Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 4


★ የኢባዳ አይነታዎች

⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
☞ የኢባዳ አይነቶች በርካታ ናቸው የተወሠኑትን በአጭሩ በአጭሩ እንመልከት

♙ ዱአ

☞ ዱአ ከኢባዳ አይነቶች ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዝ የኢባዳ አይነት ነው ።ለዚህም ነው ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ያሉት

« ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ﻫﻮ ﺍﻟﻌﺒﺎﺩﺓ »

""ዱአ ኢባዳ ነው "

☞ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላም እሡን እንድንለምነው ሢያነሣሣ እሡን ከመለመን የተዘናጉ ሠዎችን ደግሞ እንዲህ ሲል ይዝትባቸዋል

(( ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺭَﺑُّﻜُﻢُ ﺍﺩْﻋُﻮﻧِﻲ ﺃَﺳْﺘَﺠِﺐْ ﻟَﻜُﻢْ ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ
ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ ﻋَﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩَﺗِﻲ ﺳَﻴَﺪْﺧُﻠُﻮﻥَ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﺩَﺍﺧِﺮِﻳﻦَ)) [ﻏﺎﻓﺮ 60: ]

"(ጌታችሁ) ለምኑኝ እቀበላቹሀለው እነዚያ እኔን ከመለመን የሚኮሩ የተዋረዱ ሢሆኑ ጀሀነም ይገባሉ አለ "

☞ ከአላህ ውጪ ያለን አካል መለመን ሽርክ ነው!!!

★ እርድ

☞ እርድ ከኢባዳ አይነቶች መካከል የሚቆጠር ነው።
አላህ እንዲህ ይላል ፦

(ﻓﺼﻞ ﻟﺮﺑﻚ ﻭﺍﻧﺤﺮ ) ( ﺍﻟﻜﻮﺛﺮ : 3 )

(ለጌታህ ስገድ እረድም) (አልከውሰር 3)

☞ እርድ የአላህ መብት ነው ከአላህ ውጪ ላለ አካል አሣልፎ መስጠት ከአላህ እዝነት (ከጀነት) ለመባረሩ ምክንያት እንደሆነ ሙስጠፋ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ

"ﻟﻌﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﻦ ﺫﺑﺢ ﻟﻐﻴﺮ ﺍﻟﻠﻪ "

"ከአላህ ውጪ ላለ አካል ያረደ ሠው አላህ ረግሞታል (ከራህመቱ (ከጀነት) አባሮታል "

★ ክጃሎት ፣ ፍራቻ ፣ መተናነስ ፦

☞ አላህ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር (ጀነት) መከጀል ፣ አላህ ዘንድ ያለውን ቅጣት(ጀሀነም) መፍራት እና ለአላህ መተናነስ እና መዋረድ
አላህ እንዲህ ይላል

( ﺇﻧﻬﻢ ﻛﺎﻧﻮﺍ ﻳﺴﺎﺭﻋﻮﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﺨﻴﺮﺍﺕ ﻭﻳﺪﻋﻮﻧﻨﺎ ﺭﻏﺒﺎ ﻭﺭﻫﺒﺎ
ﻭﻛﺎﻧﻮﺍ ﻟﻨﺎ ﺧﺎﺷﻌﻴﻦ )

( እነሡ በመልካም ነገር ላይ የሚቻኮሉ ነበሩ እየከጀሉ እና እየፈሩ የሚገዙ ነበሩ ለኛም የሚተናነሡ ነበሩ)

★ ነዝር (ስለት)

☞ አላህን በማያምፅበት መልኩ መሣል ኢባዳ ነው አላህ ስለ ትክክለኛ አማንያን ሢናገር እንዲህ ይላል

( ﻳﻮﻓﻮﻥ ﺑﺎﻟﻨﺬﺭ ﻭﻳﺨﺎﻓﻮﻥ ﻳﻮﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﺷﺮﻩ ﻣﺴﺘﻄﻴﺮﺍ )

((ስለታቸውን ይሞላሉ ክፋቷ የተሠራጨ የሆነን ቀን ይፈራሉ))

የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ

((አላህን ለማመፅ የተሣለ ስለቱን እንዳይሞላ፣ አላህን ለመታዘዝ የተሣለ ይታዘዘው))

☞ እና ሌሎችም በርካታ የኢባዳ አይነታዎች አሉ እነዚህን የኢባዳ አይነቶች ከአላህ ውጪ ላለ አንድም አካል አሣልፎ መስጠት ከእስልምና ያስወጣል

ይቀጥላል
 

Post a Comment

0 Comments