Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው

ሁሉም የቢድዓ ተግባር ጥመት ነው

ከረሱል የተላለፉልን ትዕዛዞች በመቀበል እና ሱናቸውን በመተግበር ልንብቃቃ ይገባል፡፡ ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት (ተከተሉ! አዲስ ነገር አታምጡ ሱንና በቂያችሁ ነውና) ሁዘይፋ ኢብኑ የማን እንዲህ ይላሉ (ማንኛውም የመልዕክተኛው ሰሀቦች ባልሰሩት የኢባዳ ተግባር አምልኮን አትፈፅሙ! የመጀመሪያዎቹ ለመጨረሻዎቹ ይህንን ክፍተት አልተውም) አቡ ዳውድ እና ሌሎችም ዘግበውታል

አላህ የሚያቃርቡን እና የእርሱን ውዴታ የሚያስገኙልን የመልካም ስራ በሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር አዳዲስ የፅድቅ መንገዶችን ለመቅደድ መሯሯጥ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው አላህ ከደነገጋቸው እና መልዕክተኛው ከወደዷቸው የመልካም ስራ በሮች ምን ያህሉን አንኳክቻለሁ ብሎ ራሱን ቢጠይቅ ጉድለቱን ያስተውላል፡፡ 

ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ፡- ‹‹ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው ሰዎች መልካም አድርገው ቢያዩት እንኳ!›› ኢብኑ በጣህ አለለካኢይና ሌሎችም በትክክለኛ ሰነድ ዘግበውታል

የአላህ ዲን ሞልቷል ነብዩም መልዕክታቸውን አድርሰዋል ብሎ ያመነ ሰው በፍፁም ቢድዓ የሆነን ነገር ፈጥሮ ጥሩ ነው አይልም! ፈጠራ እስከሆነ ጥሩ ሊሆን አይችልም፡፡ እስቲ ይህንን ክስተት እናስተዉል፡፡

አንድ ቀን አቡ ሙሳአል-አሽዓሪ ወደ ዓብዱላህ ኢብኑ መስኡድ ቤት ይመጡና እንዲህ ይለዋቸዋል፡- ‹አሁን መስጂድ ውስጥ የሚነቀፍ ነገር ተመለከትኩ።› ‹ምንድነው›? አሉ ኢብኑ መስዑድ።‹በሕይወት ካለ ህታየዋለህ! ሰዎች መስጊድ ውስጥ ሆነው ክብ ሰርተው ተቀምጠው ሶላትን ይጠባበቃሉ፤ ከተሰበሰቡት አንዱ በእጁ ጠጠር ይዞ፡-አንድ መቶ ጊዜ ተክቢራ አድርጉ፣ አንድ መቶ ተስቢህ፣ አንድ መቶ ታህሊል እያለ ያዝዛቸዋል።
እነሱም መቶ፣ መቶ ጊዜ ይላሉ።› ኢብኑ መስዑድም ‹ምን አልካቸው ታዲያ?› ብለዉ ይጠይቋቸዋል።‹ምንም አላልኩም፣ የአንተን አስተያየት በመጠበቅ!› ኢብኑ ‹ታዲያ ለምን ወንጀላቸውን እንዲቆጥሩ በመንገር፣ በጎ ተግባራቸውን መስዑድም ግን አላህ ዘንድ እንደማያጡት ዋስ አትሆናቸውም?› ከዚያም ወደ መስጊድ ‹ምንድነው መሥራት የያዛችሁት? ገቡ። ወደተሰበሰቡት ሰዎች በመምጣትም ወንጀላችሁን ቁጠሩ፣ ጥሩ ሥራችሁን ግን አላህ ዘንድ እንደማታጡት ቃል እገባላችኋለሁ።የሙሀመድ ኡመቶች! ለመጥፋት ምን አስቸኮላችሁ።የነቢዩ ሰሀቦች ሞልተዋል፤ የነቢዩም ልብስ (ገና) አላለቀም፤ ዕቃቸው እነኳ አልተሰበረም።
ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እናንተ ከነቢዩ መንገድ የበለጠ የተመራችሁ ናችሁ ወይም የጥመት በር ከፋች ናችሁ?!› ‹አቡ አብዱራህማን እኛ እኮ ጥሩ አስበን እንጂ ሌላ አሏቸው። ሰዎቹም አይደለም›‹ጥሩ እያሰቡ ግብ የማይመቱ ስንቶች አሉ?!
ነቢዩ አሉ። እንደነገሩን፡- (ሰዎች ይመጣሉ፣ ቁርዓን ይቀራሉ፤ ግን ከጉሮሯቸው አይወርድም!) ምናልባት ብዙዎቹ ከእናንተ ሳይሆኑ አይቀሩም።…› ከዚያ ጥለዋቸው ሄዱ። (አድዳሪሚይና ሌሎች ዘግበውታል)