Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 3

October 18 · · 
 

ተውሒድ አል ኡሉህያ

⊗ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን በአምሎኮ መነጠል ማለት ነው ፣ የአምልኮ አይነታዎችን ከአላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ውጪ ላለ ( ለመላይካ ፣ ለነብይ ፣ ለወልይ ፣ ለሸይጣን…) አለማድረግ

☞ ተውሒድ አል ኡሉህያ ኢባዳን ለአላህ ብቻ ስለማድረግ ስለሚያወራ (ስለሚዳስስ) ተውሒድ አል ኢባዳ በመባል ተጠርቷል 

★ ኢባዳ ማለት ምን ማለት ነው???

☞ በኢባዳ ትርጓሜ ላይ ሀሣባቸዎ አንድ የሆነ እና የቃል አጠቃቀማቸው የተለያየ የሆኑ የበርካታ ኡለሞች አስተያየት አለ ከነዛ ትርጉሞች መካከል ሁሉንም ያቀፈ እና ምጥን እና ግልፅ የሆኑ ቃላቶችን የተጠቀመው የሼህ ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ትርጓሜ እንደሚከተለው ይቀርባል

ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﻗﺎﻝ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
" ﺍﻟﻌﺒﺎﺩﺓ ﺍﺳﻢ ﺟﺎﻣﻊ ﻟﻜﻞ ﻣﺎ ﻳﺤﺒﻪ ﺍلله
ﻭ ﻳﺮﺿﺎﻩ ﻣﻦ ﺍﻷﻗﻮﺍﻝ ﻭﺍﻷﻋﻤﺎﻝ ﺍﻟﻈﺎﻫﺮﺓ ﻭﺍﻟﺒﺎﻃﻨﺔ"
"ኢባዳ ማለት ፦ ከንግግር ፣ ከስራ ፣ በላይኛው እና በውስጠኛው የሠውነት ክፍሎች የሚሠሩ አላህ የሚወዳቸው ተግባራቶችን አጠቃሎ የያዘ ስም ነው "

★የኢባዳ ሸርጦች

☞ ኢባዳ ሦስት ወሣኝ የሆኑ ሸርጦች አሉት

① በአላህ ማመን ፦ አንድ ሠው በአላህ ሣያምን ምንም ያክል እንደ ባህር አረፋ የበዙ ኢባዳዎችን ቢፈፅም ኢባዳው አላህ ዘንድ ቅንጣት ታክል ነገር አይጠቅመውም አሔራ ላይም የማይያዝና የማይጨበጥ ትብያ ሆኖ ነው የሚቀርበት

አላህ እንዲህ ይላል «(ከሀዲያን) ወደ ሚሠሩት ስራ አሠብን የተበተነ አብዋራም አደረጎነው»

②(ኢኽላስ) ፍፁማዊነት ፨ ይህም ማለት የሚሠራውን ኢባዳ ፍፁም ለአላህ ብቻና ብቻ ማድረግ (ስራን ከእዩልኝ እና ከይሰሙላ የፀዳ
ማድረግ ማለት ነው)አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ "ለሡ ሀይማኖትን ጥርት አድርገው እንዲገዙት እንጂ አልታዘዙም "

③ ሙታበአ(ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምን መከተል) ፦ በአላህ ያመነ እንዲሁም ስራውንም አላህ ይመነዳኛል ሢል አስቦ ኢባዳ የሚሠራ ሠው የሚሠራውን ኢባዳ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሠርተውታል አልሠሩትም ብሎ መፈተሽ ይኖርበታል

አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ ""መልዕክተኛው ያመጣላችሁን ያዙት ፣ ከከለከላችሁም ተከልከሉ ""

⇑ ከእነዚህ (ከላይ ከተጠቀሡት ሦስት መስፈርቶች) አንዱን ያጎደለ ኢባዳው ተቀባይነት አይኖረውም!!!

☞ ሙስሊም ያልሆነ ሠው የሠራው ስራ ዋጋ የለውም
☞ ኢቲባእ የሌለው ስራ ቢድአ ነው
☞ የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ እዩልኝ እና ስሙልኝ ነው (ትንሹ ሽርክ ነው)
★ የኢባዳአርካኖች ( መሠረቶች)

☞ ሙስሊም የሆነ፣ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የሠሩትን እና ለአላህ ፊት ብቻ ብሎ ኢባዳ የሚያደር ሠው የሚያደርገው ኢባዳ በሁለት መሠረቶች ላይ የተመሠረተ መሆኑ የግድ ነው ሁለቱ የኢባዳ አርካኖች እንካቹ

① ውዴታ፦ ክጃሎት ፦ አላህን በምንገዛበት ወቅት እየወድነው እና እሱ ዘንድ ያለውን መልካም ነገር እየከጀልን መገዛት አለብን

② ማላቅ ፣ ፍራቻ፦ አሁንም እሱን ስንገዛው እሱን እያላቅነው እና እሡ ዘንድ ያለውን ቅጣት እየፈራን መሆን አለበት

አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ስለነብያቶች የአምልኮ አደራረግ ሢናገር እንዲህ ይላል

ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻳُﺴَﺎﺭِﻋُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺨَﻴْﺮَﺍﺕِ
ﻭَﻳَﺪْﻋُﻮﻧَﻨَﺎ ﺭَﻏَﺒًﺎ ﻭَﺭَﻫَﺒًﺎ ۖ ﻭَﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻟَﻨَﺎ ﺧَﺎﺷِﻌِﻴﻦَ .

"እነሡ በመልካም ነገር ላይ የሚቻኮሉ ነበሩ ። እየፈሩ እየከጀሉ ይገዙን ነበር ለኛም የሚፈሩን ነበሩ "

ይቀጥላል

Post a Comment

0 Comments