Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ ክፍል 1


ተውሒድ

ትርጉም ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን በስራው፣ በአምልኮእንዲሁም በስም እና
በባህሪው መነጠል ማለት ነው ።

★ የተውሒድ ትምህርት አስፈላጊነት

☞ ተውሒድ ከሌሎች የውቀት ዘርፎች የመጀመርያ ደረጃ ሊቸረው የሚገባ
የትምህርት አይነት በመሆኑ ላይ ያለ ምንም ተቃርኖ አምነን እንድንቀበል
ከሚያስገድዱን በርካታ ምክንያቶች መካከል የተወሠኑትን እንመልከት

★ ነብያቶች በአጠቃላይ ወደ

የህዝቦቻቸው ሢመጡ መጀመርያ ላይ ይዘውት
የቀረቡት ነገር ተውሒድን ነው

ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻋﻦ ﻧﻮﺡ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ : ( ﻟﻘﺪ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎ ﻧﻮﺣﺎً ﺇﻟﻰ ﻗﻮﻣﻪ ﻓﻘﺎﻝ ﻳﺎ ﻗﻮﻡ ﺍﻋﺒﺪﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ
ﻣﺎﻟﻜﻢ ﻣﻦ ﺇﻟﻪ ﻏﻴﺮﻩ ) ( ﺍﻷﻋﺮﺍﻑ 59/ )

አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ስለ ኑህ አለይሒ ሠላም ሢያወራ " በእርግጥ ኑህን ወደ
ህዝቦቹ ላክነው። (ኑህ) አለ ህዝቦቼ ሆይ ከአላህ ውጪ ሌላ አምላክ የላችሁም
" አእራፍ

ﻭﻗﺎﻝ ﻫﻮﺩ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ ﻟﻘﻮﻣﻪ : ( ﺍﻋﺒﺪﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺎﻟﻜﻢ ﻣﻦ ﺇﻟﻪ ﻏﻴﺮﻩ ) ( ﺍﻷﻋﺮﺍﻑ 65/ )

ሁድ አለይሒ ሠላም "አላህን ተገዙ ከእርሡ ውጪ ሌላ አምላክ የላችሁም
"አእራፍ

ﻭﻗﺎﻝ ﺻﺎﻟﺢ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ : ( ﺍﻋﺒﺪﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺎﻟﻜﻢ ﻣﻦ ﺇﻟﻪ ﻏﻴﺮﻩ ) ( ﺍﻷﻋﺮﺍﻑ 73/ )

ሦሊህ አለይሒ ሠላም " "አላህን ተገዙ ከእርሡ ውጪ ሌላ አምላክ የላችሁም
"አእራፍ

، ﻭﻗﺎﻝ ﺷﻌﻴﺐ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ ﻟﻘﻮﻣﻪ : ( ﺍﻋﺒﺪﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺎﻟﻜﻢ ﻣﻦ ﺇﻟﻪ ﻏﻴﺮﻩ ) ( ﺍﻷﻋﺮﺍﻑ 85/ )

ሹአይብ አለይሒ ሠላም " "አላህን ተገዙ ከእርሡ ውጪ ሌላ አምላክ የላችሁም
"አእራፍ

✔ በአጠቃላይ ስለ ሁሉም ነብያቶች እን ዲህ ይላል

، ﻭﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﻭﻟﻘﺪ ﺑﻌﺜﻨﺎ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺃﻣﺔ ﺭﺳﻮﻻ ﺃﻥ ﺍﻋﺒﺪﻭﺍ ﻭﺍﺟﺘﻨﺒﻮﺍ ﺍﻟﻄﺎﻏﻮﺕ ) (ﺍﻟﻨﺤﻞ 36/ )

በእርግጥ ወደ እያንዳንዱ ህዝብ አላህን ተገዙ ጣኦትንም ራቁ የሚሉ
መልእክተኞችን ልከናል " አል ነህል

، ﻭﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ : ﻭﻣﺎ ﺃﺭﺳﻠﻨﺎ ﻣﻦ ﻗﺒﻠﻚ ﻣﻦ ﺭﺳﻮﻝ ﺇﻻ ﻧﻮﺣﻲ ﺇﻟﻴﻪ ﺃﻧﻪ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺃﻧﺎ ﻓﺎﻋﺒﺪﻭﻥ )
( ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ 25/ )

""ከአንተ በስተፊት ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም እኔን ተገዙኝ ብለን
መልዕክት ያስተላለፍንለት ቢሆን እንጂ መልዕክተኛን አሌላክንም ""

★ የሠው ልጆች እንዲሁም አጋንንቶች የተፈጠሩት ለተውሒድ (አላህን
በብቸኝነት ለመገዛት) ነው

አላህ እንዲህ ይላል

(አጋንንትንም የሠው ልጅንም እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ ለሌላ
አልፈጠርኳቸውም)

★ ተውሒድን አውቆ ያልተገበረው ሠው የሚሠራው መልካም ስራ ፋይዳ ቢስ
ይሆንበታል

☞ በእነዚህ ወሣኝ ምክንያቶች እና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች አማካኝነት
ተውሒድ ከሌሎች የትምህርት አይነቶች ቅድሚያ ሊቸረው የሚገባ የትምህርት
ዘርፍ ይሆናል ።

የተውሒድ ክፍሎች
☞ ኡለሞች ከቁርአን እና ከሀዲስ በመነሣት ተውሒድን ለሦስት ይከፍሉታል
እነሡም
1 ተውሒድ አሩቡብያ
2 ተውሒድ አል ኡሉህያ
3 ተውሒድ አል አስማ ወሢፋት

≅ የተውሒድን በሶስት መከፈል ለሚቆረቁራቸው ሠዎች …

☞ኡለሞች ተውሒድን ወደ ሦስት ጥቅል ወደ ሆኑ ቃላቶች ያመጡት ቁርአን ላይ
ተዘርዝረው የተቀመጡ ቃላቶችን መሠረት በማድረግ ነው እነዚህ የተዘረዘሩ
የቁርአን መረጃዎች በአላህ ፍቃድ ከአይታዎቹ ማብራሪያ ጋር ይመጣል

ይቀጥላል
 

Post a Comment

0 Comments