Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 5


☞ እነዚህን ሦስት ሸርጦች እና ሁለት አርካኖች ያሟላ ኢባዳ ከአንድ አላህ ውጪ ላለ ለማንኛውም አካል (ለመላይካ ፣ ለነብይ ፣ ለሦሊሆች… ) አሣልፎ መስጠት አግባቡ አይደለም አሣልፎ የሠጠ ሠው ከእስልምና በቀይ ካርድ ⚀ ይባረራል

☞ ሙሉ ቁርአን(ከመጀመርያው – መጨረሻው ማለት ይቻላል) አምልኮ(ኢባዳ) የአላህ መብት እንደሆነ እና ከሡ ውጪ ላሉ አካላቶች ለአንዳቸውም አሣልፎ መስጠት እንደማይገባ እንዲሁም አሞልኮን (ኢባዳ) ለአላህ ብቻ ያደረጉ ሠዎች በዱንያም በአሔራም የተስተካከለ እና ሠላም የሆነ አኗኗርን እንደሚኖሩ አምልኮን ከሡ ውጪ ላለ አካል አሣልፈው የሠጡ ደግሞ በዱንያ ላይ የጥበት እና የጭንቀት ኑሮ እንዲሁም በአሔራ ደግሞ ከባድ የሆነ እና ዘላለማዊ የሆነ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ይሠብካል ።

☞ ቁርአን አላህን መገዛት እና ከእርሡ ውጪ ያለን አካል አለማምለክ እንዳለብን በተለያየ አገላለፅ ይነግረናል፣ ያበስረናል እንዲሁም ያስጠነቅቀናል ከነዛ ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል

1 እርሡን በብቸኝነት እንድናመልከው እና ከእርሡ ውጪ ሌላን አካል እንዳንገዛ ከገለፀባቸው አናቅፆች መካከል

((ﻭَﺍﻋْﺒُﺪُﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻭَﻻ ﺗُﺸْﺮِﻛُﻮﺍ ﺑِﻪِ ﺷَﻴْﺌﺎ))

(( አላህን ተገዙ በሡም ቅንጣት ታክል እንዳታጋሩ))

2 ፍጡርን የፈጠረው እሡን በብቸኝነት እንዲያመልኩት መሆኑን በመናገር ከገለፀባቸው አንቀፆች መካከል

(ﻭَﻣَﺎ ﺧَﻠَﻘْﺖُ ﺍﻟْﺠِﻦَّ ﻭَﺍﻹﻧْﺲَ ﺇﻻّ ﻟِﻴَﻌْﺒُﺪُﻭﻥ))

((የሠውንም ልጅ ሆነ ጋኔንን እኔን ሊገዙኝ እንጂ አልፈጠርኳቸውም)

3 መልዕክተኞችን የላከበትን ምክንያት በመናገር

ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺑَﻌَﺜْﻨَﺎ ﻓِﻲ ﻛُﻞِّ ﺃُﻣَّﺔٍ ﺭَﺳُﻮﻻً ﺃَﻥِ ﺍﻋْﺒُﺪُﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻭَﺍﺟْﺘَﻨِﺒُﻮﺍ ﺍﻟﻄَّﺎﻏُﻮﺕ

((በእርግጥ ወደ ሁሉም ህዝቦች አላህን ተገዙ ጣኦትንም እራቁ የሚሉ መልዕክተኞችን ልከናል))
َ

4 በመፍጠሩ ብቸኛ በመሆኑ በመመለኩም ብቸኛ እንደሆነ በመናገር

ﻻ ﺗَﺴْﺠُﺪُﻭﺍ ﻟِﻠﺸَّﻤْﺲِ ﻭَﻻ ﻟِﻠْﻘَﻤَﺮِ ﻭَﺍﺳْﺠُﺪُﻭﺍ ﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺧَﻠَﻘَﻬُﻦّ

ለፀሀይ እና ለጨረቃ አትስገዱ ለዛ ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ َ

5 በስም እና በባህሪው ብቸኛ በመሆኑ በመመለኩም ብቸኛ መሆኑን በመናገር

((ﻭَﻟِﻠَّﻪِ ﺍﻵﺳْﻤَﺎﺀُ ﺍﻟْﺤُﺴْﻨَﻰ ﻓَﺎﺩْﻋُﻮﻩُ ﺑِﻬَﺎ))

" ለአላህ መልካም የሆኑ ስሞች አሉት በሦም ለምኑት "

6 ከእርሡ ውጪ የሚመለኩ አማልክቶች ደካማ መሆናቸውን በመናገር

ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﺿُﺮِﺏَ ﻣَﺜَﻞٌ ﻓَﺎﺳْﺘَﻤِﻌُﻮﺍ ﻟَﻪُ ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺗَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠﻪ ﻟَﻦْ ﻳَﺨْﻠُﻘُﻮﺍ ﺫُﺑَﺎﺑﺎً ﻭَﻟَﻮِ ﺍﺟْﺘَﻤَﻌُﻮﺍ ﻟَﻪُ ﻭَﺇِﻥْ ﻳَﺴْﻠُﺒْﻬُﻢُ ﺍﻟﺬُّﺑَﺎﺏُ ﺷَﻴْﺌﺎً ﻻ ﻳَﺴْﺘَﻨْﻘِﺬُﻭﻩُ ﻣِﻨْﻪُ ﺿَﻌُﻒَ ﺍﻟﻄَّﺎﻟِﺐُ ﻭَﺍﻟْﻤَﻄْﻠُﻮﺏ

እናንተ ሠዎች ሆይ! ምሣሌ ተደረገላችሁ ለሡም አድምጡት እነዚያ ከአላህ ውጪ የምትለምኗቸው ቢሠባሠቡ ዝንብ መፍጠር አይችሉም ዝንብ የሆነ ነገር ቢወስድባቸው ማስጣል አይችሉም የሚለመነውም የሚለምነውም ደካማ ነው
7 ከእርሱ ውጪ ያለን አካል የሚገዙትን ሠዎች ጅል መሆናቸውን በመናገር

ﺃَﻓَﺘَﻌْﺒُﺪُﻭﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠﻪ ﻣَﺎ ﻻ ﻳَﻨْﻔَﻌُﻜُﻢْ ﺷَﻴْﺌﺎً ﻭَﻻ ﻳَﻀُﺮُّﻛُﻢْ ﺃُﻑٍّ ﻟَﻜُﻢْ ﻭَﻟِﻤَﺎ ﺗَﻌْﺒُﺪُﻭﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠﻪ ﺃَﻓَﻼ ﺗَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ
ከአላህ ውጪ የማይጠቅማችሁን እና የማይጎዳችሁን ትገዛላችሁን? ለእናንተ እና ከአላህ ውጪ ለምትገዟቸው ለምትገዟቸው "ኡፍ! " አትገነዘቡምን?

8 የሙሽሪኮችን መጨረሻ(መመለሻቸው የከፋ መሆኑን) በመናገር

ﻭَﻳَﻮْﻡَ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ ﻳَﻜْﻔُﺮُﻭﻥَ ﺑِﺸِﺮْﻛِﻜُﻢْ ﻭَﻻ ﻳُﻨَﺒِّﺌُﻚَ ﻣِﺜْﻞُ ﺧَﺒِﻴﺮ

የቂያማ ቀን እናንተ በማጋራታቹ (ተጋሪዎች) ይክዳሉ እንደ ውስጥ አዋቂው ማንም አይነግርህም

☞ እና ሌሎች መንገዶችንም በመጠቀም አላህ በብቸኝነት መመለክ እንዳለበት እንዲሁም ከሡ ውጪ ያሉ አካላትን ማምለክ እንደሌለብን ያስተምረናል

ይቀጥላል

Post a Comment

0 Comments