Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተውሒድ ዳዕዋን እያደናቀፈ ያለው የነማን ጽንስ ሀሳብ ነው መልሱን ከሽይኽ ፈውዛን የ አል ኢርሻድ ኪታብ


ይህ ያለንበት ዘመን የትክክለኛው የዳዕዋ ስልት የተድበሰበሰበት ዘመን ነው። ብዙዎቹ በዳዕዋ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎች ዐቂዳን ችላ በማለት ያለ “አቂዳ” ቅንጣት ፋይዳ ሊኖራቸው ለማይችሉ ነገሮች የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ። ሰዎች በመቃብሮች ዙሪያ ታላላቅ የሽርክ ተግባራትን ሲፈፅሙና ከቢድዐና ከንቱ እምነቶች ውስጥ ተዘፍቀው እየተመለከቱ፥ የጥመት አቀንቃኞች ወደ ጥፍት ሲነዷቸው እያስተዋሉ በዝምታ ይመለከታሉ።

በአሁኑ ዘመን አብዛኞቹ የዳዕዋ ሰዎች ለዐቂዳ ተገቢውን ትኩረት አይሰጡም። ይባስ ብሎ ከመካከላቸው፦« የሰዎችን እምነት አትንኩ፤ አመለካከታቸውን አትተቹ።አንድነታቸውን ጠብቁ። አትበትኗቸው። በምንስማማበት ነጥብ ላይ እንረዳዳ፣ በምንለያይባቸው ነጥቦች ላይ ደግሞ እንቻቻል።» እና መሰል ፅንሰ ሐሳቦችን ያዘሉ ጥሪዎችን የሚያቀርቡ ወገኖች አሉ። ይህ አመለካከታቸው ከተከታዩ ቁርአናዊ ቃል ጋር ይቃረናል፦

ۖ ﻓَﺈِﻥْ ﺗَﻨَﺎﺯَﻋْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺷَﻲْﺀٍ ﻓَﺮُﺩُّﻭﻩُ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ
ﻭَﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺑِﺎﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﻟْﻴَﻮْﻡِ ﺍﻟْﺂﺧِﺮِ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺧَﻴْﺮٌ
ﻭَﺃَﺣْﺴَﻦُ ﺗَﺄْﻭِﻳﻠًﺎ )
[ Surat An-Nisa : 59]
፤ በማንኛውም ነገር
ብትከራከሩ በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ
(የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው
መልሱት ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው።
(አል ኒሳእ: 59

እውነተኛ አንድነት የሚመነጨው የአላህን ቁርአንና የነቢዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሐዲስ በመከተል፣ እነርሱን ተቃርኖ ከተገኘ ነገር ሁሉ በመታቀብ ነው።
አላህ እንዲህ ብሏል፦

(ﻭَﺍﻋْﺘَﺼِﻤُﻮﺍ ﺑِﺤَﺒْﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻔَﺮَّﻗُﻮﺍ
[Surat
Aal-E-Imran : 103]

የአላህንም (የማመን) ገመድ ሁሉችሁም ያዙ፤ አትለያዩም፤
(አሊ ዒምራን: 103

ይህ ኡማም ስኬታማ ሊሆን የሚችለው የመጀመሪያው ኢስላማዊ ትውልድ የተከተለውን ጎዳና ሲከተል ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ትክክለኛውን ጎዳና የሚያመላክተው አላህ ብቻ ነው። በአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይስፈን።

(ዶ/ር ሷሊህ ቢን ፈውዛን ቢን ዐብደላህ አል ፈውዛን)
ከአል ኢርሻድ ኪታባቸው ላይ መቅድም ብለው ካሰፈሩት ፅሁፍ የተወሰደ።
 

Post a Comment

0 Comments