Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‪አላማህን እወቅ‬

‪#‎አላማህን_እወቅ‬
አላህ የሠው ልጆችንና ጋኔኖችን የፈጠረው እሱን እንዲገዙና እንዲያመልኩት ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنْسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም” (አል ዛሪያት 56)
በመሆኑም በአላህ ማመንና እርሱን ብቻ ማምለክ ሰዎች የተፈጠሩለት ዋናው ዐላማ ነው፡፡ የሰው ልጅ አላህን በሚገባ ለማምለክና የተፈጠረለትን ዐላማ ለማሳካት የሚረዳው ዋና መሠረት ከቁርዓንና ከሐዲስ የተወሰደ ትክክለኛ እምነትን መማር ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ነብዩ መካ በነበሩበት አስር አመታት ከሌሎች ኢስላማዊ ተግባሮች ቅድሚያ በመስጠት እምነትን በከፍተኛ ትኩረት ያስተምሩ ነበር፡፡
የእምነት መስተካከል የአምልኮ (ዒባዳ) የባህሪና የማህበራዊ ኑሮ መስተካከልን ያስከትላል በአንፃሩ ትክክለኛ እምነት ከሌለ ወይም ከተበላሸ ስራ ባህሪና ስርዓቶች ይበላሻሉ፡፡
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ “አካል ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለ እሱ ከተስተካከለ መላ አካል ይስተካከላል እሱ ከተበላሸም መላ አካል ይበላሻል እሱም ልብ ነው”
ልብ ሲስተካከል የንግግር፣ተግባርና ባህሪ ይስተካከላል፡፡ ልብ ከተበላሸም እነዚህ ሁሉ ይበላሻሉ፡፡ ስለዚህ ከሁሉም በፊት ልብን ሊያስተካክልና ሊያሳምር የሚችለውን ትክክለኛ እምነት (ኢማን) ትኩረት በመስጠት መማርና መተግበር ያስፈልጋል፡፡
በኢማን ምክንያት በዚህች ዓለም በተረጋጋ መንፈስና በሰከነ ልብ መልካም ህይወት ሲኖር በመጨረሻው እለትም በዘላለማዊ ደስታና በማይቋረጥ ምንዳ ጀነት ውስጥ ይዘወተራል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُمْ بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
“ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን” (አን ነህል 97)
وَمَنْ أَرَادَ الْآخِرَةَ وَسَعَى لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولئِكَ كَانَ سَعْيُهُمْ مَشْكُورًا
“መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው እርሱ አማኝ ኾኖ ለርሷ (ተገቢ) ስራዋን የሰራም ሰው እነዚህ ስራቸው የተመሰገነ ይሆናል” (አል ኢስራእ 19)
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا
خَالِدِينَ فِيهَا لَا يَبْغُونَ عَنْهَا حِوَلًا
“እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ የፊርደውስ ጀነቶች ለነሱ መስፈሪያ ናቸው:: በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ከርሷ መዛወርን የማይፈልጉ ሲኾኑ::” (አል ከህፍ 107−108)
وَمَنْ يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَى
جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَذَلِكَ جَزَاءُ مَنْ تَزَكَّى
“በጎ ስራዎችን በእርግጥ የሰራ አማኝ ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለነሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ጀነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ (አሏቸው)፤ ይህም የተጥራራ ሰው ምንዳ ነው” (ጣሃ 75−76)
ይህን እድል ለመጎናፀፍ በትክክለኛው እምነት ላይ ፀንተው ለሚቀጥለውም ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ግንባር ቀደም የሆኑት ነብዩ እና የሳቸው ባልደረቦች (ሶሀቦች) ነበሩ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْ رُسُلِهِ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ
“መልክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፤ ሁሉም በአላህ በመላእክቱም በመፃህፍቱም በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም (የሚሉ ሲኾኑ) አመኑ ፤ ሰማን ፤ ታዘዝንም ፤ ጌታችን ሆይ ! ምህረትህን (እንሻለን) ፤ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው አሉም” (አል በቀራህ 285)
በተማርነው የምንጠቀም ያድርገን አሚን!!!!
‪#‎አላማችን‬ መሰረታዊ የሆነውን የተውሂድ እውቀት ለሙስሊሙ ማህብረተሰብ በሰፊው ማድረስ ነው::
መሰረታዊ የተውሂድ ዕውቀትን መማር የሚፈልግ ሁሉ like ሊያደርገው የሚገባ ፔጅ
--------------------------------------
https://www.facebook.com/firsttewhed
---------------------------------------------------------

Post a Comment

0 Comments