Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አያሙተሽሪቅ

አሰላሙ ዐለይኩም
===አያሙተሽሪቅ===
ከዒድ ቀን ቀጥሎ በተከታታይ ያሉ ሶስት ቀናት ( የዙልሒጃ 11፣ 12 እና 13ኛው ቀናት) አያሙተሽሪቅ በመባል የሚታወቁ ሲሆን እነዚህ ቀናት
{ አሏህ በፈቀደው መሰረት፥ በመብላት፣ በመጠጣትና ዚክር በማብዛት ልናሳልፋቸው የሚገቡ ቀናት እንደሆኑ ነቢያችን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናግረዋል} ሐጅ ላይ ሆኖ በተመቱዕ እና ቂራን ምክንትት በግ ማረድ ግዴታ ሆኖበት ማረድ ሳይችል ቀርቶ በጾም መካስ ግዴታ የሆነበት ሰው ካልሆነ በስተቀር እነዚህን ቀናት መጾም ከልክለዋል::

የአሏህ ባሮች ሆይ፥ አሏህ የፈቀደላችሁን ሁሉ በሱናው መሰረት ብሉ፣ ጠጡ ነገር ግን አታባክኑ
ብሉ፣ ጠጡ ነገር ግን አሏህን ማመስገን አትዘንጉ
ብሉ፣ ጠጡ ነገር ግን ከዙሪያችሁ ያሉ አቅመ ደካሞችን አስታውሱ
ብሉ፣ ጠጡ ነገር ግን ከዓለም ዙሪያ እየተሰቃዩ ያሉ ሙስሊሞችን በየደስታችሁ መሀል እያስታወሳችሁ ዱዓ አድርጉላቸው
ብሉ፣ ጠጡ ነገር ግን አሏህን ማስታወስና ህግጋቱንም መተግበር አትዘንጉ፥ በሱ ማንንም ምንንም አታጋሩ፣ ሰላትን በጀመዓና በወቅቱ ስገዱ ሐራም ከመመልከትና ከመናገር ታቀቡ

አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ላ ኢላሀ ኢለሏህ አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ