Golgul/ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ
መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
(ኢብኑ ሙነወር) ( Ibnu Munewor )
http://www.goolgule.com/minor-correction-to-amsalus-mateb-and-what-is-secularism-article/

ከአዘጋጆቹ፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን
ነው?” በሚል ርዕስ ለጻፉት ሥርዓት ጠብቆ ምላሽ የሚሰጡ ተቀብለን እናትማለን ባልነው መሠረት ኢብኑ ሙነወር
“መጠነኛ ማስተካከያ ለሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው” በሚል ርዕስ ጨዋነት በተሞላበት አጻጻፍ የላኩልንን ምላሽ
ከዚህ በታች አትመናል፤ ምስጋናችንንም እናቀርብላቸዋለን፡፡ ሌላ አዲስ አጀንዳ እስካልመጣ ድረስ በዚሁ ይህንን
ውይይት የቋጨን በመሆኑ ምላሽ ጽሁፎችን የማንቀበል መሆናችንን እንገልጻለን፡፡ ጉዳዩን መቀጠል የሚፈልጉ ከጸሐፊዎቹ
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋውና ኢብኑ ሙነወር ጋር በኢሜይል ወይም በፌስቡክ ወይም በሌላ በሚያመቻቸው መንገድ
በመገናኘት ሃሳባቸውን መላክ ይችላሉ፡፡
*********************************
በቅርቡ በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ መንግስት ለአመራሮቹ በሰጠው ስልጠና ላይ የተንፀባረቀውን ሀላፊነት የጎደለው ፀረ-ሀይማኖት እይታ በማስመልከት “ማተብ እናስወልቃለን? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው?” በሚል ርእስ በሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው የተፃፈ ፅሁፍ ዛሬ መስከረም 29/2007 አውጥታችኋል፡፡ በቀረበው ፅሁፍ ላይ “በጨዋነት” መመለስ ለሚፈልጉ ሁሉ ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን በመግለፃችሁ “የኔ” የምለውን ሀሳብና ማስተካከያ ስልክላችሁ እንደምታወጡት ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
በኔ በኩል እንደ ሙስሊምነቴ “ይመለከቱኛል እርማትም ይሻሉ” ከምላቸው ፀሀፊው ካነሳቸው ነጥቦች የተወሰኑትን እያነሳሁ ጥቂት ማለት እወዳለሁ፡፡
1. “የእስላም ሴቶች በትምህርት ተቋማትና መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ሂጃብና ኒቃባቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን ይበጥስ” ማለታቸው በተነሣ ጊዜ አቶ ሽፈራው “ማተቡም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢሆን መውለቁ አይቀርም” …” እዚህ ጋ ማለት የምፈልገው ሀሳብ አለኝ:-
1.1. “ኢስላም” የሀይማኖቱ መጠሪያ እንጂ የተከታዮቹ መጠሪያ አይደለም፡፡ የተከታዩ መጠሪያ “ሙስሊም” ነው፡፡ በርግጥ ይህን ከባድ ነገር አድርጌው ሳይሆን በስፋት የሚንፀባረቅ ስህተት ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ እርምቱን ማስታወሱ አይከፋም ብየ ነው፡፡
1.2. ወደ ነጥቡ ስገባ እውነት ሙስሊሞቹ “እኛ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ ክርስቲያኑም ማተቡን ይበጥስ” ብለው ከሆነ እኔም ስህተት እንደተሰራ ይሰማኛል፡፡ ምክኒያቱም ሙስሊሞቹን ጂልባብና ኒቃብ እንዲያወልቁ እያስገደደ ያለው የሴኩላሪዝም ጭንብል የለበሰው መንግስት እንጂ ህዝበ-ክርስቲያኑ አይደለምና፡፡ “እኔን የምትገድለኝ ከሆነ እንግዲያው እከሌንም ግደል” አይነት አመክንዮ ጤነኛ አይደለምና፡፡
1.3. ባይሆን አንድ ነገር እሰጋለሁ፡፡ ልክ ፀሀፊው እንዳደረገው ለራሳቸው የእምነት እሴቶች የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ሳለ (ማድረግም መብታቸው ነው) የሙስሊሞችን እምነታዊ እሴቶችና የሚከላከሉባቸውን ምክኒያቶች ዋጋ የሚያሳጡ ወይም የሚያቃልሉ ሲመለከቱ ጊዜ ምናልባት ሙስሊሞቹም እንዲህ አይነት ሀሳብ ቢሰነዝሩ ብዙ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ማለት የፈለግኩት ሀሳቡ ትክክል ነው አይደለም ሳይሆን የተናገሩበት አግባብ ሊጤን ይገባዋል ነው- ምናልባት ተናግረው ከሆነ፡፡
1.4. ከዚያ ባለፈ “ማተቡም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው እንደ የሃይማኖት መለያ እስካገለገለ ድረስ አደረጃጀታችንን ስንጨርስ ማተብም ቢሆን መውለቁ አይቀርም” የሚለው የአቶ ሺፈራው ንግግር (እውነት ከሆነ ደግሞም አይባልም አልልም) አስተዋይ ለሆኑ ክርስቲያኖች ትልቅ መልእክት ነበረው፡፡ መንግስት የሙስሊሞቹን እምነት ሲዳፈር “ኒቃብና ማተብ የተለያዩ ናቸው” እያሉ ለመንግስት ብርታትና ጊዜ ከሚሰጡ “ነግ-በኔ” ብለው ከወዲሁ “ለምን” ቢሉ መልካም ነበር፡፡ ዘመቻው ምናልባትም ሙስሊሙ ላይ ብቻ ላይሆን ይችላልና የተነሳው፡፡
2. ሌላው ፀሀፊው “ለማንኛውም ለሁሉም ሰው ግልጽ ይሆንለት ዘንድ የማተብንና የሂጃብ ሊቃብን ምንነት ማየት ይኖርብናልና” በማለት ያጋደለ ድምዳሜ ሰርቷል፡፡ ልክ ማስተዋል እንዳቃተው መንግስታችን የሙስሊሟ ሴት ልብስ መታገድ እንዳለበትም አምኖ ሊያሳምነን ሞክሯል፡፡ “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” ነው ነገሩ፡፡ በዚህ ነጥብ ስር የተነሱትን ሃሳቦችና የራሴን ምልከታ ጥቂት ልበል፡፡
ፀሀፊው የሙስሊሟ ልብስ መታገድ እንደሚገባው ሁለት ምክኒያቶችን አቅርቧል፡፡ አንዱ የልብሱን ዋጋ ማቅለል ነው፡፡ “ሂጃብና ኒቃብ ለመከለያነት ለመሸፈኛነት ለመደበቂያነት ለመሸሸጊያነት ከሚያገለግል ልብስነት የዘለለ ትርጉምና አገልግሎት የለውም” በማለት፡፡ ሌላኛው የፀጥታ ስጋት ነው “ለአሸባሪዎች መጠቀሚያነት” ሊውል ይችላል በማለት፡፡
2.1. በቅድሚያ የሙስሊሟም የአለባበስ ስርኣት የማንነት ጉዳይ ነው፡፡ ፀሀፊው “እኛ ክርስቲያኖች ማተብ የምናስርበት ምክንያት በኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔር በሆነ በእግዚአብሔር ልጅ) ማመናችንን ለሌሎች ለሚያዩን ሁሉ ለመመስከር ወይም ክርስቲያን መሆናችንን ለሌሎች ለማረጋገጥና ክርስቲያን በመሆናችንም እንደማናፍርበት ይልቁንም እንደምንኮራበት ለማረጋገጥ ነው” እያለ ስለማተብ ሲሞግት ሙስሊሙም ተመሳሳይ ነገር እንደሚል ባይዘነጋ መልካም ነበር፡፡ ይሄ እኮ ቀላል ሂሳብ ነበር? ደግሞም ከማንነት ባለፈ የሙስሊሟ አለባበስ ሌላ ፋይዳም አለው፡፡ እራሱ ፀሀፊው እንዳለው “በሴትነታቸው ሰው እንዳይፈትኑ ወይም እንዳይፈተንባቸው እንዳያሰናክሉ ወይም እንዳይሰናከሉባቸው” ያገለግላል፡፡ ይሄ ከትልቅ ማህበራዊ ቀውስ የሚታደግ ልዩ ስርኣት ነው፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እምነታዊ ግዴታ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
2.2. የፀጥታ ስጋቱን በተመለከተ በቅድሚያ ስጋቱ የጋራ ስጋት ነውና የመፍተሄ አቅጣጫውም በጋራ ነው መፈለግ ያለበት፡፡ ይልቅ እንዲህ አይነቱ ሚዛን አልባ እይታ እና “እኛ እናውቅልሃለን” ነው የስጋት ምንጭ ለሆኑ አካላት ምክኒያት እየሰጠ ያለው፡፡ በትንሽ በትልቁ ማንነቱ የሚደፈርበት፣ እምነታዊ እሴቶቹ ኢላማ የሚሆኑበት አካል የእምነትና የሞራል ገደብ ሳይገድበው የራሱን ፅንፈኛ አካሄድ በእምነት ስም ሊያራምድ ይችላል፡፡ በተለያዩ የአለማት ክፍል እያየን ያለነውም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከዚህ ጋር ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ይልቁንም መፍተሄው ማግለል ሳይሆን ማሳተፍ ነበር፡፡ ስለሙስሊሟ አለባበስም ብንመጣ በየተቋማቱ ጠባቂዎችና ፈታሾች አሉ፣ ለወንድ ወንድ ለሴት ሴት፡፡ ኒቃብ የለበሰችዋ ሙስሊምም ልክ እንደሌሎቹ ሴቶች የምትፈተሸው በሴቷ ብቻ ነው፡፡ አለቀ፡፡ ለሴቷ ደግሞ ለጉዳዩ የሚያስፈልገውን ያክል ትገለጣለች፡፡ ቀላሉን ነገር አቀበት እያደረግን በሴኩላሪዝም ስም እምነትን ለሚያጠቁ አካላት አጋር ባንሆን መልካም ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ ከኢትዮጵያ በበለጠ አሸባሪዎቹ ጥርሳቸውን የሚነክሱባቸው፣ ከኢትዮጵያ በበለጠም ሽብርን በመዋጋት ስም የሚታወቁ በርካታ የምእራቡ ሀገራት ውስጥም ኒቃብ ይለበሳል፡፡ ኒቃብን ያገደችዋ ፈረንሳይ እራሷ ኒቃብን ለማገድ በቀዳሚነት ስታራግብ የነበረው የሽብር ስጋት ሳይሆን ጭፍን ጥላቻዋን የሚያንፀባርቅ ሌላ ምክኒያት ነበር፡፡
3. የአቀራረብ እርማት፡-
በቅድሚያ የማልደብቀው ነገር ፀሀፊው በእምነት ስም ከሚፅፉ ብዙ ፀሀፊዎች አንፃር ሲታይ ቀላል የማይባል ሚዛናዊነት አይቻለሁ፡፡ ይህን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሚዛናዊ ለመሆን ሲቸገር ብቻ ሳይሆን አላስፈላጊ ቃላት ሲሰነዝርም አስተውያለሁ፡፡ ይሄ ለማንም አይበጅም፡፡ ለምሳሌ እነዚህን ሁለት አ/ነገሮች ያስተውሉ፡- “ሂጃብና ኒቃብ የሚያደርጉ እስላም ሴቶች … በየትኛውም መመዘኛ ሊነጻጸር የማይችል የማይገባ ነገርን ለማነጻጸር በመሞከራቸው አለማወቃቸው ባመጣባቸው ስሕተት ሊያፍሩ ይገባል፡፡” “ስለሆነም ማተብን በሂጃብ ኒቃብ ምንነትና አገልግሎት አንጻር ማየት ፍጹም የተሳሳነና ከድንቁርና የመነጨ ከባድ ድፍረትም ነው፡፡” እንዲህ አይነቱ ያልፀዳና ያጋደለ አቀራረብ ወደ አላስፈላጊ እንካ ስላንትያ ነው የሚያስገባን፡፡ እናም ፀሀፊው በሀሳብ ስላልተጋሩት ብቻ በድንቁርናና በአጉል ድፍረት ለመሸበብ መሞከሩን እርማት ሊወስድባቸው ከሚገቡ ነገሮች ሊያካትተው ይገባል እላለሁ፡፡
4. ፅንፈኛ ሴኩላሪዝም
ሴኩላሪዝም በግርድፉ ሀይማኖት በአስተዳደር ውስጥ አስተዳደሩም በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡ የማድረግ ስርኣት እንጂ ግለሰቦችን እምነት አልባ የማድረግ ስርኣት አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው የሴኩላሪዝም አረዳድና አፈፃፀም ግን አጉራ ዘለል ነው፡፡ ከመንገስት ቀርቶ ሀላፊነት ከሚሰማው ግለሰብም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ በተጨባጭ እየታየ ያለው ልክ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ስርኣቶች እንደሚንፀባረቀው በቃላት ባይገለፅም በተግባር ግን በሴኩላሪዝም ጭንብል እምነትን ለይቶ ማጥቃት ወይም በእምነት ውስጥ ገብቶ ማቡካት ነው፡፡ የሚያሳዝነው መሬት ላይ ያለው እውነታ ሌላ በሚዲያ የሚነገረው ሌላ መሆኑ ነው፡፡ ማንን እንደሚዋሹ እራሱ ግራ ያጋባል፡፡ “የምታዩትን ሳይሆን የምንነግራችሁን እመኑ” የሚል ሀይል የክፉ አካሄዱ ዳፋ ለሀገርና ለህዝብ ቀርቶ ለራሱም እንደሚተርፍ በምን ቋንቋ ቢነገረው እንደሚገባው አላውቅም፡፡
የመጨረሻውን ነጥብ እንዲሁ ሀሳቤን ለመግለፅ ያክል እንጂ ከፀሀፊው ጋር አያይዤ አይደለም ያነሳሁት፡፡ ከዚያ በተረፈ ሀሳቤን የመግለፅ እድሉን የሰጠኝን ጎልጉል የድረ-ገፅ ጋዜጣና በአንፃራዊ መልኩ የተሻለ ሚዛናዊነት ያየሁበትን ፀሀፊ ሳላመሰግን አላልፍም፡፡ “ሰዎችን የማያመሰግን አላህን አያመሰግንም” ይላሉ ነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ውዳሴና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና፡፡)