Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ግፍና በደል እድሜያቸው አጭር ነው

"ግፍና በደል እድሜያቸው አጭር ነው"

አሰላሙ ዐለይኩምምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ይሁን ሰላትና ሰላም በነቢያት መደምደሚያ ሙሐመድ ላይ ይሁንአሏህ የሰው ልጆችን ካልነበሩበት አስገኝቶ ምድርን ጊዜያው መኖሪያ አድርጎላቸዋል:: እርሱ የሚወደውንና የሚጠላውን የሚነግሯቸው ነቢያትም በየግዜው ልኳል:: ጌታውን ያወቀና ነቢያትን የተከተለ በሁለቱም ዓለም ደስታን ይታደላል:: ይሄን ያላደረገ ግን ከመኖር መሞት ይሻለዋልየሰው ልጆች በዚህች ምድር ላይ ሲኖሩ በዙ ፈተናዎች ይፈራረቁባቸዋል ጌታውን የያዘ፣ መንገዱንም የተከተለ ፈተናዎች ብዙም አይጎዱትም:: ከትልልቅ ፈተናዎች መሀል አንዱ ሰዎች "በሰው መፈተናቸው ነው " (وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًا) {ከፊላችሁን ለከፊሉ መፈተኛ አደረገን፥ በአላማችሁ ጸንታችሁ ትቀጥላላችሁ ወይስ ወደ ኋላ ትንሸራተታላችሁ?ጌታህም ሁሉን አዋቂና ተመልካች ነው} አልፉርቃን 20መልእክተኞች ለተላኩላቸው ህዝቦች መፈተኛ ናቸው ማን ይሁን የጌታውን መልእክተኛ እሺ ብሎ  የሚታዘዘው ማንስ ነው እምቢ የሚለው?!፣ ሀብታሙ በድሃው ይፈተናል፣ መሪዎችም በህዝቦቻቸው ይፈተናሉ ወዘተ ማንም ከፈተና አይድንም::ታላቁ ነቢይ ሙሳ ዐለይሂስሰላም ወደ አምባገነኑ ፊርዐውንና ህዝቦቹ ተላከ ፊርዐውንም ከጌታው በኩል ብዙ ተአምራትን ይዞ የመጣውን ነቢይ አስተባበለ በዚህም አላበቃም እሱን የተከተለን ሁሉ ከምድረ-ገጽ እንደሚያጠፋ ዛተ ብዙ ሙእሚኖችን አሰቃይቶ ገደለ የተቀሩትንም አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው አስፈራራ በተለይ ደግሞ መጀመሪያ  ላይ የሱ አጃቢ የነበሩና ኋላ ላይ ሀቅን ሲያውቁና የነቢዩ  ሙሳን እጅግ በጣም አስገራሚ ተአምራትን ሲያዩ  ያመኑትን! ሀቅ ይዞ የመጣውንም ነቢይ ለመግደል ሙከራዎችን አደረገ አሏህም ነቢዩን ጠበቀ እውነትን መቀበል አሻፈረኝ፣ ያለውና ትንሽ እንኳ ሳያፍር ( እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ) ያለው ፊርዐውን ከእርሱና አድናቂዎቹ በስተቀር ምድር ላይ ማንም በሰላም እንዳይኖር ቆርጦ ተነሳ እንዲህ የሚል መልእክት አስይዞም መልእክተኖችን በየመነንደሩ ላከ፥{ እነዚ በቁጥረ-አናሳ የሆኑ ቡድኖች ናቸው እኛንም አናድደውናል ጠላቶቻችን በመሆናቸው ልንጠነቀቃቸውና ልናጣፋቸው ይገባል } አሹዐራእ 52_56ሙሳም ምእምናንን እንዲህ ሲሉ መከሩ (  اسْتَعِينُوا بِاللَّهِ وَاصْبِرُوا إِنَّ الْأَرْضَ لِلَّهِ يُورِثُهَا مَنْ يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ وَالْعَاقِبَةُ لِلْمُتَّقِينَ  ) " ወገኖቼ ሆይ፥ እርዳታን ከአሏህ ፈልጉ ከእርሱ ድልን በመጠበቅም ታገሱ ምድር የፊርዐውን ሳትሆን የአሏህ ናት ለተወሰነ ጊዜም በጥበቡ ከባሮቹ መሀል እርሱ ለፈለገው ያስወርሳታል አማኞች ለተወሰነ ግዜ መከራ ቢበዛባቸውም መጨረሻ ላይ ድል የነሱ ናት "  አል አዕራፍ 128ምእምናንም የስቃዩን መበርታትና የትዕግስታቸውን ማለቅ እንዲህ ሲሉ ነገሯቸው ( قَالُوا أُوذِينَا مِنْ قَبْلِ أَنْ تَأْتِيَنَا وَمِنْ بَعْدِ مَا جِئْتَنَا  )" ከአንተ መላክ በፊትም በስቃይ ላይ ቆየን አንተም ከመጣህ በኋላ ስቃዩ  እንደቀጠለ ነው" እኮ! ኣሉሙሳም፥ ( قَالَ عَسَى رَبُّكُمْ أَنْ يُهْلِكَ عَدُوَّكُمْ وَيَسْتَخْلِفَكُمْ فِي الْأَرْضِ فَيَنْظُرَ كَيْفَ تَعْمَلُونَ ) " ጌታችሁ ጠላታችሁን አጥፍቶ እናንተን ምድር ላይ ተተኪዎች አድርጓችሁ ከዛ በኋላም እናንተ ምድር ላይ ምን እንደምትሰሩ መመልከት ይችላል " አሏቸው  ፊርዐውን  በዛቻው መሰረት ሰራዊቶቹን ሰበሰበ ነቢዩ  ሙሳና ተከታዮቹም ሰምተው ተጨነቁ ምድርም ጠበበቻቸው! ነቢያቸውንም ምን እንደሚሻል ጠየቋቸው ሀገሪቱን በመልቀቅ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ እንደሚሻል በማመን ውድ የአሏህ ባሪያዎች በነቢያቸው መሪነት ተሰብስበው ጉዞ ጀመሩ ጠላቶቻቸው ጉዞ መጀመራቸውን ሰምተውም በግፈኛና ጨካኙ አለቃቸው ፊርዐውን መሪነት ተከታተሏቸው ነቢዩ  ሙሳና ተከታዮቻቸው ከሀገር እየወጡ ባህሩ ዳርቻ ላይ ሲደርሱ ከኋላቸው መጥተው ደረሱባቸው ልክ ሁለቱም ፊት ለፊት ሲገናኙ ምእምናን ተደናገጡ ሙሳ ሆይ፥ ከፊታችን በሀር ከጀርባችን ፊርዐውን እስከነሰራኢቶቹ.....!!ወዴት ነው የምንሄደው? ምንስ ይሻለናል?! አረ አለቅን!!  አሉበጌታቸው ከማንም በላይ የሚተማመኑት ሙሳ  (  كَلَّا إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ) " በፍጹም በጠላቶቻችን እጅ አንወድቅም! እነሆ ከኔ ጋር ጌታዬ አሏህ አለ! " አሉ አሹዐራእ 62ይሄኔም አሏህ ሙሳን በብትራቸው ባህሩን እንዲመቱት አዘዛቸው መቱትም 12 ለጥ ያሉ ሜዳዎች ተፈጠሩ (ባህሩ ላይ!) ከሙሳ ጋር የነበሩ 12ቱም ነገዶች በተከፈተው መንገድ ላይ መሻገር ጀመሩ ፊርዐውንና ወታደሮቹም ግራ ተጋቡ የሚያዩትንም ማመን አቃታቸው ልክ ሙሳና ተከታዮቻቸው በባህር ላይ ያለ መርከብ እንደተጓዙት ለመጓዝ ፊርዐውንም ሀሰበ ፈራ ተባ እያለም ገባ ተከታዮቹም ተከትለውት ገቡ! ሙሳና ምእምናን ሁሉም ከባህሩ እንደወጡ ፊርዐውንና ተከታዮቹም መሀል ላይ እንደደረሱ አሏህ ባህሩን መጀመሪያ ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ አዘዘውግፈኞች በሙሉ እዛ ውስጥ ሰምጠው ቀሩ የአሏህ ትክክለኛ ባሮች ዳኑ! ያዩትንም ማመን አቃታቸው! አሏህም በቁድራው የፊርዐውንን ሬሳ ከባህሩ ላይ በማንሳፈፍ መሞቱን አሳያቸውከዝያኔ ጀምሮ ሙእሚኖች ከግፉ እፎይ ኣሉ ጌታቸውንም አመሰገኑዕለቱ ዓሹራ ነበረና በየዓመቱም ይሄን ቀን ለጌታቸው ምስጋና ሲሉ ይጾሞ ጀመርከዘመናት በኋላ ነቢዩ ሙሀመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ተልከው ወደ መዲና ሲሰደዱ በግዜው የነበሩ አይሁዳውያን ዕለቱን ሲጾሙ አይተዋቸው  ለምን እንደሚጾሙ ጠየቋቸው " ፊርዐውን የጠፋበትና ሙሳ የዳነበት ዕለት ስለሆነ አሏቸው" ነቢዩም እኛ ከእናንተ ይልቅ የሙሳን መንገድ ተከታዮች ነን በማለት እሳቸውም ጾሙ ሙስሊሞችም እንዲጾሙ አዘዟቸውከአይሁዳዊያን መመሳሰል እንዳይሆንም ቀጣይ  ዓመት አሏህ ካኖረኝ 9ኛውንም ቀን እጾማለሁ አሉ ግን ግዜው ሳይደርስ ሞቱ!በሰሂህ ሀዲሳቸው ይሄንን ቀን መጾም የአንድ ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ተናግረዋልከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን ጹሙም ብለዋልአንባቢያን ሆይ፥ እነሆ ድል የሚመጣው፥ አሏህን እርዳታ በመለመን፣ የሱ እርዳታ እንዲዘገይ የሚያደርጉ ነገሮችን በመራቅ፣ ሰብር በማድረግና ዒባዳ ላይ በመበርታት እንደሆነ እንወቅ:: ጠላቶቻችንን አሏህ የሚያጠፋቸው ወንጀለኛ በመሆናቸው ነው እኛም እነደነሱ ወንጀን ከተዳፈረን አብረን እንጠፋለ!ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ  // አሕመድ ኣደም//