንዴ ወደ ሸኸና ኑርሑሴን ቀብር ሲጓዙ ተው ይቅርባቹ በላቸው ። ጡንቻህን በፌስ ቡክ ብቻ አትገድበው ። ብሎም ወደ ተውሒድና ሱና የሚጣሩ ወንድሞችና እሕቶች ላይ ምላስህን አትዘርጋ ። እስኪ ወጣ ብለህ ተመልከት ! ሴቷ ሱሪ ለብሳ መጥታ ጅልባብ አድርጋ የምትወጣው ፌስ ቡክ ላይ ይመስልሃልን? በጭራሽ ! አንተ ዛሬ ባለሥልጣን በዚ ወጥቶ በዚ ገባ ብለው ስላልቸከቸኩ የሒጃብ ጉዳይ አያሳስባቹም ያልካቸው ወንድሞችና እሕቶች መድረሳ ነው ። ካንተ cyber ፉከራ የተሻለ መሬት የወረደ ስራ የሚሰሩት እነሱ ናቸው ። ይሄንንም ጠንቅቀህ ሳታውቅ ቀርተህ አይደለም አመል ሆኖብህ እንጂ ። ከሱም ብሶ ለሒጃቧ ብቻ ሳይሆን ወደ ጀሃነም ሊወረውራት ስለሚችለው ሽርክና ቢድዐ ጭምር እንድታውቅ ጥረታቸው ነው ። እንደውም ትናንት የሰፈር ሴቶች አላህ አዝኖላቸው ኒቃብን ቢለብሱ ይሄ የስዑዲ ባሕል ነው ! ሰፋ ቦርቀቅ በሉ የምትሉን የነበራቹት እናንተው አልነበራቹምን ? ዛሬ ኡስታዜ እያላቹ ነሺዳ ያወጣቹላቸው ሰዎች አይደሉም እንዴ ስንት ኪሎሜትር ተሳፍረው ሄደው የክፍልሃገር ውድ እሕቶቻችን ኒቃብ ለብሰው ቢያምርባቸው አውልቁት ይቅርባቹ ብለው አስወልቀዋቸው የመጡት? (አይደለም ያለ ካለ በማስረጃ እመጣለው) ። ታዲያ ዛሬ ምነው ከሃላ የመጣ አይን አወጣ ሆናቹሳ ?
ለማንኛዋም ወዷ እሕቴ መሪ ሄዶ መሪ ይተካል ። ንጉሳዊው ሄዶ ሶሻሊስቱም ተተክቷል ኮሚኒስቱ ሄዶ ዲሞክራቱ መጥቷል ። ላንቺ ነፃነትን የሚሰጥሽ የማርክና ሌኒን ወይንም የፍራንኮ ህግ አይደለም ! ነፃነትሽ በእጀሽ ነው ። ነፃነትሽ ከጌታሽ ዘንድ የመጣልሽ ኢስላም ነው ። ኢስላም ሒጃብን ልበሺ ይልሻል ። እሺ ብለሽ ተቀበይ ። ነፃነትሽን ለማንም አሳልፈሽ አተስጪ ።
የናንተ ኤጭ _ቲሺስቶች ጉዳይ ግን .....

ስለመውሊድ ተፃፈ ውስጡ ሽርክና አለ ውስጡ ቢድዐ አለ ሲባል እናንተ የሒጃብ ጉዳይ የማያሳስባቹ !
ስለ መንዙማ ተፃፈ ውስጡ ሽርክና አለ ውስጡ ቢድዐ አለ ሲባል እናንተ የሒጃብ ጉዳይ የማያሳስባቹ !
አረረ ክሳችንን ለከት ይኑረው
አረረ አድብ እንያዝ
ﻧﺴﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﻌﺎﻓﻴﺔ ﻭﺍﻟﺴﻼﻣﺔ

Post a Comment

0 Comments