Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 6


ተውሒድ አል አስማ ወሢፋት

ተውሒድ አልአስማ ወሢፋት ማለት፦

አላህ ለራሡ ያፀደቀውን ወይ ነብዩ
ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም. ሠሒህ በሆኑ ሀዲሦች ያፀደቁትን እነሡ ባፀደቁት
መልኩ ማፅደቅ ነው ከአላህ ያራቁትን ከማራቅ ጋር ይህንን በሚያምንበት ግዜ

1. ሚንገይሪ ተህሪፍ ፦ ተህሪፍ ማለት አንድን ነገር መጀመርያ ከነበረው ፊት
ማዞር ይህ በሁለት አይነት መንገድ ሊከሠት ይችላል

1.1. ቃሉን በመለወጥ ፦ በቃሉ ላይ በመጨመር ፣በመቀነስ ፣እና የቃሉን ሀረካ
(አናቢዎች) በመለዋወጥ የሚደረግ ለውጥ ነው

ለምሣሌ አላህ በቁርአኑ
ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦُ ﻋَﻠَﻯﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ } [ ﻃﻪ : 5 ] ( ﻃﻪ :5)
( አረህማን ከአርሽ በላይ ከፍአለ) (ጠሀ 5 )

ﺇﻟﻰ ﺍﺳﺘﻮﻟﻰ
ወደ (አረህማን ከአርሽ በላይተሾመ) ወደሚል.

ሁለተኛው ትርጉም ከነብዩም ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ፣ከሠሀቦችም ፣
ከታብዕዬችም በአጠቃላይ ከሠለፎች አልተገኘም ስለዚህ ውድቅ ነው

1.2. ትርጉሙን በመለወጥ ፦ አላህ እና. መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
ያልፈለጉበትን ትርጉም በመተርጎም
.ምሣሌ " ﺍﻟﻴﺪ " እጅ አላህ በቁርአን ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በሠሒህ
ሀዲስ አላህ እጅ እንዳለው አስፍረዋል " ﺍﻟﻴﺪ " እጅ የሚለውን በ ሀይል ወይ ፀጋ
በሚል የተረጎመ ከቀደምቶች አንድም የለም ስለዚህ ይህ አተረጓጎም ስህተት
ነው

2 ሚንገይሪ ተዕጢል(ማራቆት) ፦ አላህን ባህሪ አልባ አለማድረግ ። አንዳንድ
የጠመሙ አንጃዎች እንደሚሉት "አላህ ባህሪ የለውም "

∴ተህሪፍ (ማዛነፍ) እና ተእጢል (ማራቆት)የሚለያዩት.
ተህሪፍ. ፦ በሌላ ሸሪአው ባልደነገገውን አዲስ ቃል.ወይም ትርጉም መለወጥ
ማለት ነው. ምሣሌው ላይ እንዳለፈው
ተእጢል ፦ ቃሉን ያለምንም መለወጫ ቃል ትርጉም አልባ ማድረግ.

3 ሚን ገይሪ ተክይፍ.( ሁኔታን ሣንገልፅ) ፦ የአላህን ባህሪዎች ሁኔታቸውን መግለፅ
አንዳንድ አፈንጋጮች እንደሚሠሩት ምሣሌ የአላህ እጅ እንዲህ ነው
ቡሎ መናገር ይህ በጣም ትልቅ ስህተት ነው!! የአላህን ዛት ማንም ሠው
አላየም ማንም ሠው ያላየውን መናገር አይችልም ከተናገረም ይሣሣታል

።ይህም እውቀት ከሠው ልጆች ግንዛቤ እጅጉኑ የራቀ ነው! የሠው ልጅ እንኳን
ስለ ጌታው ስለራሡ አፈጣጠር ጠንቅቆ የማያቅ ደካማ ፍጥረት ስለሆነ ስለ
አላህ ባህሪዎች ሁኔታ ከመናገር ሊቆጠብ ይገባል ።

4 ሚን ገይሪ ተምሢል ፦ አላህ ከሌላ ፍጥረት ጋር ማመሣሠል ምሣሌ አላህ
ሠሚ እንደሆነ ተናግሯል ይህን ንግግሩን አዎ በልቅናው የሚገባው መስማትን
ይሠማል ብሎ ማመን ሢገባው እንደ እንት… ነው የሚሠማው ብሎ አላህ
አምሣያ የሌለው ሀሊቅ ሆኖ ሣለ ለአላህ አምሣያን ማበጀት ነው

በአስማ ወሢፋት ዙርያ እነዚህን ሦስት እምነቶች ያረጋገጠ በአላህ ፍቃድ
ከውዥንብር ፈጣሪዎች ነፃ ይሆናል

1 አላህ እና መልዕክተኛው የገለፁልንን ባህሪ በአጠቃላይ ማመን ።

2 አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን የሡን በሀሪ ከፍጡር ጋር አለማመሣሠል።

3 የአላህን የባህሪዎች ሁኔታቸውን በፍፁም ሊያውቅ ስለማይችል ለማወቅ
አለመሞከር ።

አላህ ካለ ይቀጥላል

Post a Comment

0 Comments