Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢስላማዊ ነሺዳ ሁክሙ ምንድን ነው? በሸህ ሷሊህ አልፈውዛን (አላህ ይጠብቃቸው)

በወንድም ሳዳት ከማል የተዘጋጀ::
ኢስላማዊ ነሺዳ ሁክሙ ምንድን ነው?
በሸህ ሷሊህ አልፈውዛን
(አላህ ይጠብቃቸው)
★ይህ ጠያቂ እንዲህ ሲል ይጠይቅዎታል
ሸይኽ:
" ያለ ሙዚቃ መሳሪያና ያለ ድቤ በህብረት ስለሚዜሙት
ኢስላማዊ ነሺዳዎች ምን
አስተያየት አለዎት?
★" ምንም መሠረት አናውቅላትም ለዚች ነገር.... ይህች ፈጠራ
ነች ወደ ኢስላም
ከተጠጋና " ኢስላማዊ ነሺዳ " ከተባለ....
እስልምና ደንግጎታል ማለት ነው ነገር
ግን ይህ ምንም መሠረት የለውም
እንዲሁም ደግሞ ይህ ነሺዳ ለአምልኮና ወደ አላህ
ለመቃረቢያነት ከሆነ የተዘጋጀው
ይህ ከሱፊያዎች መገለጫ ነው እነሱ ( ሱፊያዎች ) ናቸው
አናሺድን የሚይዙት
ለአሏሁ ( ዐዝ-ዘወጀል-ለ)
ጥሩው ነገር ሙስሊም ፊቱን ወደዚህ ነገር ማዞር የለበትም
አዎ: ግጥም መግጠም {{ ጠቃሚ የሆነን}} ምንም ችግር
የለውም በህብረትና በዜማዊ
ቅላጼ ሳይሆን አንድ ሰው ለብቻው ሆኖ ነሺዳ ቢል ችግር
የለውም ግጥም ሰዎችን
ይጠቅማል ከሱ ጥቅም ይወሰዳል ልክ በነቢያችን (ሰለሏህ
ዐለይሂ ወሰለም)
ጊዜገጣሚዎች እንደነበሩት ማለት ነው ግጥምቻቸውን
ያነቡላቸዋል ነቢያችንም
ይሰሟቸዋል ( ሰለሏህ ዐለይሂ ወሰለም)
አንደዚሁ ደግሞ : በስራ ሰዐትና መስራት ሲደብራቸው:
እንዲያነቃቃቸው ሰለ ስራቸው
ሁኔታ ያንጎረጉራሉ ይህ ደግሞ ነሺዳ አይባልም ይህ አጭር
የሆነና ስራ ላይ
ተነሳሽነታቸውን የሚጨምር ነው እና እነዚህ ዜማዎች በእንድ
አይነት ድምጽ
በአዝማች ወይም በተለያዩ የድምፅ ቅላፄዎች ወ.ዘ.ተ የታጀቡ
አይደለም::
እነዚህ ሁሉ መጤ ነገሮች ናቸው::
ወደ ኢስላም ካልተጠጋ ( ኢስላማዊ ካልተባለ)
" ለህው " ነው
ወደ ኢስላም ከተጠጋ ( ኢስላማዊ ከተባለ) ግን "ቢድዐ" ነው::
★ሸይኽ አሏህ ይጠብቆዎትና አንዳናድ ሰዎች እነዚህን ነሺዳዎች
ልምድ አድርገው
ይዘዋቸዋል::
መኪናቸው ውስጥ : ቤታቸው ውስጥ : ከልጇቻቸው ጋር...
ማለትም ሙሉ
ጊዜያቸውን እዚህ ነገር ላይ አድርገዋል::
★ይህቺ ነገር ምንም መሰረት ስለሌላት ይቺ "ፊትና" ነች
እና ታላቁን ቁርአን
ሊያዳምጡ ይገባቸዋል እየተቀራ በድምጽ የተቀዳውን በቪዲዮም
የተቀረፀውን ለነሱ
የሚበቃቸውን በቂ የሆነ ነገር እዛ ውስጥ አለ ለነሱ ይበቃቸዋል
እንደዚሁም ደግሞ
ሙሀደራዎችንና የዲን ትምህርቶችን ያዳምጡ ጊዜውን በአናሺድ
አይግደል ከዚህ
( ከነሺዳ) ጊዜያዊ ደስታንንጂ ምንም እይገኝም::
"ቢድዐ" ማለት ሰለፎቻችን ያልሰሩት ከጊዜ በሗላ ሰዎች ፈጥረው
ወደ እስልምና ያስጠጉት የአምልኮ ተግባር ነው::
"ለህው" ማለት ደግሞ ማንኛውም አታላይ የሆነ ወሬ ወይም
ዝባዝንኬ የሆነ ወሬ
ነው:

Post a Comment

0 Comments