Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥበበኛው ጌታ አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህን ባዕል ውስጡ ባቀፋቸው ስርዓቶች ደነገገው ከነሱም ውስጥ

ጥበበኛው ጌታ አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህን ባዕል ውስጡ ባቀፋቸው ስርዓቶች ደነገገው ከነሱም ውስጥ
1) የእርሱን ብቸኛ ተመላኪነት ላኢላሃኢለላህ በማለት ከፍ ባለ ድምፅ፣
2) የእርሱ ታላቅነት አላሁ አክበር በማለት፣
3) ለእርሱ ታዛዥነት ለበይክ አላሁመ ለበይክ በማለት፣
4)የእርሱ ተመስጋኝነት ወሊላሂልሃምድ በማለት፣
5) ጠዋፍን ለእርሱ ብቻ እሱ የደነገገው ቤቱ ላይ ሀረም በማድረግ፣
6) እርድን ለእርሱ ብቻ፣ በእርሱም ስም ብቻ ቢስሚላሂ አላሁ አክበር በማለት
7) አማኝ ለአማኝ እንደ አንድ አካል ነው የተባለውን አንተ ትብስ አይነት ያረዱትን ስጋ አቅም ላነሳቸው ሙስሊም ወንድም እና እህቶች በማካፈል፣
8) የአለም ሙስሊሞች የአረፋ ሜዳ ላይ አንድ የምታደርጋቸውን "ላኢላሃኢለላህ ዋህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ብለው የነብያትን ፋና በመከተል፣ የሙስሊሞቸ አንድነት የተመሰረተባትን የተውሂድ ቃል ይናገራሉ።

እናም ሌሎችም። አላህ ሆይ! ዲንን አስገንዝበን፣ ጥበብህን ከሚረዱት የአእምሮ ባለቤቶችም አድርገን።