Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙሀመደ ረሡሉላህ ብሎ የምሥክርነት ቃሉን የሠጠ ሠው መውሊድን ሊያከብር አይገባውም!!!


ሙሀመደ ረሡሉላህ ብሎ የምሥክርነት ቃሉን የሠጠ ሠው መውሊድን ሊያከብር አይገባውም!!!

☞ ምክንያቱም ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ ሢመሠክር እነዚህን አራት ነገሮች አምኖ ሊቀበል ፣ በምላሡ ሊናገር እና በሠውነት ክፍሉ አምኖ ሊቀበል የግዴ ነው

1,ረሡል ሠለላሁ ለይሒ ወሠለምን መውደድ. እሣቸው የአላህ
መልዕክተኛነታቸውን የመሠከረ ሠው እሣቸውን መውደዱን በልቡ ሊያምን በምላሡ ሊናገር እንዲሁ እሣቸውን መውደዱን በሠውነት ክፍሎቹ እሣቸውን በመመሣሠል ውዴታውን ማመላከት የግድ ነው በምላስ ብቻ አበድኩሎት ፣ ሞትኩሎት ምናምን እያሉ እየተነሡ በመፍረጥ የነብዩ ውዴታ ሊገለፅ አይችልም የነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ውዴታ የሚገለፀው እሣቸውን በመከተል ብቻና ብቻ ነው አላህ እንዲህ ይላል

"አላህን እምትወዱ ከሆነ እኔን ተከተሉኝ እሡም ይወዳቹሀል በላቸው "

☞ እውን እኛም ነብዩን የምንወድ ከሆነ በዚህች አንቀፅ እንመዘናለን ነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የምወድ ከሆነ ያልሠሩትን አንሠራም የጠሉትን እንጠላለን የወደዱትን እንወዳለን እሣቸው ደግሞ ቢድአ አይወዱም እንደማይወዱም ተናግረዋል ስለዚህ ከሣቸው እውነተኛ ፍቅር ከያዘን መውሊድን አናከብርም

2,የከለከሉትን መከልከል አሁንም ምሥክሩን የሠጠ ሠው መልዕክተኛው የከለከለውን ነገር ሊከለከል የግድ ነው
ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ቢድአ (መጤ) የሆኑ ነገሮችን ከልክለዋል

☞ "ሁሉም ቢድአ ጥመት ነው "
" የኛትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ወደራሡ ተመላሽ ነው "

☞ ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ስለ ቢድአ በግልፅ እንዲህ ካሉ መውሊድን የሚያከብር ሠውለነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የሠጠውን ቃል ሊፈትሽ ይገባዋል!!!

3,ያዘዙትን መታዘዝ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እሣቸውን እና የቅን
ምትኮቻቸውን ሡና አጥብቀን እንድንይዝ አዘውናል

" ከናንተ መካከል የሚቆይ ሠው ብዙ ልዩነቶችን ያያል የዚኔ አደራችሁን ሡናዬን እና የተመሩ የሆኑ የቅን ምትኮቼን ሡና አጥብቃቹ ያዙ "

☞ መውሊድ የሚያከብር ሠው ግን የነብዩን እና የሠለፎችን መንገድ ትቶ የነማንን መንገድ እየተከተለ እንደሆነ እሪሱን ይጠይቅ!!!

4,አላህን በሚገዛበት ግዜ መልእክተኛው መሆናቸውን የመሠከረላቸው ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በደነገጉት መንገድ ብቻና ብቻ ሊሆን የግድነው

"መልዕክተኛው ያመጣላችሁን ያዙት ከከለከላችሁም ተከልከሉ "

☞ መውሊድን ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዳልደነገጉት ማንም ሠው አስረግጦ ያውቃል ታድያ እሳቸው ያልሠሩትን ለመስራት ምን አነሣሣን??? ውዴታ?? ይሄማ አይሆንም!! ውዴታ እንዴት በአመፅ ይገለፃል አበቃው