#የኢኽዋን_ውንጀላ_በነቢያቶች_ላይ
በወንድም Namus Abdella የተሰጠ ድንቅ ምላሽ
ኢኽዋኖች የሚወነጅሉት ሳዑዲ እና ዑለሞችዋን ብቻ አይደለም መልክተኞችንም ጭምር እንጂ
።።።።።።።።።
ውንጀላ ቁጥር አንድ
1) #ነቢዩላህ_ሐሩን_ዐለይሂ_ሰላም
"አንድነትን የሚበታትን ከሆነ ተውሂድም ቢሆን ይተዋል። " አሉ የኢኽዋን ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የተሰራጨ ሰዎች ።
በምን ማስረጃ? ተጠየቁ
የቁርዐን አንቀጽና የመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሀዲሶች ማንሸዋረር በለመደው ምላሳቸው " ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ወደ ጡር ተራራ በሄደ ጊዜ ወንድሙ ሐሩንን መተካቱ ይታወሳል ። ይህን ጊዜ ነበር ሳሚሪይ የፈለሰፈው ጣኦት (ጥጃውን) በኒ ኢስራኢሎች እያመለኩ እያየ ለአንድነታቸው በመስጋት ሐሩንም ዝም ያለው " አሉ የሚከተለው የቁርዐን አንቀጽ በኢኽዋን ቫይረስ በተጠቃው ጠባብ አዕምሯቸው አቅጣጫውን በመጠምዘዝ ።
(قَالَ يَا ابْنَ أُمَّ لَا تَأْخُذْ بِلِحْيَتِي وَلَا بِرَأْسِي ۖ إِنِّي خَشِيتُ أَنْ تَقُولَ فَرَّقْتَ بَيْنَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَمْ تَرْقُبْ قَوْلِي) [طه ٩٤ ]
ጥራት ለአላህ ተገባ ይህ የኢኽዋን ውንጀላ ከመልክተኞች ክብርና ስብዕና እንዲሁም ከተላኩበት ዓላማ ጋር እጅጉን ተቃራኒ ነውና።
ወንድምና እህቶች ሆይ በመጀመርያ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቁርዐንና ሀዲስን የምንገነዘበው ከመልክተኛው አንደበት በቀጥታ (lively) ከአላህ እንደተወረደ በተረዱ የዚህ ኡማ አበው ትውልዶች (ሰለፉና ሷሊሒን) ግንዛቤ መሠረት ብቻና ብቻ ነው። ይህ ከሆነ አዕምሯችን ምንም ዓይነት ጥበት እና ጭንቀት አያገኘውም ። ለአላህ ምስጋና ይገባውና ሰለፎቹ የተገነዘቡት ግንዛቤ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ በጠንካራ ሰነድ (chain) እኛ ዘንድ ደርሷል። ለዛሬ በነቢዩላህ ሐሩን ላይ የተቀጠፈው ቅጥፈት እንመርምር ።
ነቢዩላህ ሙሳ አላህ ሊያናግረው በቀጠረው ጊዜ በቦታው ተተኪ በማደረግና የሰዎችን ጉዳይ በጥቅሉ እንዲያሰተካክል (በመልካም እንዲያዛቸው ከመጥፎ እንዲከለክላቸው ) እና የአጥፊዎችን (የአጋሪዎችና የቢድዓ ባልተቤቶች) መንገድ እንዳይከተል ወንድሙ ሐሩንን አደራ በማለት ወደ ቀጠሮው ቦታ ሄደ።
( وَقَالَ مُوسَىٰ لِأَخِيهِ هَارُونَ اخْلُفْنِي فِي قَوْمِي وَأَصْلِحْ وَلَا تَتَّبِعْ سَبِيلَ الْمُفْسِدِينَ)
[الأعراف ١٤٢ ]
" ሙሳም ለወንድሙ ሐሩን " በሕዝቦቼ ላይ ተተካኝ፣ አሳምርም (በመልካም እዘዛቸው ከመጥፎም ከልክላቸው) ፤ የአጥፊዎች (የአጋሪዎችና የቢድዓ ባልተቤቶች) መንገድ አትከተል። " አለው "
ታዲያ ሙሳ ወደ ቀጠሮው ቦታ ሲሄድ ነበር በኒ ኢስራኢሎች በሳሚሪይ የተሰራውን ጥጃ ማምለክ የጀመሩት ። ሐሩንም አላህን የጣለበት ግዴታ እና የወንድሙ ሙሳም አደራ በማስታወስ ሰዎቹ ሲጠሙ ሽርክ ላይ ሲወድቁ አይቶ ዝም አላለም እንዲህ ቢላቸው እንጂ
(وَلَقَدْ قَالَ لَهُمْ هَارُونُ مِنْ قَبْلُ يَا قَوْمِ إِنَّمَا فُتِنْتُمْ بِهِ ۖ وَإِنَّ رَبَّكُمُ الرَّحْمَٰنُ فَاتَّبِعُونِي وَأَطِيعُوا أَمْرِي) [طه ٩٠ ]
" በርግጥ ከዚህ በፊት ሀሩን እንዲህ አላቸው "ሕዝቦቼ ሆይ !(ይህ ጥጃ ) የተሞከራችሁበት (የተፈተናችሁበት) ነገር ነው። (ልታመልኩት ተገቢ የሆነው) ጌታችሁ አረህማን ብቻ ነው ፤ ተከተሉኝ ፤ ትዕዛዜንም አክብሩ ""
ሆኖም ግን ሊሰሙት አልቻሉም ይልቁንም እርሱን በማዋረድና በማሳነስ ሊገድሉት ሁሉ አሰቡ።
( ابْنَ أُمَّ إِنَّ الْقَوْمَ اسْتَضْعَفُونِي وَكَادُوا يَقْتُلُونَنِي فَلَا تُشْمِتْ بِيَ الْأَعْدَاءَ وَلَا تَجْعَلْنِي مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ) [ الأعراف ١٥٠]
"የናቴ ልጅ ሆይ! ሕዝቦቼ ናቁኝ ፤ ሊገድሉኝም ተቃረቡ ። ስለዚህ በእኔ ጠላቶችን አታስደስትብኝ ፤ ከአመፀኛ ሕዝቦችም አታድርገኝ " አለው።"
በኒ ኢስራኢሎች ግን እስቲ የምታመጣውን እናያለን በሚመስል ዓይነት ስሜት እንዲህም አሉት
(قَالُوا لَنْ نَبْرَحَ عَلَيْهِ عَاكِفِينَ حَتَّىٰ يَرْجِعَ إِلَيْنَا مُوسَىٰ ] [ طه ٩٤ ]
"ሙሳ ወደኛ እስኪመለስ (ጥጃውን) ከማምለክ አንወገድም አሉ።"
ሙሳም ቀጠሮውን አጠናቅቆ ሲመጣ በሕዝቦቹ መሀከል የተፈጠረው ጥመት እጅግ በጣም ስላናደደውና ስላስቆጣው በእጁ የያዘውን ሰሌዳ በመወርወር የወንድሙን ፀጉርና ፂም ሰብስቦ በመያዝ እና ወደ ራሱ ጎትቶ በማስጠጋት እንዲህም አለው
(قَالَ يَا هَارُونُ مَا مَنَعَكَ إِذْ رَأَيْتَهُمْ ضَلُّوا * أَلَّا تَتَّبِعَنِ ۖ أَفَعَصَيْتَ أَمْرِي) [ طه ٩٢ـ٩٣ ]
"(ሙሳ) አለ አንተ ሐሩን ሆይ! ሲጠሙ ባየህ ጊዜ ልትከለክላቸው ምን ከለከለህ ? እነን ከመከተል ትዕዛዜን ጣስክን?
የወንድሙን ትዕዛዝ እንዳልጣሰና ምንም እንኳ አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ዳዕዋ ቢያደርግላቸውም ሰዎቹ ግን ሊታዘዙት ፍቃደኞች አልነበሩም ። በሽርክ እና ቢድዓ ላይ ሆነው አንድነታቸው እንዳይበታተን ፤ ሙሳ እስኪመለስ ብሎም ዝም አላለም ። ፍፁም ከተላከበት ዓላማ ተቃራኒ ነውና። ነብያት የተላኩበትን ዓላማ ፍፁም ዘንግተው አያውቁም፤ ትእዛዙ ከበላይ ነውና። በትረ–ስልጣኑን ለመቆናጠጥ ብቻ ዓላማቸውን ያደረጉት ኢኽዋኖች እና ተዛማጆቻቸው ግን በጠባብ አእመሯቸው ወነጀሉት፤ ሰው ሁሉ እንደራሳቸው መሰሏቸው። እውን የአንቀጹ ግንዛቤ ኢኽዋኖች እንደሚሉት ወይስ ሌላ [" ተይሲሩል ከሪሚ ረህማን ፊ ተፍሲሪ ከላሚል መናን (የሸይኽ አብዱረህማን ሳዕድይ (1307_1376 ዓ·ሂ) " መክተበተ ቁድስ የመጀመርያ ዕትም ገፅ 514 ] ያለውን እንመልከት
فإنك أمرتني أن أخلفك فيهم، فلو تبعتك لتركت ما أمرتني بلزومه وخشيت لائمتك، و ( أَنْ تَقُولَ فَرَّقْتَ بَيْنَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَمْ تَرْقُبْ قَوْلِي) حيث تركتهم، وليس عندهم راع ولا خليفة، فإن هذا يفرقهم ويشتت شملهم،
("አዎ በነሱ ላይ ተተኪ አድርገኸኛል ፤ በአንተ ቦታ ሆኜ በመልካም እንዳዛቸው ከመጥፎ እንድከለክላቸው አዘኸኛል ። ያለምንም ጠባቂ እና ተተኪ ትቻቸው ወደ ሄድክበት የተከሰተው ነገር ልነግርህ ብከተልህ ኖሮ የጣልክብኝ ግዴታ አልተወጣሁምና "በኢስራኢል ልጆች መሀከል ለያየህ (ያለምንም ጠባቂ ወይም ዳዕዋ አድራጊ ትተሀቸዋል።) ፤ ትዕዛዜንም አላከበርክም ብለህ " ትወቅሰኛለህ ብዬ ፈራሁ ። ደግሞም እነርሱን ያለምንም ጠባቂና ተተኪ መተዉ ይለያያቸዋል አንድነታቸውም ይበታትንባቸዋል ። ሆኖም ሊሰሙኝ አልቻሉምና በድርጊትህ (አንተ በኔ ላይ በምትወስደው እርምጃ ) ጠላትን አታስደስት አለው።")
ተፍሲር ኢብን ከሲር ውስጥ ያለው የአንቀጹ ትርጉምም እንደሚከተለው ነው
هذا اعتذار من هارون عند موسى في سبب تأخره عنه ، حيث لم يلحقه فيخبره بما كان من هذا الخطب الجسيم قال ( إني خشيت ) أن أتبعك فأخبرك بهذا ، فتقول لي : لم تركتهم وحدهم وفرقت بينهم ( ولم ترقب قولي ) أي : وما راعيت ما أمرتك به حيث استخلفتك فيهم .
… ተከትዬህ መጥቼ የተከሰተውን ነገር ልነግርህ ለምን ብቻቸው ትተሀቸው እና በታትነሀቸው መጣህ ? በነርሱ (በኢስራኢል ልጆች ላይ) ተተኪ አድርጌህ ባስጠበቅኩህ ጉዳይ ላይ አልጠበቅክም ብለህ ትወቀሰኛለህ ብዬ ፈራሁ ። ይህ ነበር የሐሩን ምክንያት ሙሳ ዘንድ የተናገረው እንጂ አዲስ ባመጡት ጥመት ብገስጣቸው አንድነታቸው ይበታተናል ፤ ሙሳ ሲመለስ ለምን ስለ ተውሂድ ጥሪ አደረግክ ብሎ ይወቅሰኛልን ፈርቶ አይደለም ። እንዴትስ ይሆናል ? መልክተኞች የተላኩበት ዓላማ ተውሂድ ሆኖ ሳለ
(وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ ) [ الأنبياء ٢٥ ]
"ከአንተ በስተፊት ከመልክተኛ አንድም አላክንም ወደርሱ እነሆ ከኔ ሌላ የሚመለክ የለምና አምልኩኝ (በማለት) ወህይ ያደረግን ቢሆን እንጂ"
ውንጀላ ቁጥር ሁለት
2) #አሽረፈል_ኸልቅ_ሙሐመድ_ሰለላሁ_ዐለይሂ_ወሰለም
የኢኽዋኖች ውንጀላ በነብዩላህ ሐሩን (ዐለይሂ ሰላም) አያበቃም የሰው ልጆች ሁሉ አለቃና የነብዮች መደምደሚያ የሆኑት ነብያችንንም ( ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ቢያካትት እንጂ ። ይህን አሉ ኢኽዋኖች " አንድነት የሚበታትን ኃይል ሲመጣ ተውሂድ ተትቶ ሰዎች ስለተውሂድ ምንም ሳያውቁ ለአደባባይ ሰልፍና አመፅ እንዲሁም ለጂሀድ ማሰለፍ ይቻላል።" በምን ማስረጃ ሲባሉ "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሁነይን ዘመቻ ቀን ስለ ተውሂድ ምንም የማያውቁ አዳዲስ ሰለምቴዎችን አሰልፈዋል እንዲያውም በሆነ ዛፍ አጠገብ ሲያልፉ ለአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ’ ሙሽሪኮች ለበረከት መሳሪያ ማንጠልጠያ እንዳላቸው ለኛም አድርግልን’ ብለው ጠየቀዋል ። ከዚህ የምንረዳው" አሉ ኢኽዋኖች " ስለ ተውሂድ ምንም የማያውቀው ሰው ጠላት በመጣ ጊዜ ባለበት ሁኔታ ታሰልፈዋለህ አራት ነጥብ" በርግጥ ይህ የታሪኩን መነሻና መድረሻ የማያውቅ የተራ ግለሰብ ፍልስፍና እንጂ ሌላ አይደለም። እስቲ ስለ ታሪኩ (ከቀውሉል ሙፊድ እና ከፈትሁል መጂድ ) እናገላብጥና እንየው ። ሀዲሱ ኪታቦቹ ውስጥ እንደሰፈረው ፦
«عَنْ أَبِي وَاقِدٍ اللَّيْثِيِّ، قَالَ: خَرَجْنَا مَعَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآلِهِ وَسَلَّمَ إِلَى حُنَيْنٍ -وَنَحْنُ حُدَثَاءُ عَهْدٍ بِكُفْرٍ-، ولِلْمُشْرِكِينَ سِدْرَةٌ يَعْكُفُونَ عِنْدَهَا، ويَنُوطُونَ بِهَا أَسْلِحَتَهُمْ يُقَالُ لَهَا: ذَاتُ أَنْوَاطٍ، قَالَ: فَمَرَرْنَا بِالسِّدْرَةِ، فَقُلْنَا: يَا رَسُولَ اللهِ, اجْعَلْ لَنَا ذَاتَ أَنْوَاطٍ كَمَا لَهُمْ ذَاتُ أَنْوَاطٍ، فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وآله وَسَلَّمَ: اللهُ أَكْبَرُ، إِنَّهَا السُّنَنُ، قُلْتُمْ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ كَمَا قَالَتْ بَنُو إِسْرَائِيلَ: ﴿اجْعَلْ لَنَا إِلَهًا كَمَا لَهُمْ آلِهَةٌ قَالَ إِنَّكُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ﴾ [الأعراف: 138]، لَتَرْكَبُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ» رواه الترمذي وصححه
ሁነይን ዘመቻ ፦
።።።።።።።።።።።
፨ መካ ከተከፈተ በኃላ
፨ 12,000 ተሳታፊ የተገኘበት
፨ ከብዛት በኩል ዛሬ አንሸነፍም ቢሉም አላህ ድል በብዛት እንዳልሆነ የገለፀበት
፨ የሆነውን ሆኖ በስተመጨረሻ ላይ ከነብዩ ጋር የቀሩ ሰሀቦች 100 አካባቢ ሲሆኑ በስተመጨረሻ ላይ ግን ድሉ ለመልክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነበር። [ቀውሉል ሙፊድ]
ጥያቄያቸው
።።።።።።።።
"ሙሽሪኮች ከርሷ በረካ ፍለጋና እርሷን ለማላቅ የመሳርያ ማንጠልጠያ እንዳላቸው ለኛም አድርግልን " [ፈትሁል መጂድ]
ይህን መሠል ጥያቄ ለምን ጠየቁ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አቢ ዋቂዲ ለይሥይ እንደተናገረው እነርሱ ገና ለእምነቱ አዲስ መሆናቸው።
[ ከዚህ የምንረዳ ዑዝር ቢልጀህል አለ]
የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ምላሽ፦
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከነዚህ ውጭ ካጠገቤ ሌላ ከጠላት የሚካላከልልኝ የለምና ንግግራቸውን ባወግዝባቸው ብቸኛ እሆናለሁ ፤ ከፊት ለፊት ያለው ጠላት ያጠቃኛል የሚል ፍርሀት አላሸነፋቸውም። ይልቁንም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለእምነቱ አዲስ ሰሀቦች የተናገሩት ነገር በማውገዝ "አላሁ አክበር ይህች የቀደምት ህዝቦች መንገድ ናት። ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ የጠየቃችሁት ጥያቄ በኒ ኢስራኢሎች ሙሳን የጠየቁት ዓይነት ነው [(እነርሱም) ’ሙሳ ሆይ! ለእነርሱ (ለሰዎቹ) አማልክት እንዷላቸው ለኛም አምላክን አደርግልን’ (አሉት) (ሙሳም) ’እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናችሁ ’ አላቸው። ] ብለው ምሳሌ በማከል እዚያው ቀውጢ ቦታ ነበር ተውሂድን ያስተማርዋቸው። ከድል በኃላ እንደርስበታለን አሁን ወደ ፊት አላሉም ይልቅ መለኮታዊ ግዴታቸው ቢወጡ እንጂ የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን።

0 Comments