Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላማዊዎቹ (ተብዬዎች) በኢስላም

ኢስላማዊዎቹ (ተብዬዎች) በኢስላም
ምስጋና ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ጨለማዎችንና ብርሃንን ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው ከዚያም እነዚያ የካዱት (ጣኦታትን) በጌታቸው ያስተካክላሉ እርሱ ያ ከጭቃ የፈጠራችሁ ከዚያም (የሞትን) ጊዜ የወሰነ ነው እርሱም ዘንድ (ለትንሳኤ) የተወሰነ ጊዜ አለ ከዚያም እናንተ (በመቀስቀሳችሁ) ትጠራጠራላችሁ እርሱም ያ በሰማያትና በምድር (ሊገዙት የሚገባው) አላህ ነው ሚስጥራችሁን ገልጻችሁንም ያውቃል የምትሰሩትን ሁሉ  ያውቃል (አል-አንአም 1-3)
ምስጋና ለአላህ  (ሱብሀነሁ ወተአላ) ይግባው እርሱን ብቻ እንግገዛለን፡፡ እርሱን ብቻ እናወድሳለን ከርሱም እርዳታ ምህረት ይቅርታንና ጥበቃን እንለምናለን ከነብሳችን ክፋትና ከምንሰራው ክፉ ነገር ሁሉ በአላህ እንጠብቃለን አላህ ቀጥተኛውን መንገድ የመራውን ሰው ማንም ፈጽሞ ሊያጣመው አይችልም፡፡ እርሱ በጥመት ውስጥ የተወውን ሰው ደግሞ ማንም ሊያቀናው አይችልም፡፡ ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመላክ የሚገባ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፡፡ መሀመድም (ሰለላሁ አለይኒ ወሰለም) የአላህ ባሪያና መልእክተኛው መሆናቸውንም እመሰክራለሁ የአላህ ሰላም እዝነትና በረከት በርሳቸው በቤተሰቦቻቸው በባልደረቦቻቸውና የርሳቸውን ፈለግ በቅንነት በሚከተሉት ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ 
ከዚህ በመቀጠል አላህ (ሱብሀነሱ ወተአላ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል ከሰዎች ያለ እውቀት ሆኖ ከኣላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለል እነዚያ ለነሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው ሱረቱል ሉቅማን 6
አላህ (ሱብሀነሱ ወተአላ) ለዚህ ኡማ ከሰጠው ፀጋ ሁሉ በቀጭ የሆነው ፀጋ የእስልምና ፀጋ ነው የዚህን ፀጋ ፍሬ የሚታደሉት ደግሞ እርሱ ከከለከላቸው የተከለከሉ እንዲሁም በታዘዙት ነገር ላይ ታዘው የተገኙት ብቻ ናቸው፡፡ አላህ (ሱብሀነሱ ወተአላ) እንዲህ ይላል፡፡
ከእናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ  ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡
መልእክተኛው የሰጣችሁን ነገር ያዙት ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ አል ሀሽር 7 ከላይ እንደተመለከትነው በሱረቱል ሉቅማን አላህ (ሱብሀነሱ ወተአላ) ለህወልሀዲስ ብሎ የጠቀሰውን አብደሏህ ኢብን መስኡድ አላህመልካም ስራውን ይውደድለት ዘፈን መሆኑን ሶስት ጊዜ በመሀላ አስረግጠው ተናግረዋል ከርሳቸውም ውጪ ሌሎች ሰሀባዎችእንዲሁም ታብኢዮችም በዚህ ላይ አንድ አቋም አላቸው ከእነርሱም ውስጥ አብደላህ ኢብኑ አባስ አብደላህ ኢብኑ ኡመር፣ ጃቢር ኢብኑ ኡመር ይገኙበታል የሰሀባዎች ንግግር በቁርአን ትርጉም ላይ ማስረጃ ነው ምክንያቱም ከሌላው በበለጠ የቁርአንን ትርጉም የሚያውቁት እነርሱ ናቸው፡፡ ቁርአን ሲወርድ የነበሩ ከመሆናቸውም በላይ እያንዳንዱ የቁርአን አንቀጽ ሲወርድ በቅርብ የተመለከቱ የወረደበትን ሁኔታ የሚያውቁ በቂ እውቀትና ግንዛቤን ከመልክተኛው በቀጥታ የጨበጡ ናቸው፡፡ ከነርሱም በመቀጠል ታብእዮች (ከሰሀባዎች ቀጥሎ የመጡ ትውልዶች) በአንድ የቁርአን አንቀጽ ላይ ከተጋጠሙ ለማስረጃ በቂ ይሆናል ከነዚህም ታላላቅ የታብእይ ሊቃውንት መካከል ሙጃሂድ፣ ኢቡኑ ጃቢር፣ ኢክሪማ፣ ሀሰኑል በስሪይ ሰኢድ ኢብኑ ጁበይር፣ ቀታዳ አብኑ ዱአማ፣ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ ሁሉም ባጠቃላይ ለህወል ሀዲስን ዘፈን በማለት ተርጉመውታል፡፡
  የኢስላም ስም እየተለጠፈላቸው ለኢስላም ስም ሙስሊሙን ወደ ጥመት እየመሩ የሙስሊሙን ቀልብ እያደረቁ የአላህን ፍራቻ ከሰው ቀልብ እየገፈፉ በዚህ እኩይ ተግባር ላይ በመሰማራት ኢስላማዊ ነሺዳ መንዙማ፣ ፊልም በማለት ኪሳቸውን የሚያደልቡ አላዋቂዎችን ኢብነል ቀይም እንዲህ ሲሉ ይገልጻቸዋል፡’’ የኢልምን ሽታ ለቀመሰ ሰው የዘፈንን ሀራምነትቅንጣት  ያህል እንክዋን ሊጠራጠር አይገባውም፡፡ ቢያንሰ ዘፈን የፋሰቆች (የጋጠ ወጦች) እና የሰካራሞች መለያ ነው ዘፈን የዚና (የዝሙት) መወጣጫ መሰላል ነው፡፡የኒፋቅ ማብቀያ የሰይጣን መጋረያ የአዕምሮ መሸፈኛ ከቁርዓን ከልካይ ነው፡፡(ኢጋሰቱን ሉህፋን) ለአላህ (ሱብአነው ወተአላህ) ምስጋና ይግባውና ለአንዳንዱ ቢዳአና ሙብተዲእ በቂ ምላሾችን ያዘሉ ታላላቅ ኡለሞችን አስነስቷል ከእነዚህ ታላላቅ ኡለማዎች መካከል የዘመናችን ታላቅ ሙሀዲስ መሀመድ ነስሩዲን አልባኒ ይገኙበታል፡፡ እኚህ ታላቅ ሙሀዲስ አስኢለቱል ኢማራቲያ በሚለው ከሴታቸው ቁጥር ዘጠኝ ላይ ሰለዚህ ተግባር ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ እንዲህ ይነበባል፡፡
ጥያቄ ኢስላማዊ ፊልም በማየት ላይ ያሉት አስተያየት ምንድን ነው በተለይ ሙስሊም  በሀይማኖቱ ላይ እንዲጠናከር ተጽእኖ የሚያደርጉትን እንደ (ሪሳላ) የሚባለው የእስልምና ጥሪ ጅማሬን ስርጭት የሚያሳየውን ፊልም መመልከት እንዲት ይታያል መልሶች አይቻልም ከሆነ ምክንያቱ ምንድንነው፡፡
መልስ ጠያቂው መልሶት አይቻልም ከሆነ ማለቱ ትክክል ነው ይህ ስራ አይቻልም፡፡ በእስልምና ውስጥ አልተደነገገም (ቦታ የለውም) ለዚህም ብዙ ምክንያቶች አሉ ፡፡ ከእነዚህም ምክንያቶች ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ተግባር የመጣው ከካፊሮች ነው የነሱም መንገድ ነው የነሱ መንገድ ደግሞ የሚገባው ለራሳቸው እንጂ ለሙስሊሞች አይደለም፡፡ ለምን ቢባል ካፊሮች በዲናቸው ውስጥ እስልምና ውስጥ ወደ ጥሩ የሚገፋፋቸው ነገር ስለማያገኙ ወደዚህ ተግባር ለመሄድ ተገደዋል እኛ ግን ለአላህ ምስጋና ይግባው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም  በሀዲሳቸው  ወደ አላህ የሚያቀርባችሁ የሆነን ነገር ምንም አላስቀረባችሁም ብለውናል ስለዚህ ከቁርአን አንድ ሙሉ ስራ (ምእራፍ) አይደለም አንድ አንቀጽ በተበረከላቸው ከብዙ ፊልሞች ያብቃቃቸዋል ከካፊሮች የመነጨውና በእስልምና ላይ አዲስ መጤ የሆነው ይህ ፊልም ወደ ሙስሊሞች ተፈላጊ አይደለም እንዴት አላህ  የፈቀደውን ከሚከለክሉና የከለከለውን ከሚተገብሩ ህዝቦች አካሄዳቸውን አምጥተን ከእስልምና  ነው ብለን እንተገብራለን አንድ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም  በኡመር እጅ (አላህ ሥራውን ይወደድለትና) ወረቀት ይመለከቱና ምንድን ነው በማለት ጠየቁት እሱም አንድ የሁዲ የፃፈልኝ የተውራት ጽሁፍ ያለበት ወረቀት ነው ሲላቸው እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት ሙሳ እንኳ በህይወት ቢኖር እኔን እንጂ ሌላን መከተል አይችልም በማለት  ገለጹ  እስኪ ይህን ሀዲስ እናስተውለው አላህ ያናገረው ታላቁ ነቢይ ሙሳ (አ.ሰ) እንኳን በህይወት ቢኖር ከሳቸው ውጪ መከተል ካልቻለ ታዲያ እኛ ማን ሆነን ነው እነዚህ የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ የሚጻረሩ ሰዎች ላመጡት ሸንጋይ ነገራቶች ተከታይ የምንሆነው እንግዲህ ይህ ነው እስላማዊ ፊልም እየተባለ የሚጠራው ነገር
የማይቻልበት የመጀመሪያ ምክንያት ሁለተኛው የመከልከሉ ምክንያት በዚህ ፊልምና ድራማ በሚባለው ነገር ውስጥ በኢስላማዊ ታሪክ ላይ ውሸት እና እውነታነት የሌላቸው ነገሮች መደባለቃቸው የማይቀር ነው ይሄ ደግሞ አውሮፓውያን ባመጡት ተግባር እንድንከተላቸው ያደርገናል ምክንያቱም እነሱ እንደሚታወቀው የሚጓዙበት  ደንብ አላቸው ሙስሊሞችም በሚያሳዝን መልኩ በዚህ መጥፎ በሆነው “አላማህ ጥሩ ከሆነ መንገዶችህን ጥሩ ያደርጋቸዋል” በሚለው ደንባቸው ላይ ከኋላ እየተከተሏቸው ነው፡፡ ለምሳሌ ገንዘብ ለማግኘት ስራን ሲሰሩ ይህ ስራ ሀራምም ይሁን ሀላል አሳሳቢ አይደለም፡፡ ይህ ተግባር ደግሞ የሀላልና የሀራምን መንገድ ግልጽ ካደረገው የእስልምና ሀይማኖት ጋር ይቃረናል፡፡ ካፊሮች በሚሰሩት ፊልምና ድራማ ላይ እውነታነት የሌላቸው ድርጊቶች ይደባለቃሉ፡፡ እናም የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ እንዳሉት እነሱ በሄዱበት እየሄድን ነው፡፡ እንዴት ቢባል በዚህ ፊልምና ድራማ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ይደበላለቃሉ ታዲያ እስልምና ይህንን ይፈቅዳል? በሌላ በኩል አንድ በተፈጥሮ ጺም ያሳደገ ሙስሊም የካፌሮችን ልማድ በመከተል ጺሙን ይላጨዋል ከዚያም አንድ ሰሀባን ሆኖ ፊልም ለመስራት ይፈልግና ሰው ሰራሽ ጺም አድርጎ ይሰራል፡፡ ታዲያ ይህ ውሸት አይደለም? በመጀመሪያ ደረጃ በመላጨቱ አላህንና መልእክቶቻቸውን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አመፀ ይባስ ብሎ ያለሆነውን ነኝ በማለት ውሸት ይተገብራል፡፡ እንዲሁም በተፈጥሮ ፂም የሌለው ወጣት ሰው ሰራሽ ጺም አድርጎ በዚህ ተግባር ላይ ይሳተፋል እነዚህን ሁኔታዎች ስንመለከት ይህ ኢስላማዊ ፊልም በእስልምና ውስጥ ቦታ የለውም ክልክል ነው አንዱ ያልሆነውን ኡመር ነኝ ሌላዋ ደግሞ የኡመር እህት ነኝ እያሉ ይቀጣጥፋሉ ስለዚህ መሰረቱ በብልሹ ተግባር ላይ የሆነ ስራ  ሁሉ ብልሹ ነው ታላቁ የዘመናችን ሙሀዲስ መሀመድ ነስሩዲን አልባኒ እዚህ ጋር አበቁ፡፡
እንግዲህ የኡለማዎች ምክር ይህን ይመስላል ነገሩ ስሜትን የመከለተል እንጂ ከመረጃ አሳማኝና ግልጽ የሆነ መረጃ ኖሯችው አይደለም ፊልም ነሺዳ መንዙማ የሚሰራው ከላይ የተገለጸው የነዚህ ትግባራት ጦስና መዘዝ ውጪ በሀገራችን ኢስላማዊ ፊልም ተብለው የሚሰሩ እኩይ ተግባራት በየፊልም ቤት የሚከራዩ መሆኑን ለማንም ያልተደበቀ የአደባባይ ሚስጥር ነው ንጹህ አእምሮ ላለው ሰው የኢስላማዊ ፊልም ውጤት ይህ መሆኑ ብቻ ይህ ነገር ኢስላማዊ መሰረት የሌለው ክልክል ተግባር መሆኑን እንረዳለን ጊዜያችን በቁርአን በሀዲስ በሌሎችም መልካም ተግባራት መዋል ሲገባቸው ለነዚህ እኩይ ተግባራት መዋሉ ሙስሊሙ ወዴት እያመራ መሆኑን ያመለክታል ይህም ውርደት ውድቀት የመጣው በዚህ እንጂ በሌላ አይደለም  አላህ ከቢድአና ከሙብተዲኦች ይጠብቀን፡፡
በመጨረሻም ታላቁ ሙሀዲስ እንዲህ ይላሉ ሀቅ ፈላጊ አንድ ማስረጃ ብቻ ይበቃዋል ስሜቱን የሚከተል ግን 1ሺህ ማስረጃዎች አይበቁትም አላዋቂ ከሆነ እንዲማር ይጋብዛል ስሜቱን ከሚከተል ሰው ግን ምንም አማራጭ የለንም፡፡

Post a Comment

0 Comments