Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 2


… የተውሒድ አይነቶች

1 ተውሒድ አሩቡቢያ ፦
⇄⇄⇄⇄⇄⇄

ተውሂዱ ሩቡቢያ ማለት፡- አላህ ብቸኛ ፈጣሪ ተቆጣጣሪና ንጉስ መሆኑን ህያው
አድራጊ ገዳይ ሲሣይ ለጋሽ እሱ ብቻ እንደሆነና ባጠቃላይ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉብ ቸኛ እንደሆነና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

ﺧﻠﻖ ﺍﻟﺴﻤﺎﻭﺍﺕ ﺑﻐﻴﺮ ﻋﻤﺪ ﺗﺮﻭﻧﻬﺎ ﻭﺃﻟﻘﻰ ﻓﻲ ﺍﻷﺭﺽ ﺭﻭﺍﺳﻲ ﺃﻥ ﺗﻤﻴﺪ ﺑﻜﻢ ﻭﺑﺚ ﻓﻴﻬﺎ ﻣﻦ ﻛﻞ ﺩﺍﺑﺔ ﻭﺃﻧﺰﻟﻨﺎ ﻣﻦ ﺍﻟﺴﻤﺎﺀ ﻣﺎﺀ ﻓﺄﻧﺒﺘﻨﺎ ﻓﻴﻬﺎ ﻣﻦ ﻛﻞ ﺯﻭﺝ ﻙﺭﻳﻢ ( 10 ) ﻫﺬﺍ ﺧﻠﻖ ﺍﻟﻠﻪ ﻓﺄﺭﻭﻧﻲ ﻣﺎﺫﺍ ﺧﻠﻖ ﺍﻟﺬﻳﻦ ﻣﻦ ﺩﻭﻧﻪ ﺑﻞ ﺍﻟﻈﺎﻟﻤﻮﻥ ﻓﻲ ﺿﻼﻝ ﻣﺒﻴﻦ ( 11 ) )

‹‹ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ
በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡
ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ (ሉቅማን 1ዐ-11)

ﻗُﻞْ ﺃَﺭَﺃَﻳْﺘُﻢْ ﻣَﺎ ﺗَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻣِﻦْ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺃَﺭُﻭﻧِﻲ ﻣَﺎﺫَﺍ ﺧَﻠَﻘُﻮﺍ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﺃَﻡْ ﻟَﻬُﻢْ ﺷِﺮْﻙٌ ﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ۖ َ ﴿٤﴾

“ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ አሳዩኝ፤
ወይም በሰማያት ለነሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን?” (አል አህቃፍ 4)

ይህ የተውሂድ ክፍል ከእምነት ክፍል ውስጥ አንዱ ቢሆንም አንድ ሰው ይህንን
ብቻ በማመኑ በአላህ አመነ አይባልም እንዲያውም በነብዩ ላይ ጦርነት የከፈቱ
አጋሪዎች በዚህኛው የተውሂድ ክፍል ያምኑ እንደነበር አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች ገልጿል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

ﻭَﻟَﺌِﻦْ ﺳَﺄَﻟْﺘَﻬُﻢْ ﻣَﻦْ ﺧَﻠَﻖَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽَ ﻭَﺳَﺨَّﺮَ ﺍﻟﺸَّﻤْﺲَ ﻭَﺍﻟْﻘَﻤَﺮَ ﻟَﻴَﻘُﻮﻟُﻦَّ ﺍﻟﻠَّﻪُ ۖ ﻓَﺄَﻧَّﻰٰ ﻳُﺆْﻓَﻜُﻮﻥَ ﴿٦١﴾

‹‹ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ
ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ (አንከቡት 61)

ﻭَﻟَﺌِﻦْ ﺳَﺄَﻟْﺘَﻬُﻢْ ﻣَﻦْ ﻧَﺰَّﻝَ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻣَﺎﺀً ﻓَﺄَﺣْﻴَﺎ ﺑِﻪِ ﺍﻷَﺭْﺽَ ﻣِﻦْ ﺑَﻌْﺪِ ﻣَﻮْﺗِﻬَﺎ ﻟَﻴَﻘُﻮﻟُﻦَّ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻗُﻞِ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ ﻟِﻠَّﻪِ ﺑَﻞْ ﺃَﻛْﺜَﺮُﻫُﻢْ ﻻ ﻳَﻌْﻘِﻠُﻮﻥَ [ ﺍﻟﻌﻨﻜﺒﻮﺕ 63:]

‹‹ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት
ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ (አንከቡት 63)

ﻭَﻟَﺌِﻦْ ﺳَﺄَﻟْﺘَﻬُﻢْ ﻣَﻦْ ﺧَﻠَﻘَﻬُﻢْ ﻟَﻴَﻘُﻮﻟُﻦَّ ﺍﻟﻠَّﻪُ ۖ ﻓَﺄَﻧَّﻰٰ ﻳُﺆْﻓَﻜُﻮﻥَ ﴿٨٧﴾

‹‹ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ
(ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ፡፡ (ዙኽሩፍ 87)

}ﻗُﻞْ ﻟِﻤَﻦِ ﺍﻷﺭﺽ ﻭَﻣَﻦْ ﻓِﻴﻬﺎ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ ( 84 ) ﺳَﻴَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﻟِﻠَّﻪِ ﻗُﻞْ ﺃَﻓَﻼ ﺗَﺬَﻛَّﺮُﻭﻥَ ( 85 ) ﻗُﻞْ ﻣَﻦْ ﺭَﺏُّ ﺍﻟﺴَّﻤﺎﻭﺍﺕِ ﺍﻟﺴَّﺒْﻊِ ﻭَﺭَﺏُّ ﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﻟْﻌَﻈِﻴﻢِ ( 86)
ﺳَﻴَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﻟِﻠَّﻪِ ﻗُﻞْ ﺃَﻓَﻼ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ ( 87) ﻗُﻞْ ﻣَﻦْ ﺑِﻴَﺪِﻩِ ﻣَﻠَﻜُﻮﺕُ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻭَﻫُﻮَ ﻳُﺠِﻴﺮُ ﻭَﻻ ﻳُﺠﺎﺭُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﺇِﻥْ ﻛُﻨْﺘُﻢْ ﺗَﻌْﻠَﻤُﻮﻥَ ( 88) ﺳَﻴَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﻟِﻠَّﻪِ ﻗُﻞْ ﻓَﺄَﻧَّﻰ ﺗُﺴْﺤَﺮُﻭﻥَ
( .{(89

«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን
ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)»
በላቸው፡፡ በእርግጥ ‹‹የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ታዲያ አትገሰጹም ፡፡ የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው? «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ እንግዲያ አትፈሩትምን፡፡ የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ
እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ
እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡ (አል ሙእሚኑን 84-89)

ከዚህ የምንረዳው በተውሂዱ ሩቡቢያህ ማመን ብቻ አንድን ሰው ከቅጣት
እንደማያድነው እና ሙስሊምም እንደማያሰኘው ነው፡፡ ስለዚህ በአላህ አማኝ ሙስሊም ለመሆን አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ በአምልኮው ላይ ከማጋራት መጠንቀቅ ግዴታ ነው::

ይቀጥላል

Post a Comment

0 Comments