Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ አልባኒ vs ሸይኽ የህያ አልሀጁርይ

ሸይኽ አልባኒ vs ሸይኽ የህያ አልሀጁርይ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በአንድ ወቅት "ሀዚሂ ዳዕወቱና " በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ሸይኽ አልባኒን ወደ መድረክ ሊጋብዝ መድረክ መሪው ንግግሩን ሲከፍት ይህን ነበር ያለው "…በአላህ ይሁንብኝ ይህች ሰዓት ከትልቁ ሸይኻችን ፣ ዓሊማችን እና ኡስታዛችን ክቡር ሸይኽ ሙሀመድ ነስሩዲን አልባኒ ጋር ቆይታ የምናደርግበት ያማረች ሰዓት ናት… ሁሉም እሳቸውን ለማየት ጓጉቷል እንዴት አይጓጓም ሁላችንም እርሱ ዘንድ ካለው የዒልም ማዕድ እና ሂክማ በአላህ ፈቃድ ለመስማት ጓጉተናል። …እርሱ ዘንድ አላህ ከሰጠው የእውቀት ፀጋ አብረን እንቋደስ (እንስማ)…" [ በግርድፉ]
መድረኩ ሸይኽ አልባኒ ተረከቡና አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ እንዲሁም በመልክተኛው ላይ ሰላምታ ካወረዱ በኋላ ግና እያለቀሱ እንዲህ በማለት ነበር ንግገራቸውን የጀመሩት [ " ወንድማችን ኡስታዝ ኢብራሂም ላደረገው ንግግርና ውዳሴ አመሰግነዋለሁ ። በበኩሌ እውነተኛውና የመጀመርያው የመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምትክ አቡበከር ሲዲቅ ድንበር ባለፈ ቃል አንዱ ባወደሰው ጊዜ ያለውን ከማለት ሌላ የምለው የለኝም ። ምንም እንኳ አቡበከር ለውዳሴው ተገቢ ቢሆንም እንኳ እንዲህ ነበር ያለው ’አላህ ሆይ እነርሱ በሚሉት ነገር አትያዘኝ ፤ ከሚያስቡት በላይ መልካም አድርገኝ ፤ በማያውቅት ነገር ማረኝ’ የአቡበከር ፋና በመከተል እኔም የምለው " አላህ ሆይ እነርሱ በሚሉት ነገር አትያዘኝ ፤ ከሚያስቡት በላይ መልካም አድርገኝ ፤ በማያውቅት ነገር ማረኝ ’
በርግጠኝነት እላችዋለሁ አሁን ክቡር ወንድማችን እንደገለፀው ሳይሆን እኔ እውቀት ፈላጊ እንጂ ሌላ አይደለሁም። ሁሉም እውቀት ፈላጊ ዘንድ በሰሂህ ቡኻሪ ከአብደላህ አብን አምር እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ "ከኔ የሰማችሁትን አንድም አያ ቢሆን አስተላልፉ… " ለዚህ ነብያዊ ትዕዛዝ መልስ ለመስጠት እና ሰዎች የማያውቁትን ለማድረስ በምናደርገው ጥረት ወንድሞቻችን በጥሩ እንደሚገምቱን አይደለንም " ] ካሴቱ ላዳመጠ በርግጠኝነት የዳዕዋው ርዕስ ተቀየረ እንዴ ? ብሎ ማሰቡ አይቀሬ ነው ። አዎ ሰዎች በርሳቸው ላይ ያላቸው አመለካከት ድንበር እንዳያሳልፋቸው በማሰብ ሸይኽ አልባኒ የተመረጠላቸውና የተዘጋጁበትን ርዕስ ወደ ኋላ በማዘግየት "ጥሩ ሲጠፋ ይመለመላል ጎባጣ ወይም ጋኖቹ አለቁና ምንቸቶቹ ጋን ሆኑ " በሚመስል አገርኛ ተረት ራሳቸውን እጅግ በጣም ሲያሳንሱ የሚከተለውን ነበር የተናገሩት

إن البغاث في أرضينا يستنسير
ማለትም ነስር በሌለበት ምድራችን ላይ እርግቦች ነስር ሆኑ ዓይነት አባባል ።
ልብ በሉ በነ ኢማም ኢብን ባዝ አንደበት "ከሰማይ በታች ሀዲስ እንደርሱ የሚያውቅ አላውቅም " ተብሎ የተመሰከረላቸው የዚህ ዘመን ብርቅዬ ሙሀዲስ ደረጃቸውን ሲገልፁ የአዋቂ ቁጥር ባነሰበት ወይም በጠፋበት ዘመን መገኘቴ እንጂ እኔ አዋቂ አይደለሁም ማለታቸው እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህን በሰማችሁበት ጆሯችሁ ወይም ባነበባችሁበት አይናችሁ በተማሪዎቹ ዘንድ ብቻ የዚህ ዘመን ሙሀዲስ ፣ ፈቂህ ፣ ኢማሙ ጀርህ ወታዕዲል ከዚህም ሲያልፍ ’ኢማሙ ሰቀለይን እንደው ቢሟሟ (ቢቀልጥ) ስጋው የቁርዐን አንቀፅና የመልክተኛው ሀዲስ ይሆን ነበር ’ የሚል የመሀይማን አድናቆት የተቸረው ሸይኽ የህያ አልሀጁርይ አላህ ይምራውና የገዛ ተማሪው በግጥም እንደሚከተለው ነበር ያደነቀው
ﻳﺎ ﺷﻴﺨﻨﺎ ﻳﺮﻋﺎﻙ ﺭﺑﻲ ﺇﻧﻨﻲ ﻻ ﺃﺑﺘﻐﻲ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﺃﻧﺖ ﺭﺣﻴﻞ ﺃﻗﺴﻤﺖ ﺃﻧﻲ ﻟﻮ ﻣﺴﺤﺖ ﺣﺬﺍﺀﻩ ﻃﻮﻝ ﺍﻟﺤﻴﺎﺓ ﻟﻜﺎﻥ ﺫﺍﻙ ﻗﻠﻴﻞ
(ግጥሙ በአማርኛ ቤት እንዲመታ በግርድፉ ሲተረጎም ይህን ይመስላል)
(ሸይኻችን ሆይ! አላህ ይጠብቅህ አንተ ብትሄድ ( ብትሞት) ዱንያ ለምኔ ፥ እምላለሁ ጫማህ እየጠረግኩ እድሜ ልኬን ብኖር ይቀለኛል ለኔ። )
ይህ ግጥም በውስጡ ድንበር ማለፍ ያለበት ፤ በመሠረቱ ፊት ላይ አፈር የሚያስረጭ ሆኖ ሳለ ሸይኹ ግን የአላህና የመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ማስጠንቀቂያዎች ችላ በማለት ይልቁንም ተማሪው ይህንን ቀሲዳ (ግጥም) ሲጨርስ የሚከተለውን ነበር ያለው
ﺟﺰﺍﻙ ﺍﻟﻠﻪ ﺧﻴﺮﺍ ﻭﻧﻔﻊ ﺑﻚ ﺃﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻨﺎ ﻭﻟﻜﻢ ﺍﻟﺘﻮﻓﻴﻖ
አላህ ጥሩ ይመንዳህ እና (ለሌሎች) ጠቃሚም ያድርግህ ። ላንተም ለእኔም የአላህ ስኬት ይገጥመን ዘንድ አላህን እለምነዋለሁ።
ከቶ ምን የሚሉት ኩትኮታ (ተርቢያህ) ነው? ሰው በውዳሴ ድንበር ሲያልፍ ሰምቶ ዝም ማለት ። ለነገሩ ተማሪው ይህን ከማለት ሌላ ምን አማራጭ አለው ሸይኹ ከርሱ ውጭ ያሉትን በሙሉ አጥማሚ እንደሆኑ ነገረውና ጉዳዩ ሁሉ " አባይን ያላየ ምንጭን ያደንቃል " ሆነበት ። አላሁ ሙስተዐን

Post a Comment

0 Comments