Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጫት መቃምን ዲናዊ ተግባር አድርገው ለሚያቀርቡ ወገኖች የተሰጠ ልባዊ ምክር

‎ጫት መቃምን ዲናዊ ተግባር አድርገው ለሚያቀርቡ ወገኖች የተሰጠ ልባዊ ምክር
_______

ማንም ሰው ከመጥፎ ተግባር መላቀቅና
ሸይጣንንም ታግሎ ማሸነፍ ካልቻለ፤ እጅግ አደገኛ በሆነ ቦታ ላይ ወኔ አጥቷልና ሊታዝንለት ይገባል ። ነገር ግን ከወደቀበት መነሳት ስላቃተው መጥፎ ተግባሩን ዲናዊ ካባ በማልበስ ሌሎችንም የሚሞግት ከሆነ ለሰዎች ውድቀትን የሚመኝ ከሆነ እጅግ አሳፋሪ የሸይጣን ወታደር ሆኗል ማለት ነው።

ጫት ከዲን አካል ነው ፣ ሃጃ ያወጣል፣ የሳሊሆች ትጥቅ፣ የወሊዮች ሚስጥር ወዘተ... ነው ያሉትን ወገኖች በተለያየ ጊዜ ስናርምና ሀቁን ስንገልፅላቸው ቆይተናል። አሁን አሁን ግን... በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተሸሙ አንዳንድ አካላት በሚያደርጉት ማበረታቻ ምክኒያት (ጫት የሸሆቻችን ስጦታ ነው፣ አኼራን ያወርሳል፣ ከመጥፎ ያድናል፣ የቃመ ተጠቀመ ያልቃመ ተለቀመ) የሚል ጥሪ ማሰማት የጀመሩ የአህባሽ በቀቀኖችን ማየት ጀምረናል። በጣም ያሳዝናል !!

★ ይህ ዲን የተሟላ ነው። የፈለግነውን የምናክልበት አይደለም ። ማንም ተነስቶ የወደደውን ነገር ከዲን ጋር ማያያዝ የሚቻል ቢሆን ሰዎች ሁሉ ሱስ የሆነባቸው የወደዱት ነገር ስለማይጠፋ ጥሩነቱን በሰበኩ ነበር ። 
'ሸኽ' እገሌ ብለዋል የሚል ፈትዋና  የተለያዩ አፈታሪኮችን ቢደረድሩልህ...
ልቦናህ ግን እውነታውን አንተ ታውቀዋለህ!

★★★ ለመሆኑ ጫት ጠቃሚ ነው ጎጂ? 

ከኢስላማዊ የድንጋጌ መርሆች አንፃር ስንገመግመውስ እንዴት ይታያል?

◆ጫት የሚቅሙ ሁሉ በይፋ እንደሚመሰክሩት ወይም ባይናገሩም እንደሚታወቀው ጫት ጎጂ ነው። ኑሮን ያፋልሳል፣ ማንም ቃሚ ለልጆቹና ለትዳር ጓደኛው አይመኘውም፤ ጎጂ መሆኑ ለሁሉም ግልፅ ነው ። ኢኮኖሚን ይጎዳል ፣ ከዲናዊ ግዴታዎች ያዘናጋል ፣ ተዘርዝሮ በማያልቅ መልኩ ቤተሰባዊ ህይወትን ያዛባል ፣ ማህበራዊ ኑሮ ላይ መገለልን ይፈጥራል ፣ አካላዊ ጉዳቶች አሉት...ያጀዝባል ፣ ብዙ አገራት ከአደንዛዥ ዕፅ መድበውታል ቅጣትም ደንግገዋል።

★★★ ኢስላም ጎጂ ነገርን ማስወገድን ደንግጓል ፤ መሰረታዊ የፊቅህ መርሆችንም..قواعد فقهية ..ስንመለከት ይህንን ያካተቱ መሆናቸውንም እንረዳለን ። አላህ ስለ መልዕክተኛው ሲናገር እንዲህ ይላል፤

قال الله تعالى :(ويحرم عليهم الخبائث) الآية157 

(መጥፎ ነገሮችን ይከለክላቸዋል) አዕራፍ 157

عن أبي سعيد سعد بن سنان الخدري رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال : (لا ضرر ولا ضرار ) حديث حسن رواه ابن ماجة 

ከአቡ ሰኢድ አልኹድሪይ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤
«በዕቅድም ይሁን ካለዕቅድ ጉዳትን ማስከተል አይፈቀድም» ኢብኑ ማጀህ

ስለዚህ ማንም ሰው እራሱን መጉዳት አይፈቀድለትም ሰውን መጉዳትም እንዲሁ ።  ከዚህና መሰል መረጃዎች በመነሳት ዑለማዎች 'ጉዳት ይወገዳል'  الضرر يزال የሚል መርህ አስቀምጠዋል ።

▶ ከላይ ጫት ጎጂ መሆኑን ኣስመልክቶ የጠቀስክዋቸው ነጥቦች ዕውነታውን ለሚቀበል ሰው ሁሉ ግልፅ ናቸው ። 
ስለዚህ ይወገድ !!

★★★ (አምስቱ ታላላቅ ሸሪዓዊ ግቦች)  ኢስላማዊ ህግጋት የተመሰረቱባቸው ዋና ዋና መሰረቶች ናቸው። አምስቱ መቃሲድ ወይንም ኩሊያት አሸሪያ በመባል ይታወቃሉ።

1→ ዲንን መጠበቅ (حفظ الدين)፤ 
በዲን ላይ በዲን ጉዳይ ላይ ጉድለትን የሚያስከትሉ ነገሮችን ሁሉ ከልክሎናል።

2→ ነፍስን መጠበቅ (حفظ النفس)፤ 
ኢስላም ለህይወት ትልቅ ትርጉም ሰጥትዋል ስለዚህም የራስንም ይሁን ሌላ ነፍስ ላይ ጉዳት ማድረስን ከመከልከሉም ባሻገር ይህንን በሚተላለፉ ላይ ቅጣትን ደንግጓል።

 3→ አዕምሮን መጠበቅ (حفظ العقل)፤  አዕምሮ፤ አንድ ሰው ሃቅ እና ባጢል የሚለይበትና የተጠያቂነት ሃላፊነትን እንዲሸከም የሚያደርግ ነው። ስለዚህም ሸሪዓ አዕምሮን የሚያውኩ ንጥረ ነገሮችን ከልክሏል፤ ዲንን ከምንጩ መማርን ሲያዝ፤ ሃቅን ከማወቅ ሰዎችን በመጋረድ ዕውነትና ሃሰትን ከሚደባልቁ መርዘኞች መራቅን ደንግጓል።

4 → ዘርና ክብርን መጠበቅ (حفظ النسل)፤ ኢስላም፤ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማሳመር ክብርን እና ዘርን የሚያስጠብቁ ድንጋጌዎችን አቅፎዋል። የወንዶችንና የሴትቶችን ልቅ ግንኙነት ከልክሎ ቤተሰባዊ ህይወትን ቀርፆዋል።

5 → ገንዘብን መጠበቅ (حفظ المال) ፥ 
ገንዘብ የአላህ ስጦታ ነው ፤ ኢስላም ገንዘብ የሚመጣባቸውን እና የሚወጣባቸውን መንገዶች ስርዓት አስይዞዋል፤ ስለዚህም ወለድንና ማጭበርበርን ከልክሏል፤ ሃራም ነገር ላይ ገንዘብ ማውጣትን እና ገንዘብን ማባከንን ከልክሏል ።

▶ ከሁሉም በላይ ለሙስሊም ትልቅ ቦታ ያለው (ጊዜ) ነው ። ጊዜን ማባከን እጅግ አስወቃሽ ተግባር ነው። 

ኢስላም ባጠቃላይ ጉዳትን ከልክሎዋል ። እነዚህን ነጥቦች ካስተዋልን፤ ጫት መቃም ከመሰረታዊ የዲን መርሆች እና ግቦች እንደሚጋጭና ግልፅ ይሆንልናል ።

 ስለዚህም ወንድሞቼ ፣ በአላህ በመታገዝ ከጫት ተላቀቁ::ኢኒ ለኩም ናሲህ! 

ከጫት ብትላቀቁ:- 

◆ አዕምሯቹሁን ትጠቀሙበታላቹህ፤
ተስፋን ከማሳደድና ከምርቃና ህይወት ወጥታችሁ ደስተኛና በፕሮግራም የሚመራ ህይወትን ትጀምራላቹህ። አዕምሮዋቹህ በተሻለና በተረጋጋ ሁኔታ ማሰብ ይጀምራል:: 

◆ ዲናዊ ሃላፊነቶችን ባማረ መልኩ ትወጣላቹህ፤ ለአላህን ውዴታና ሽልማትም እራሳችሁን ታዘጋጃላችሁ፤ የኢባዳን ጥፍጥና ታጣጥማላችሁ።

◆ ከብክነት ትርቀላችሁ፤
ነፍሳችሁንም ከብክነትና አላማቢስነት ብሎም በጫት ከሚደርስባችሁ የጤና መታወክ ትጠበቃላቹህ::
 
◆ ክብርን ትጎናፀፋላችሁ፤ 
ወደ ሚስታችሁ እና ልጆቻቹህ በመዞር የረሳችሁትን ወይንም የማታውቁትን አስደሳች ቤተሰባዊ ህይወት ታጣጥማላቹህ::

◆ ገንዘብና ጊዜን በማትረፍ እና በአግባቡ በመጠቀም ዕድሜያችሁን በስኬት የተሞላ ታደሩታላችሁ::

▶ አላህ ሁሉንም ቃሚዎች ዕውነታውን ለማስተዋል የልብ ብርሃን ይቸራቸው ፤ ነብስን እና ሸይጣንን ለማሸነፍ ቆራጥነትን ይለግሳቸው ፤ አላህ ሆይ ቃሚ ወንድሞቻችንን የጫትን ጥላቻ በልባቸው አድርግ፣ ምክርን የሚሰሙ አድርጋቸው።

የአላህ ሰላምታና ዕዝነት በታላቁ ነቢይ በሙሃመድ፣ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን።
 _______ 

ወንድማችሁ ሳላህ አሕመድ‎

ወንድማችሁ ሳላህ አሕመድ