Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሶለዋት‬ ሙሃደራ በዑስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ



አላህ እናመላእክቱ በነብዩ ላይ ሶለዋት (ሰላምታ ማውረድ) ያወርዳሉ ።እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! በእርሱ ላይ ሶለዋት አውርዱ።የማክበርን ምሰላምታ ሰላም በሉ። (አል-አሕዛብ 56)
ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረድየላሁ አንሁም) የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል ‹‹እኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ አስር ያወርድበታል፤ አስር ወንጀሉ ይማርለታል፤ ደረጃው በአስር ከፍ ይልለታል››ኢማሙ አህመድ በሙስነዳቸው ላይ፤ ኢማሙ አልቡኻሪ አደበል ሙፍረድ 642 እና 643፤ ጃሚ ሳጊር 6359 አልባኒ ሰሂህብለውታል
የሰለዋቶች ሁሉ በላጭ
«قُولُوا: اللَّهُمَّصَلِّعَلَىمُحَمَّدٍوَعَلَىآلِمُحَمَّدٍ،كَمَاصَلَّيْتَعَلَىآلِإِبْرَاهِيمَ،إِنَّكَحَمِيدٌمَجِيدٌ،اللَّهُمَّبَارِكْعَلَىمُحَمَّدٍوَعَلَىآلِمُحَمَّدٍ،كَمَابَارَكْتَعَلَىآلِإِبْرَاهِيمَ،إِنَّكَحَمِيدٌمَجِيد»

የሰለዋቱ ትርጉም፡ (አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ እዝነትህን እንዳሰፈን ከው ሁሉ በሙሀመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም እዝነትህን አስፍን፣ አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህ። አላህ ሆይ! በኢብራሂምና በቤተሰቦቻቸው ላይ በረከትህን እንዳሰፈንክ ሁሉ በሙሀመድና በቤተሰቦቻቸው ላይም በረከትህን አዉርድ ። አንተ ምስጉንና የላቅክ አምላክ ነህ።)
---ድምበር ከማለፍ(ከታዘዝ ነውበላይበማድረግ) እና ከመዘናጋት (ከመድከም) በመራቅ በነብያችን(ﷺ) ላይ ሶለዋት እናውርድ !!!
--->በዑስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ
በብሉቱዝ በመላላክ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ :: Share