Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተንቢሃት ትምህርት ቁጥር 7 አል ሂጃብ

ተንቢሃት
ትምህርት ቁጥር 7
አል ሂጃብ
ሴት ልጅ ሂጃብ በመልበሷ ወንዶች እርሷን አይተው ፈተና ላይ ከመውደቅ ትጠበቃለች፡፡
እንዲያውም አይናቸውን ሰበር ለሚያደርጉ ብርቅዬዎች ብቻ ሳይሆን ላይ ታቹን ለሚያማትሩትም አደብ ታስገዛበታለች፡፡
ምክንያቱም ምንም ቢቁለጨለጩ የሚያገኙት ነገር የለምና ነው፡፡
ነገር ግን በተቃራኒው ሆና የምትገላለጥ ከሆነ የፈተናና የጥፋት በር ሊዘጉት በማይቻል መልኩ ይበረገዳል፡፡
በዘመናችን ያለውን ሁኔታ ያስተዋለ አላህ ያዘነላት ካልሆነች በስተቀር ሴት ልጅ በገዛ እራሷ ክብሯን አሽቀንጥራ ወርውራዋለች፡፡
በሰበቡም የቂሎችና ጅቦች ጉርሻና እራት ሆና አንግታለች፡፡ አይንሽ፣ከንፈርሽ፣ዳሌሽ ብለው በማማለል የማይረግብ ስሜታቸው ማርኪያ ሎሌ አድርገዋታል፡፡
እርሷም ይህ መርዝ ያስቀረባት ጠባሳ ይመስላል ፊቴ አምሮ ቅርፄ ተስተካክሎ ይሆን እያለች የነሱ የወሲብ መግነጢስ ሆኖ ከመቅረት ውጪ ሌላ ግብና አላማ አልታይ ብሏታል፡፡
አሁን አሁንማ ለዚህ አባዜ የህይወት መስዋዕትነትም እየከፈለችበት ይገኛል፡፡
ለምኑ ካላችሁኝ ለዚሁ ከንቱ አላማዋ ስትል: - አፍንጫ፣ አይን ፣ከንፈር ፣ ሆድና የመሳሰሉትን ቀዶ ጥገና በማድረግ ኣምሮና ሸንቅጦ ለመቅረብ የምታደርገው መራወጥ በቂ ምስክር ነው፡፡
ይህን መሰል ከምእራቡ አለም የመጣው አባዜ ሙስሊሙንም አለም እየናጠው ይገኛል፡፡
እዚህ ጋ ሊታወቅ ሚገባው ነገር ምእራቡ አለም ላይ ልብስ ለጌጥነት እንጂ ለሲትርነት እንደማይውል ነው፡፡
ሙስሊሞች ዘንድ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው ፡፡ ልብስ መሰረታዊ አላማው ሃፍረተ ገላን ለመሸፈንና ለመደበቅ ነው፡:
አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ይህን ሲናገር እንዲህ ብሏልና:-
« يَا بَنِي آدَمَ قَدْ أَنزَلْنَا عَلَيْكُمْ لِبَاسًا يُوَارِي سَوْآتِكُمْ وَرِيشًا »
[٧:٢٦]
«የአደም ልጆች ሆይ ሃፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግ ልብስ ጌጥንም በርግጥ በእናተ ላይ አወረድን»
📚 (7:26)
ከላይ ያሳለፍነው ምእራፎች ላይ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ለይቶ በዘረዘረውና ባትሸፋፈንላቸው ችግር እንደሌለው ለፈቀደላቸው የወንድ ክፍሎች ካልሆኑ በስተቀር ሴት ልጅ ሂጃብ እንድታደርግና እንዳትገላለጥ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
እንዲሁም ከዚሁ ጎን ለጎን ለእርሷ ባእድ ለሆኑ ወንዶች ብቻ ሳይሆን ከሴቶችም ጋር ስትሆን የአለባባስ ስርዓትዋን በግልፅ አስቀምጧል።
ይኸውም አንቀፁ ላይ እንደተቀመጠው ለእርሷ መህረም ወይም ሊያገቧት ከሚከለከሉት ወንዶች ፊት የምትለብሰውን ልብስ ነው ለሴቶችም መልበስ ያለባት።
ይህ ከሆነ እንግዲህ አሁንም ምን ያህል ከመራቆት መራቅ እንደሚገባ መገመት አያቅትም።
አሁን አሁን በተለይ የሴቶች ናቸው እየተባለ የሚለበሱ አልባሳት በኢስላም አይደለም የኢትዮጵያ ባህልም አይፈቅደውም።
የሴቶች ነው እየተባለ የውስጥ ልብሶችን ሳይቀር የሚያሳይ፤ እያንዳንዱን የሰውነት ቅርፅና ከፍል ቁልጭ አድርጎ የሚያስቃኝ ልብስ መልበስ ልማዳዊ ሆኗል።
አላህ ይጠብቀን።
ይቀጥላል…
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
https://www.facebook.com/tenbihat
ቀላል ስራ ብዙ አጅር ማግኘት ይሻሉ! እንግዲያውስ…
ይህን መልዕክት ቢያንስ ለ3 ሰው ያድርሱ!