Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስነስርዓት ስለ ግሳት እና ማዛጋት


ስነስርዓት
ስለ ግሳት እና ማዛጋት

ከማግሳት በኋላ ዚክር ኣለን ?
ከማዛጋት በኋላስ ምን ይባላል ?
የማዛጋትና የማግሳት ስርዓት ?
እየሰገድን ቢያዛጋንስ… … ?
በሰላት ውስጥ ሲያስገሳንስ ?
ከማግሳት እና ከማዛጋት
(ማፋሸግ) በኋላ ሊባል የሚገባው
ለየት ያለ ዚክር ኣለን ??
ተብለው ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ ተጠየቁ
📋 ምላሻቸው: -
« አንድ ሰው ካገሳም ይሁን ካዛጋ (ካፋሸገ) በኋላ ሊለው የሚገባው ዚክር የለም። በመሆኑም ለዚህ መረጃ ኣለመኖሩ ተራው ህዝብ የሚያደርገውንም ይቃረናል።
አብዛኛው የህብረተሰብ አካል ግን ካገሱ በኋላ
" አልሀምዱ ሊላህ " ይላሉ
☑ እርግጥ በማንኛውም ሁኔታችን አምላካችን አላህ ምስጋና ይገባዋል።
ነገር ግን ማግሳት አላህን እንድታመሰግን ሰበብ ሆኖ አልመጣም።
📕 ስታገሱ አልሀምዱሊላህ በሉ የሚል መመርያም አልመጣልንም።
እንዲሁም
ሲያዛጉ (ሲያፋሽጉ)
" አዑዙ ቢላሂ ሚነሸይጣኒ ረጂም " የሚሉም ኣሉ
📕 ይሁንና በዚህም ወቅት ይህንን ቃል እንድንል የደረሰን መረጃ ባለመኖሩ መሰረት አልባ ተግባር ይሆናል።
📚 ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ተግብረዋል የሚል ምንም አስረጅ አልወረደም። »
_______________________
إنـتــبـه أخـي المسلـم
⇦ هل هناك ذكر معين بعد
التجشؤ والتثاؤب ؟؟
إذا تجشأ الإنسان أو تثاءب فليس له ذكر
خلافاً للعامة , فالعامة إذا تجشئوا يقولون: الحمد لله !
والحمد لله على كل حال
لكن لم يرد أن التجشؤ سبب للحمد
كذلك إذا تثاءبوا قالوا: أعوذ بالله من الشيطان الرجيم. وهذا لا أصل له، ولم يرد عن النبي - عليه الصلاة والسلام -
أنه كان يفعل ذلك.
لفضيلة الشيخ العلامة/ محمد بن صالح العثيمين - رحـمـهُ الـلـه تـعالـى -
በታላቁ ሊቅ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን
ረሂመሁላህ
الـمـصــــدر :- ምንጭ
📚 لقاء الباب المفتوح [22]
የሸይኹን መልዕክት ከድምፃቸው ለማድመጥ
🔊 رابط المقطع الصوتي
[ http://is.gd/SoHvsS ]
<< >>~~~~~~~~<< >>
የማዛጋትና የማግሳት ስርኣቶች
……………………………
★ ኢስላም ለሁሉም የህይወታችን ሂደት ስርዓትና ገደብ ኣለው።
በኢስላም ልቅ የሚባል የህይወት መርህ የለም። ራስህን መጉዳትም፣ ሌሎችን ማስቸገርም እርም ነውና።
★ ለግለሰቦች መብት እንደሚቆረቆር ሁሉ ለማህበረሰብ ደህንነትም ቅድሚያ ይሰጣል።
ማዛጋት ሆነ ማግሳት የራስህ ውስጣዊ ግፊት ብሎም መብት እንደሆነው ሁሉ ሌሎችን ኣለመረበሽም ግዴታ ነው።
★ ኢስላም ለይዘት ማማር ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያደርግ ሁሉም ለቅርፅ መስተካከልም በተጓዳኝ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል።
ለዚህም ማሳያ አርካኑል ኢማንና አርካኑል ኢስላም ለቅርፅና ይዘታችን መስተካከል በቂ ምስክር ናቸው።
~ ልቦናችን በኢማን ማማር
መዋብ አለበት
~ አካላችን በተግባር ማሸብረቅ
ይገባዋል
~ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ክፋት … ከልባችን መፅዳት በዚህም ውስጣችን ይዘታችን መዋብ እንዳለበት ሁሉ
~ ስድብ፣ ማንቋሸሽ፣ መገላመጥ፣ መንቦጣረር፣ የመሳሰሉትም ውጫዊ ማንነታችን ላይ ጎልቶ ይዘታችንን የሚያበላሽ በመሆኑ ከተግባራችን መፅዳትና መራቅ ይገባዋል።
ሲያዛጋን (ሲያፋሽገን)ምን
እናድርግ ??
========~~~~=======
ማግሳትና ማዛጋት አላህ የፈጠረብን ተፈጥሯችንና ውስጣዊ ስሜታችን ቢሆንም በተግባር ስናውለው ግን በዙርያችን የሚገኙትን ወገኖች ቅር በማያሰኝና በማያስጠላ መልኩ ልንወጣው እና ለሸይጣንም መግቢያ ላለመክፈት መከላከል ይገባናል።
ለዚህም ነው መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማዛጋትን በተመለከተ:
📚
وروى مسلم (2995)
عن أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ :
( إِذَا تَثَاوَبَ أَحَدُكُمْ فَلْيُمْسِكْ بِيَدِهِ عَلَى فِيهِ ، فَإِنَّ الشَّيْطَانَ يَدْخُلُ ) .
ኢማም ሙስሊም ረሂመሁላህ በዘገቡትና አቢ ሰዒድ አል ኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ ባወሩን መሰረት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: -
« አንዳችሁ በሚያዛጋው (በሚያፋሽገው) ግዜ ኣፉን በእጁ (ዘግቶ) ይያዝ፣ ሸይጣን ይገባበታልና »
وفي لفظ له :
በሌላ ዘገባ ደግሞ በተለይ ሰላት ውስጥ ሳለን ሲያዛጋን ምን ማድረግ እንዳለብን ይጠቁሙናለል:-
📚
(إِذَا تَثَاوَبَ أَحَدُكُمْ فِي الصَّلَاةِ فَلْيَكْظِمْ مَا اسْتَطَاعَ)
« ሰላት ላይ እያላችሁ አንዳችሁን ካዛጋው (ካፋሸገው) የሚችለውን ያህል ኣፍኖ ይያዝ »
እንዲሁም
وفي رواية أبي داود :
በአቢ ዳዉድ ዘገባ ማዛጋት(ማፋሸግ) ከሸይጣን እንደሆነ ተገልፆአል።
( فإذا تثاءب أحدكم فليرده ما استطاع، ولا يقول: هاها، فإنما ذلك من الشيطان يضحك منه )،
« አንዳችሁን ያዛጋችሁ እንደሆነ በቻለው አቅም ለመመለስ (ላለማዛጋት) ይሞክር። (ኣፉን ከፍቶም) … ሃ… ሃ… አይበል። ይህም ከሸይጣን ነውና ይስቅበታል። »
ስለሆነም ሊያዛጋን በፈለገ ግዜ እንደምንም ለማፈንና ላለማዛጋት መጣር ይጠበቅብናል ፣ ካልሆነና አሻፈረኝ ብሎን ከወጣ ግን በተለይ በግራ እጃችን ኣፋችንን መሸፈን ይገባናል።
~~√√~~√√√~~~~√√~~
ሲያስገሳንስ ምን እናድርግ
……………======……………
📚
وعن ابن عمر - رضي الله عنهما -
أن رسول الله - صلى الله عليه وسلم -
سمع رجلا يتجشأ فقال :
" أقصر من جشائك ، فإن أطول الناس جوعا يوم القيامة أطولهم شبعا في الدنيا "
. رواه في ( شرح السنة ) . وروىالترمذي نحوه
[قال الألباني رحمه الله: له شواهد يرتقي بها إلى درجة الحسن]
ከኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ በተወራው ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ እያገሳ የነበረን ሰው ሰሙትና
« ከግሳትህ ታቀብ (ተቆጠብ)። የውመል ኣኸር ለረዥም ግዜ ርሃብተኛ የሚሆኑት ሰዎች፣ በዱንያ ላይ ጥጋብ የሚያበዙ ናቸውና። »
በዚህና በሌሎች ዘገባዎች እንዲሁም ከአጠቃላይ የኢስላም ኣዳብ በመነሳት
~ ማግሳት ምግብ ከማብዛት፣
ከመጥገብ ይመጣል
~ ደስ የማይል ድምፅ ይፈጥራል
~ ጥሩ ያልሆነ ሽታም ከአንጀትና
ከኣፍ በብዛት እንዲወጣ
ያደርጋል
በመሆኑም በአጠገባችን ያለን ሰው ሊያስቸግር ስለሚችል እንደ ትእዛዙ በተቻለን መጠን ለማፈን፣ ለማስቀረት ወይም ከሰው ለመራቅ፣ ወይም ለመቀነስ መጣር ይገባናል።
NB# ለዚህ አስረጅ የሆነው ያለፈው ሀዲስ በብዙ መንገድ ተወርቷል ይሁንና ደካማ ሰንሰለቶች ይበዙበታል። ቢሆንም ሸይኽ ናስሩዲን አል አልባኒይ ከብዙ ጥናት በኋላ " ሀሰን " ብለውታል።
بعدما ذكر الشيخ الباني طرق الحديث قال في آخره:
وجملة القول: أن الحديث قد جاء من طرق عمن ذكرنا من الصحابة، وهي وإن كانت مفرداتها -أي: كل طريق بمفرده- لا تخلو من ضعفٍ، فإن بعضها ليس ضعفها شديداً، ولذلك فإني أرى أنه يرتقي بمجموعها إلى درجة الحسن على أقل الأحوال، والله سبحانه وتعالى أعلم.
~~~~~~~~~~~~~
ሰላት ላይ እያለን ሊያስገሳን
ከፈለገን ምን እናድርግ ?
======~~~~~~~======
ይህንን በተመለከተ ከኢማም አህመድ ቢን ሀንበል ረሂመሁላህ የተገኘ መልእክት ኣለን።
አቢ ጣሊብ በዘገቡት ኢማሙ አህመድ ረሂመሁሙላህ እንዲህ ኣሉ:
« እየሰገደ (ሰላት ውስጥ እያለ) ካስገሳው የግሳቱ አየር (ከኣፉ ወጥቶ እስኪሄድ) እስኪወገድ አናቱን ፣ ጭንቅላቱን ወደላይ ወደ ሰማይ ከፍ ያድርግ።
ምክንያቱም ራሱን ከፍ ካላረገ በዙርያው ያሉትን ሰዎች ያስቸግራል። ይህም ስነስርኣት ለመጠበቅ ሲባል የተደረገ ነው። »
በሌላም ዘገባ እንዲህ ብለዋል
« አንድ ሰው ካስገሳው አናቱን ወደ ላይ ማድረግ ይጠበቅበታል፣
ምክንያቱም ሰዎችን የሚያስቸግር ሽታ ( ጠረን) ከኣፉ ወደነሱ እንዳይወጣ ይረዳዋልና።
ካልሆነና ወደ ቀኙ ወይም ወደ ግራው ወይም ወደ ፊትለፊቱ ካገሳ ጠረኑ(ሽታው) ይባስ (በሰጋጆች መሀል) ይናፈሳል።
ስለዚህም አንድ ሰው ግሳቱ ገፍቶ ከመጣበትና መከላከሉ ካቅሙ በላይ ከሆነ ኣናቱን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ መተንፈስ ይገባዋል፣ የሚቻለውም ይኸው ነውና። »
ኢማሙ አህመድ ረሂመሁላህ
التجشؤ في الصلاة
الإنسان قد يغلبه التجشؤ فماذا يفعل؟يكفه ما استطاع، حتى أن الإمام أحمد رحمه الله في رواية أبي طالب قال :
إذا تجشأ وهو في الصلاة، فليرفع رأسه إلى السماء حتى تذهب الريح، وإذا لم يرفع رأسه آذى من حوله من ريحه، وهذا من الأدب، وقال في رواية مهنا،
عن الإمام أحمد:
إذا تجشأ الرجل ينبغي أن يرفع رأسه إلى فوقه؛ لكي لا يخرج من فيه رائحة يؤذي بها الناس، فإذا تجشأ عن يمينه أو شماله، أو وجهه إلى الأمام كأن الرائحة تكون أشد، فأكثر ما يمكن أن يفعله أن يرفع رأسه إلى فوق وهذا إذا اضطر إلى ذلك.
……………
ወላሁ አዕለም
ወሰለላሁ ዓላ ነቢዪና ሙሀመዲን ወዓላ ኣሊሂ ወሳህቢሂ ወሰለም
ወሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላህ
~~~~<<<<>>>>~~~~
Abufewzan
16 Muharram 2014

Post a Comment

0 Comments