“ከማግኘቱ በፊት ነገርየውን ያጣደፈ በማጣት ይፈተናል”
ትውልድ አልባኒያ፤ አብዛኛውን ህይወታቸውን ያሳለፉትና ያስተማሩት ሶሪያ ነው፡፡
በአንድ ፈትዋቸው እንዲህ አሉ ...
“… ዛሬ ሙስሊሞች አንደ ህጻናት ሁነዋል፡፡ ካፊሮችን ወይም ግልጽ የሆነ ክህደትን ይፈርዳሉ ብለው የሚያስቧቸውን መሪዎች ለመታገል መነሳት ምን ያህል መጠን ያለው ጉዳይ እንደሆነ የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፡፡ የግድ መዘጋጀት ያለባቸውን እንዳይዘጋጁ የነገሩን ልኬት አያውቁም፡፡
ጉዳዩን ልክ አንድ መቶ፣ ሺህ፣ ሁለት ሺህ ግለሰቦችን ሰብስቦ በአላህ መንገድ እንዲታገሉ ማነሳሳት አድርገው ይገምታሉ፡፡ ይሁንና ጠላታቸውን የሚዋጉበት የጦር መሳሪያ ሊሰሩ ይቅርና የተቀደደ ልብሳቸውን እንኳ የሚሰፉበት መርፌ የመስራት አቅም የላቸውም፡፡ የት ነው ታዲያ በቁርዓን የታዘዝነው ዝግጅት?(2)
ከነዚህ ቡድኖች ተጨባጭ ሁኔታና ውጤታቸውን ካየነው ሌሎች (ቡድኖች) መካከል ያገኘነው ቢኖር --- ይታገላሉ ነገር ግን መጨረሻው በሙስሊሞች ዳዕዋ ላይ ኪሳራ ሲሆን ነው! በመካ ሀረም ከነበረው የጁሀይማን ጀመዓ ጀምሮ በሁለተኛነት የኢስታንቡል ጀመዓ … በሶስተኝነት በሶሪያ የኢኽዋነል ሙስሊሚን መውጣትና በመጨረሻም አልጄሪያዎች፤ ዛሬ የሚደርስባቸው ከቀድሞው የባሰ መከራ፣ ምኑ … እስከመጨረሻው(የሚደርስባቸው ችግሮች ብዙ ናቸው)፡፡
ከዚህ ችኮላ ኢስላማዊው ዳዕዋ ምን ተጠቀመ?
ነገርየው እንደ ጥበብ የምንቆጥራቸውን አንዳንድ አባባሎች ከማረጋገጥ በቀር፡፡ ከነዛ አባባሎች 'ከማግኘቱ በፊት ነገርየውን ያጣደፈ በማጣት ይፈተናል' ዛሬ ሙስሊሞችን እያጋጠመ ያለው ይህ ነው…”
ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ካ.ቁ. 790 --- 1993 እ.ኤ.አ (3)
_________________________________
1. ሸይኽ ዓብደል ዓዚዝ ዚብን ባዝ ስለ ሸይኽ አልባኒ እንዲህ ብለዋል“በኔ ግምት ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አል-አልባኒ የዚህ ዘመን ሙጀዲድ ነው! ወላሁ አዕለም”
ሸይኽ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ደግሞ “የተገናኘነው ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ከሸይኽ (አልባኒ) የማውቀው ቢኖር በዓቂዳም ይሁን በተግባራት ላይ በሱና ለመስራትና ቢድዓን ለመፋለም በጣም ተነሳሽ መሆኑን ነው፡፡”
2. “ከሀይልም በቻላችሁት ሁሉ ተዘጋጁላቸው” አኒሳእ-60
3. ይህ ፓስት እንደ ሸይኹ ንግግር ጥቅል መልዕክትን ለማስተላልፍ እንጂ ለተወሰነ ቦታና ሁኔታ የተዘጋጀ አይደለም!
ይበልጥ ጠቃሚ ትምህርት ለማግኘት 'አል-ፈታዋ አል-ሙሂማ ሊል-አልባኒ' የተሰኘውን ኪታብ ከገፅ 609 ጀምረው ይመልከቱ።
Mohammed Ibrahim Ali

0 Comments