Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ያውቃል ነቢ ያውቃል፤ ሰው በከንቱ ይጨነቃል


‹‹አላህ ያውቃል ነቢ ያውቃል፤
ሰው በከንቱ ይጨነቃል››
ይህ አባባል ስንቶች ሲሉት ነበር አሁን ያለው ሁኔታ ባይታወቅም፡፡ ስንኙ ስህተት ነው፡፡ አላህ ብቻ ነው ሙሉ እውቀት ያለው፡፡ የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጌታ አላህ ካሳወቃቸው ውጭ ምንንም አያውቁም፡፡
አላህ ስለ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማንነት እንዲህ ይለናል
قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን᐀ አታስተነትኑምን᐀» በላቸው፡፡
قُلْ إِنِّى لَآ أَمْلِكُ لَكُمْ ضَرًّا وَلَا رَشَدًا
«እኔ ለእናንተ ጉዳትንም ቀጥታንም አልችልም» በላቸው፡፡
قُلْ إِنِّى لَن يُجِيرَنِى مِنَ ٱللَّهِ أَحَدٌ وَلَنْ أَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلْتَحَدًا
«እኔ ከአላህ (ቅጣት) አንድም አያድነኝም፡፡ ከእርሱም ሌላ መጠጊያን አላገኝም» በላቸው፡፡
قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ ۚ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
«አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም፡፡ ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፡፡ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው መጥቶ ‹‹አላህ እና አንተ ያልከው ይሆናል›› ሲላቸው ‹‹ለአላህ ቢጤ አደረግከኝን›› ነበር ያሉት፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በምንም መንገድ ከፈጣሪ አላህ ጋር እኩል አይደረጉም፤ እሳቸው ፍጡር ናቸው፡፡
ስለዚህ የአላህ ባሮች ይህን አባባል እንዲህ አይነት አደጋ እንዳው አውቀን በእምነታችን ጉዳይ ከባድ ጥንቃቄ እናድርግ፡፡ አላህ እርሱን በብቸኝነት በማምለክ ላይ ፅናቱን ይስጠን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው እናም ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments